Monday, November 9, 2015

+የሲኦል ደጆች አይችሏትም+



    ንፅህት ብርሕት የሆነችው ጥንታዊትና ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለ2000 ዓመታት ፈተናን ያሳለፈች መከራን የተጋፈጠች ሃይማኖት ናት።
    ሀ) ከውስጥ በቢፅ ሐሳውያን ወይም በሐሰተኞች ወንድሞች ለቤተክርስቲያን ክብር የቆሙ በመምሰል የራሳቸውን ጥቅምየሚያስከብሩ እንደ ይሁዳ በገንዘብ የሰከሩ ገንዘብ ከተከፈላቸው ዲያንሎስንም ቢሆን የሚያመልኩ
    ሌሎቹም ውሻ በበላበት ይጮሃል እንዲሉ ከዚህ ጥቅም የተነካኩ የፈጠራቸውን ጌታ ሳይቀር የሸጡ ...
    ለመንጋው ግድ የሌላቸው እውነትን በሐሰት መጋረጃ ሸፍነው ብርሃን በወጣበት ዘመን በጨለማ የሚኖሩ የቤተክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች የስሜት ክርስቲያኖች

መልዕክቶች እንሁን ሁሉም የሚያነበን


    ክርስቲያን ለመሆን መንገድ ላይ ለቆምነው
    ጉዞ ሳንጀምር ሁሉን ለፈጸምነው
    "ሳይገባን" ምስጢሩ የክርስቲያን ግብሩ
    ፊደልም ሳንቆጥር ሳንማር ጠንቅቀን
    መጻሕፍትንና ኃይሉንም ላላወቅን...
    እዚህኛው ጥልቅ እዚያኛው ዘው ላልን
    ንብ መሆንን ትተን እንደ እርጎ ዝንብ ለሆን
    ራሳችን ከሳሽ እኛው ዳኛ ሆነን
    በፍርድ አደባባይ ሁሉን ለወነጀልን
    ከውስጣችን ጠፍቶ ትህትናና ትዕግስት
    ማክበር መከባበር ከቶ ለተሳነን
    እንደ ባለ አእምሮ በማስተዋል ሆነን
    ቆም እንበልና ጉዞውን እንጀምር
    በፊደልም ሳይሆን በትርጉም እንኑር
    ፀጋችን እናብዛ በቃሉ ተሞልተን
    መልዕክቶች እንሁን ሁሉም የሚያነበን
    ተፃፈ፣ጥቅምት፪፯፣፪፼፰


+ዓለም ዉለታዋን ከቶ እንዴት ረሳ+


                                          ዓለም ዉለታዋን ከቶ እንዴት ረሳ
                                      ======================    
    አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን


    ዓለም ሳይፈጠር ከፍጥረቱም በፊት
    በአምላክ ኅሊና የታሰበችውን
    ጽድቅ ልምላሜ ከአዳም ጠፍቶ ሳለ
    ንጽሕት ዘር ሆና የተገኘችውን...
    ሰላምን ጸንሳ የወለደችውን
    በትንሿ እጆቿ የታቀፈችውን
    ከዘንዶው ደብቃ የሸሸገችውን
    በጀርባዋም አዝላ የባዘነችውን
    ዓለም ውለታዋን ከቶ እንዴት ረሳ
    ኢየሱስ ኢየሱስ የምትሉ እናንተ
    ነገር ግን ማርያምን ለረሳችሁ ሁሉ
    ዓይናችሁ ይከፈት ብርሃኑን እዩ
    ባይሆን ውለታዋን እንድታስተውሉ
    ሕብስት ተሸክማ የተራበችውን
    ወይኑን በጀርባ አዝላ የተጠማችውን
    የግብፅን በረሃ የታገሰችዉን
    ድልድይ የሆነችን መሸጋገሪያችን
    መሰላልም እሷ መዉጫ መውረጃችን
    ምክንያት የሆነች ለድህነታችን
    ጌታን ያየንባት ምክንያት እሷ ናት
    ተፃፈ፣መስከረም፪፮፣፪፼፰




