Tuesday, December 23, 2014

"የምሥራች መድኃኒት ተወልዷል" ሉቃ 2÷11


 

ይህንን የምስራች ቃል ያበሰሩ ከምስራቃዊ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ ከዳዊት ከተማ በቤተልሔም መንደር የነበሩ እረኞች ናቸው፡፡ (ማቴ 2÷2፣ ሉቃ 2÷5) እነዚህ የቤተልሔም በግ ጠባቂዎች ቀድሞ ያላዩትን በማየታቸው ሰምተው የማያውቁትን ጥዑመ ዜማ በመስማታቸው የደስታ ጸዳል በፊታቸው በራ ፡፡ ልባቸው የመላዕክትን ቋንቋ ለመስማት በሐሴት ተሞልታለችና ዝማሬያቸው አጥናፍ አቋርጦ ተሰማ፣ ከወዲያኛው ሀገር ወዲህ አስተጋባ የእረኞቹ ቅላጼ እስከ ሄሮድስ ቅጽረ መንግስት ድረስ ዘልቆ በመግባቱ የልደቱ ዜና የጠላትን ወረዳ አስጨነቀ ሽብርና ትርምስ ግርግርንም ፈጠረ የመምጣቱን ነገር በጽናትና በጉጉት ሲጠብቁ ለነበሩት ግን የደስታ ቀን የሐሴት ዘመን የተወደደች ዓመት ሆነ፡፡ በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፣ በቤተልሔም የብርሃን አምድ ተተከለ መላዕክት የእረኞችን ፍርሃት አርቀው ለዝማሬ በአንድ ላይ ቆሙ… ስብሐት ለእግዚአብሔር በአርያም ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብዕ" የተራራቁት ተቀራረቡ የተጣሉት ታረቁ ለዘመናት ተጋርዶ የነበረው የጸብ ግርግዳም ፈረሰ "እርሱ ሰላማችን ነውና ሁለቱን አዋሐደ" (ኤፌ 2÷14) (ኢሳ 9÷2)፡፡

በእሳትና በውሃ መካከል አሳለፍከን(መዝ65/66:12)


 

 

ይህንን ቃል የተናገረ ልበአምላክ ቅዱስ ዳዊት ሲሆን ለጊዜው የሕዝበ እስራኤልን ከግብፅ ምድር መውጣት አስመልክቶ ተናግሮታል፡፡ እስራኤል ከ430 ዓመት የግብፅ ስደትና የባርነት ኑሮ ቢከብዳቸው መከራው ቢበዛባቸው ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡ በተለይ የልጆቻቸው ሐዘን ልባቸውን የሰበረው ራሔልና መሰሎቿ የእስራኤል እናቶች እንባቸውን አፍስሰው ወደ መንበረ ፀባኦት ወደ እውነተኛው ዳኛ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ "የአምብርሃምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ ሆይ ወዴት አለህ? አብርሃምን ዘሩን ያበዛህ በዘርህ ምድር ይባረካል ብለህ ተስፋ የሰጠህ ይስሐቅንም የታደግህ ያዕቆብንም እንደ መንጋ የምትጠብቅ እረኛችን እግዚአብሔር ሆይ እስከመቼ ፈጽመህ ትረሳናለህ? እያሉ አብዝተው ተማጸኑ፡፡

Monday, December 15, 2014

የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ስለ ክርስቶስ ስለ አንዲት ሃይማኖት ያደረጉት መንፈሳዊ ተጋድሎ

