Monday, April 28, 2014

‹‹አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ዓለም››





ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ
ሦሪያዊው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ባወደሰበት በዕለተ ሐሙስ ምስጋናው አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ዓለም መከዐው ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ወተአገሱ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት፤ ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ስለ እግዚአብሔርም ደማቸውን አፈሰሱ ስለ መንግስተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ በማለት ክብራቸውን ተጋድሏቸውን መዝግቦልናል፡፡

Friday, April 25, 2014

እንደ በግ ብረር እንደ ሰው አምርር



 


ልቤ ሆይ ቸርነትና ምህረቱ በማያልቅ በእግዚአብሔር ምህረት ዳግም ለመገናኘት ስለበቃን አምላካችንን ልናመሰግነው ይገባል፡፡ እንደ ቀደሙ ሁሉ ከሩጫህ አረፍ ብለህ እኔና አንተ ልንነጋገረው የሚገባ  ምስጢር ስላለ ቀርበህ ስማኝ፡፡ ለዛሬ ከአንተ ጋር አንድ አይነት ስህተት የሚያሳዩ ሁለት ምሳሌዎችን ለኑሮህ ወስደን ማየት ይኖርብናል፡፡

ክርስቲያን በመሆንህ ታፍራለህ?



 


ክርስቲያን በመሆንህ በሌሎች ፊት ያፈርህበት ጊዜ ነበር? ምንአልባት ከማያምኑ ጋር ምግብ ልትበላ ቀርበህ ሳለ በእነርሱ ፊት መጸለይ አሳፍሮህ ያውቃል? ወይም ማማተብ እየፈለግህ ሌሎች ስለሚያዩህ እምነት በልብ ነው ብለህ በህሊናዬ አማትቤያለሁ ያልክበት ጊዜ ይኖር ይሆን? ብቻ በአንድም መንገድ ይሁን በሌላ ከማያምኑ ጋር ስትሆን ወይም ለብቻህ ሳለህ የምታደርገውን መንፈሳዊ ነገር ሌሎች ሰዎች የሚሉህን በመፍራትና በማፈር ሳታደርገው ቀርተህ አታውቅ ይሆን? ብዙዎቻችን አምነንበታል ስለምንለው ነገር እኛ ሄደን እነሱ ዘንድ ልንመሰክር ቀርቶ ገና ለገና ያዩናል በማለት ሁል ጊዜ የምናደርገውን መንፈሳዊ ነገር ስንቀንስ ይታያል ይህ ግን ግብዝነት አይደለም ትላለህ?


የሴኬምን እንቅፋት ማስወገድ



 
 
ሴኬም በውስጧ ርኩሰትና አማልክት የሞላባት የአሕዛብ ከተማ ነች፡፡ ከእቅፋቶቿ ብዛት የተነሳ ለመንፈሳዊ ሕይወት ምቹነት የላትም ለዚህም ነበር እግዚአብሔር ያዕቆብን ‹‹ከሴኬም ተነስተህ ወደ ቤቴል ውጣ›› ያለው ዘፍ 35፡1፡፡ ቤቴል ማለት የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው ያዕቆብ ከልጆቹ ላይ ጌጣጌጥን አማልክትን ሳይቀር ተቀብሎ በጉድጓድ ውስጥ ቀበራቸው፡፡ የሴኬም እንቅፋት ናቸውና ለቤቴል ኑሮ አይገቡም፡፡ ይህን ይዞ ቤቴል ቢገዛ ኖሮ የቦታ ለውጥ እንጂ ትክክለኛ የሕይወት ለውጥ አይሆንለትም ነበር እንቅፋቶቹ ዛሬም አሉና፡፡


 







የነፍስ ሕልም

 



የነፍስ ሕልም
በውስጣችሁ ሳለሁ ምናልባት ስሜን ለማታውቁት ነፍስ እባላለሁ፡፡ በዘመናት ሁሉ ስሻውና ስመኘው የነበረው ጊዜ በአምላኬ ፊት ቀርቤ በልቤ የተቀበሩ ጥያቄዎችን አንስቼ እርሱን መጠየቅ ነበር ያሳሰቡትን የማይረሳ የጠየቁትን የማይነሳ አምላክ ፈቅዶልኝ በፊቱ ቀረብሁ፡፡ ከሙሴ ጀምሮ እስከ ባለራዕዩ ወንጌላዊው ዮሐንስ ያሉት እና የእነርሱም መንገድ የተከተሉት አበው እየረዱኝ ዓለምን በያዘበት ክንዱ ተደግፌ ጌታን ፊት ለፊት ማናገር ጀመርሁ፡፡

Thursday, April 24, 2014

‹‹መሳለቂያ እንዳንሆን ተነስተን የኢሩሳሌምን ቅጥር እንስራ›› (ነህ 2፡17)




ይህንን ቃል የተናገረው እስራኤላዊው ነህምያ ሲሆን ዘመኑ የኢየሩሳሌም ቅጥር የፈረሰበት ምድሯ ምድረ በዳ ሆኖ ቤተልሔም ቂያ በቅሎባት ዳዋ ለብሳ አራዊት የሚፈነጩባት ባድማ የሆነችበት ጊዜ ነበር፡፡
ሕዝበ እግዚአብሔር የተባሉ እስራኤል በያዕቆብ ልጅ በዮሴፍ ምክንያት ሀገራቸውንና ርስታቸውን ትተው ወደ ግብጽ ሀገር ተሰደው ወልደው ከብደው በዝተው ይኖሩ ነበረ፡፡ እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ስለነበር ዮሴፍ በነበረበት ዘመን ሁሉ በደስታ ኖሩ፡፡

Wednesday, April 23, 2014

‹‹ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብሩ መጣች›› (ዮሐ ፳፩፣፩)

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን=>በዓቢይ ሃይል ወሥልጣን
ሮ ለሰይጣን => አግአዞ ለአዳም
ሰላም => እምእዘየሰ
ኮነ => ፍሰሃ ወሰላም።
+ ትረጉም +
--------------------
ክርስቶስ በታላቅ ሃይሉና ሥልጣኑ ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነሳ፤
ሰይጠንን አሰረው፤ አዳምን ነፃ አወጣው፤
ከእንግዲህ ወዲህ ፍሰሃ፣ ሰላም፣ ደስታ ሆነ:: አሜን! 

መግደላዊት ማርያም መጌዶል በሚባለው የትውልድ አገሯ መግደላዊት ማርያም ትባላለች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ማርያሞች ስላሉ መግደላዊት ማርያም በመባል ተለይታ ተጠቅሳለች በውስጧ ታላቅ የፍቅር ትንታግ የሚቀጣጠልባት መግደላዊት ማርያም እስከዚህ ቀን ድረስ እንዴት ታግሳ ተቀመጠች? ስንል ጌታችን የተቀበረው ዓርብ ማታ ነው ቅዳሜ እንዳትመጣ የአይሁድ ሰንበት ነው በሰንበት ከተወሰነ ኪሎ ሜትር በላይ መጓዝ ስለማይቻል በሕግ ገደብ ተይዛ ቅዳሜን ከሌሎች ቅዱሳን አንዕስት ጋር በጭንቀት አሳለፈች፡፡

Saturday, April 19, 2014

‹‹ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን መካከል ተነስቷል››

                                                                              
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ~~~~~~በዓቢይ ሃይል ወሥልጣን
ሮ ለሰይጣን ~~~~~~~ አግአዞ ለአዳም
ሰላም ~~~~~~~~ እምእዘየሰ
ኮነ ~~~~~~~ ፍሰሃ ወሰላም። አሜን!!!
+++ ትረጉም +++
ክርስቶስ በታላቅ ሃይሉና ሥልጣኑ ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነሳ፤
ሰይጠንን አሰረው፤ አዳምን ነፃ አወጣው፤
ከእንግዲህ ወዲህ ፍሰሃ፣ ሰላም፣ ደስታ ሆነ!!! አሜን!


ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ነውና መቃብር ይዞ አላስቀረውም፣ ትንሣኤ ነውና ሞት በእርሱ ላይ ስልጣን አልነበረውም በመሆኑም ከሦስት መዓልትና ሌሊት በኋላ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ሞትን ድል አድርጎ መውጊያውንም ሰብሮ በኃይሉ ተነስቷል፡፡ ‹‹ኦ መዊት አይቴ ሃሎ ቀኖትከ›› ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህ የታለ›› ተብሎ በትንቢት በተነገረው መሠረት ገዥውንና ኃያሉን አሸንፎ መውጊያውን ሰብሮ ጌታችን ተነስቷል፡፡



Thursday, April 17, 2014

‹‹ከክርስቶስ ጋር አብረን ከሞትን አብረን እንነሳለን››

‹‹ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሳኤውንም በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን›› ሮሜ 6፡5

 
 