 ክፍል ሶስት፡-

ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ!!! ሮሜ 13፡7
አባታችን በሃይቅ ከእየሱስ ኖሃ ጋር እግዚዓብሄርን በማገልገል ለ12 አመት ከቆዩ ቡኋላ በጸሎት ላይ ሳሉ ምንግዜም ከአባታችን ተክለ ሃይማኖት የማይለይ የእግዚዓብሄር መላዕክ ቅዱስ ሚካኤል ከድንገት ከምድር ነጥቆ ወደ ሰማይ አወጣቸው ነብያት እግዚዓብሄርን በከፍተኛ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ አየሁት ብለው እንደተናገሩ አባታችን በእግዚአብሄር ዙፋን ፊት ቀረቡ አእላፍ መላዕክት ሲያመሰግኑት አዩ ከዚህ ቡኋላ ክፍልህ ከሃያራቱ ካህናት ጋር ይሁን የሚል ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ አባታችንም የወርቅ ጽና ይዘው ከሃያራቱ ካህናት ጋር ሃያ አምስተኛ ሆነው በሰማይ ያጥኑ ጀመር አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ በማይታጠፍ ህያው በሆነ ቃሉ ቃል ኪዳን ገባላቸው፡፡ እርሱ ከመረጥኩት ጋር ቃል ኪዳኔን ፈጸምኩ እንዳለ አምላካችን እንዲሁ እንደወደከኝ እወድሃለሁ ስምህን ክቡር አደርገዋለሁ በጸሎትህ የሚተመነውን ሰው ሁሉ ስለ አንተ ይድናል መታሰቢያህን የሚያደርግ ሁሉ እኔ በሰማይ አከብረዋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ገባላቸው፡፡ አባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ ምድር ተመለሱ በዚህ ግዜ ወደ ፊት ስላላቸው ተስፋ ስለ እግዚአብሄር ፍቅር እንደ እሳት ልባቸው ነደደ የእግዚአብሄር መንፈስ ያሉባቸውን መጽሐፍት ያነባሉ ሌትና ቀን እየተጉ ይጸልያሉ እንቅልፍ በአይናቸው አይመጣም ከሰማይ ከተመለሱ በኋላ በሃይቅ ለአስር አመት ኖሩ፡፡

የአባታችን የጻድቁ ተክለ ሃይማኖታ የህይወት ታሪክ ስለ ክርስቶስ ያደረጉት መንፈሳዊ ተጋድሎ

 ክፍል ሁለት፡-

እግዚአብሔር ያከበረውን ክቡር ብትለው ከንቱ ነገር ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው ያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል በምድር ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፡፡ ኢሳ 58÷13-14

ጻድቅ አባ ተክለ-ሃይማኖት


አባታችን ተክለ-ሃይማኖት ስለ አንዲት ሃይማኖት ስለ አንድ አምላካችን በስሙ ስላደረጉት ተዓምር መንፈሳዊ ተጋድሎ አጭር የህይወት ታሪክ ፡-
የኢትዮጵያ ብርሃን የእግዚ/ር አብ ምሩጥ አባታችን ተክለ-ሃይማኖት የኢትዮ ቤተ- መንግስት ከአክሱም ወደ ላስታ የተዛወረበት ዘመን ላይ በዮዲት ወረራ ወቅት ተደናግጦ የነበርው ህዝበ ክርስቲያኑ ተረጋግተው በሃይማኖታቸው እየበረቱና እየጸለዩ አምላካቸውንና አምላካችንን እያመሰገኑ የነበሩበት ዘመን ነበረ በወቅቱ የነበሩት ነገስታት እየመነኮሱና ምንኩስና እየተስፋፋ የነበረበት ወቅት ነው፡፡

Tuesday, December 9, 2014

መንገደኛዋ ታዛቢ

 
መንገደኛዋ ታዛቢ
ወቅቱ ክረምት ነው የአየሩ ሁኔታ  የቅዝቃዜው ነገር አያድርስ ነው በረዶው መኪናም አያስነዳም በእግርም አያስጉዝም ባጠቃላይ ምን አለፋችሁ የዚህ ዓለም ጣጣ ባይኖር ኖሮ ከቤት መውጣት አያስመኝም ነበር በማግስቱ ታህሳስ 19 ቀን የመላዕኩ የቅዱስ ገብርኤል ክብርና ልዕልና የሚነገርበት የእነዚያ ሶስት የእምነት ጀግኖች የሲድራቅ የሚሳቅና የአሚዲናጎም የእምነት ምስክርነት የሚወሳበት ታላቅ ክብረበዓል ነበር፡፡ እኔም የዚህን ብስራታዊ መልዓክ ተ ለመስመትና የእነዚህን ሶስት ቅዱሳን ወጣቶችንም የእምነት ምስክርነት ከምንም በላይ ደግሞ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተአምር ለማየት ፈለግሁና በመላዕኩ በቅዱስ ገብርኤል ስም የታነፀውና በአካባቢው ምዕመናን አማካኝነት ወደ ተሠራው በዋሽንግተን ሲያትል ወደ ሚገኘው ቤተክርስቲያን ተጉዤ ነበር በአካባቢው በርካታ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰቦች የሚገኙ ሲሆን ከምንም በላይ ግን ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላቸው እግዚአብሔር ለራሱ የመረጣቸው የቤተክርስቲያን ማህበረሰቦችም አሉ፡፡