‹‹ከክርስቶስ ጋር አብረን ከሞትን አብረን እንነሳለን››
ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተውን አዳም ለማዳን ሥጋን ተዋሕዶ እንደሚሞት የሚያውቀው ከዘመናት በፊት ነው፡፡ ቤተልሔም ከመወለዱም በፊት የሚሞትበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ፣ የሰውን ልጅ ሥጋ የለበሰውም ሞቶ ሞትን ለመግደል እንደሆነ ያውቃል የመጣበት ዓላማም ለሞመት ነው ለደቀመዛሙርቱም በተለያየ ጊዜ በምሳሌ ነገረ ሞቱንና ጊዜያቱን ነግሮአቸዋል፡፡ ‹‹በደብረታቦር ብርሃነ መለኮቱን ከገለጸበት ቀን ጀምሮ አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀመዛሙርቱ ይገልጥላቸው ነበር›› (ማቴ 16፡21) ለሚጠሉት ላሰቃዩት ለአይሁድ እንኳ ሳይቀር በምሳሌ ይነግራቸው ነበር ‹‹ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ›› አላቸው፡፡ (ዮሐ 3፡19)

Thursday, April 10, 2014

‹‹የአሸናፊነት የድል ጩኸቶች››




ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለ በኋላ በመስቀል ላይ ሆኖ የተናገራቸው 7ቱ አጻርሐ መስቀል በመባል የሚታወቁት የአሸናፊነት የድል ጩኸቶች ናቸው፡፡
1. ‹‹ኤሎኼ ኤሎኼ ኤልማስ ላማ ሰብቅታኒ››
አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ማለት ነው (ማቴ 27፡46) ይህን አሰምቶ የተናገረው በ9 ሰዓት ነው እርሱ አምላክ ሆኖ ሳለ አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ ብሎ የተናገረው ለምንድን ነው፣ ቢሉ ከሕገ-እግዚአብሔር ርቆ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የተተወ አዳምን ሥጋ ተዋሕዶ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጥ ነው፡፡
ይህንን ቃል አምላካችን ስለ ብዙ ነገር ተናግሮታል

አቤቱ እባክህ አሁን አድን-ሆሳዕና



የዛሬ 1970 ዓመት አካባቢ በነገስታቱ ዘንድ ታይቶ የማይታወቅ አዲስ ነገር በኢየሩሳሌም ታየ፣ ነገስታት በጠባቂ ወታደር ታጅበው በልዩ ፈረስ ሲሰግሩ ለንጉስነታቸው ዘውድ ሲደፋላቸው የአበባ ምንጣፍ ሊነጠፍላቸው ሲገባ አዲሱ ንጉሥ የነገስታት ንጉስ ሆኖ ሳለ በተለየ ሁኔታ ለነገስታት ክብር ባልተለመደ ዘይቤ ወደ ኢየሩሳሌም ብቅ አለ፡፡



Monday, April 7, 2014

የቀድሞው ስምዖን ዛሬ በእኔ ውስጥ እንዴት ይቀየር?

 



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ይድረስ የእግዚአብሔር መንግስት ቁልፍ በእጁ ላለ ስለ ሞተልህም ስለ ክርስቶስ ስም በሮም አደባባይ ቁልቁል ለተሰቀልህ ታማኝ ምስክር ለሆንከው ለቅዱስ ጴጥሮስ፡፡ በጌታ ፊት በምስጋና ለጸናች ነፍስህ ሰላም እላለሁ፡፡ ጴጥሮስ ሆይ ከዚህ ምድር ከተለየህባት ጊዜ ጀምሮ ስለ ነፍሴ እየተጋህ እንደሆነ እምነቴ ነው፡፡ ጴጥሮስ ሆይ የፈተናው ዓለም ሕይወት እንዴት ይዞሃል? ብትለኝ ልክ አንተ በመንፈስ ቅዱስ ታድሰህ በእምነትና በቅድስና ከመመላለስህ በፊት ያለውን የቀደመ ሕይወትህን ይመስላል እልሃለሁ፡፡

ሁለተኛው ሻማህ ካልጠፋ ሌሎቹ ይበራሉ

 

 


(አባት ልጃቸውን ሲመክሩ)
ጥንት ነው አሉ አንድ ሰው ከሰማይ ወደዚህ ና ! ተመልከትም የሚል እንደ ውሃ የሚፈስ ድምጽ ሰማ፡፡ ሄደ! አየም እነሆ በአንድ እጅግ ጠባብ በሆነ መንገድ ላይ ሶስት ሻማዎች ይበሩ ነበር፡፡ የሚገርመው የመጀመሪያው ሻማ እምነት ሁለተኛው ተስፋ ሶስተኛውም ፍቅር የሚባሉ ስሞች ነበሯቸው፡፡