      ጥቅምት 16-የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ በስደቷ ወራት ያደረገችው ተአምር ይህ ነው፡- መልአኩም ለዮሴፍ ተገልጦለት ‹‹ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሥ ሕፃኑንና እናቱን... ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› አለው፡፡ እርሱም ወዲያው በሌሊት ተነሥቶ ይዟቸው ሸሸ፡፡ ከናዝሬት ጀምረው የባሕሩን ዳርቻ ይዘው እስከ ፍልስጤም ደረሱ፡፡ በ6ኛው ቀን ደክሟቸው አንድ ዋሻ ውስጥ ገቡ፡፡ እመቤታችንም በጸሎቷ ውኃን አመነጨችና ጠጡ፡፡ ያም ምንጭ ስሙ የማርያም ውኃ ተብሎ እስከዛሬ አለ፡፡ በሌሎችም ቦታዎች እመቤታች ስትጸልይ ውኃ እየፈለቀ በእርሱ ልጇን ገላውን ታጥበዋለች፡፡ ዐሥር ቀን ያህል በይሁዳ ሀገር፣ ዐሥር ቀን ያህል በምድረ በዳ እጅግ አስቸጋሪ ጉዞ ከተጓዙ በኋላ ግብፅ ደረሱ፡፡ ጌታችንም ምድረ ግብፅ በደረሰ ጊዜ በነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት መሠረት የግብፅ ጣዖታት ከመሠረታቸው ተነዋውጠው ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻቸው፡፡ በግብፅ ኤሌዎጶሊዎስ ሀገር ገብተው ዮሴፍ ማረፊያ ሠራ፡፡ በዚያም ባለች ተራራ ሥር ጌታችን ውኃን አፈለቀ፡፡ ይህችውም በእኛና በቅብጥ ሰዎች ዘንድ ሰኔ 8 ቀን የምትታሰበው ዕለት ናት፡፡
      ደም ማፍሰስ የለመደ ርጉም ሄሮድስ ሚስቱን ማርያናንም ከገደላት በኋላ ይበቀሉኛል በማለት ከእርሷ የወለዳቸውን የገዛ ልጆቹንም ገደላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ በሥጋው ጽኑ መከራ መጣበትና እግዚአብሔር የደዌውን ዘመን አስረዘመበት፡፡ ቢበላ ቢበላ ይጠግብም ይልቁንምረሀብና ጥም ይበዛበታል፣ አንጀቱም ተቋጠረ፣ ሰውነቱም ተልቶ ሰው ሁሉ አልቀርበው አለ፡፡ ማቆ ሲያበቃ በመጨረሻም ክፉ አሟሟት ሞተ፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ ዮሴፍን ሄሮድስ ስለሞተ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል እንዲመለስ ነገረው፡፡ ተመልሰውም በፍልስጤም አልፈው ድልማጥያ ወደምትባል አንዲት ገር ደርሰው በበረሃ ውስጥ ተቀመጡ፡፡ እመቤታችንም ከነልጇ ረኃቡ ቢጠናባት ትዕማን ወደምትባል አንዲት ከበርቴ ባለሀብት ቤት ሄዳ ቁራሽ እንጀራንና ለልጇም ጥቂት ወተትን ለመነቻት፡፡ ያቺ ክፉ ሴት ግን ልብን በሀዘን የሚሰብር ክፉ ንግግርን ተነጋረቻት፡፡ ጻድቅ ዮሴፍም ‹‹እንግዳን ካለ ይሰጡታል ከሌለ በሰላም ይሸኙታል እንጂ ለምን ክፉ ንግግርን ትናገሪያታለሽ?›› እያለ ሲነጋገሩ አሽከሯ ኮቲባ የእመቤቷን ቁጣ ሰምታ መጥታ ጌታችንን ከመሬት ላይ ጥላ እንደ ድንጋይ አንከባለለችው፡፡ እመቤታችንም እጅግ ደንግጣ እያለቀሰች ልጇን ፈጥና ልታነሣው ስትል ዮሴፍ ‹‹ተይው አታንሽው ኀይሉን ያሳይ›› አላት፡፡ ያንጊዜም ትዕማንን ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻት፡፡ ገረዷ ኮቲባም በለምጽ ተመታች፡፡ በቤታቸውም ውስጥ በሕይወት የቀረ የለምና የሩቅ ቤተሰቦቿም ጦጣ ሆነው ከተራራ ወደ ተራራ ሸሹ፡፡ እመቤታች፣ ዮሴፍና ሰሎሜም በትዕማን ቤት 6 ወር ከተቀመጡ በኋላ መልአኩ ተገልጦ ከዚያ እንዲወጡ አዘዛቸውና ወጡ፡፡ አርዲስ ወደምትባል ሀገርም ደርሰው የሀገሪቱ ሰዎቸ በሰላም ተቀብለው አስተናገዷቸው፡፡ እመቤታችንም ከገረ ገዥው ሆድ ውስጥ በጸሎቷ እባብ ስላወጣችለትና ከሕመሙ ስላደ በጣም አከበሯቸው፡፡ ዕውሮችን፣ አንካሶችን፣ ለምፃሞችንና አጋንንት ያደሩባቸውን ሁሉ እያመጡላት የልጇን እጆች ይዛ ከሩቅ እያማተበች ፈወሰቻቸው፡፡ ሄሮድስም እንደሚያፈላልጋቸው መልአኩ ሲነግራቸው ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር እየተዘዋወሩ ታችኛው ግብፅ ንሂሳ ድረስ ደረሱ፡፡ እመቤታችንም በዚያ ያሉ ሕመምተኞችን ፈወሰችላቸው፡፡

      ከዚህም በኋላ አሁንም መልአኩ ነግሯቸው ደመናም መጥታ ነጥቃ ወሰደቻቸውና የ38ቱን ወራት መንገድ በአንድ ጊዜ አደረሰቻቸው፡፡ በዚያም ትንሽ ከቆዩ በኋላ ወደ ቤጎር ቆላ ደረሱ፡፡ በዚያም ግብፃውያን እንደ ሕጋቸው ለአማልክቶቻቸው ላሞችን አርደው ሠውላቸው፡፡ በጎሽ፣ በአውራሪስ፣ በነጭ ዝንጀሮ የሚመሰሉ አጋንንትም መጡ፡፡ እመቤታችንም ከሩቅ ሆና ተመልክታቸው እነዚያን አጋንንት በጸሎቷ እንደጢስ በተነቻቸው፡፡ ግብፃውያንም ፈርተው እየጮኹ ሸሹ፡፡ በዚያም ወራት ‹‹ረዳት አማልክቶቻችንን ጠፉብን›› ብለው እያዘኑ ሳለ ዮሴፍን ሲጸልይ አግኝተውት አስረው በምድር ላይ አስተኝተው 40 ግርፋት ገረፉት፡፡ እርሱም በዚህ ጊዜ ‹‹እመቤቴ ሆይ ስለ አንቺና ስለ ልጅሽ ይህ መከራ አግኝቶኛልና እርጂኝ›› ብሎ በኀይል ጮኸ፡፡ እመቤታችንም ድምጹን ስትሰማ የሄሮድስ ጭፍሮች የመጡ መስሏት እጅግ ደነገጠች፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ተገልጦ ካረጋጋት በኋላ ዮሴፍን በኀይል ይደበድቡ የነበሩትን በእሳት ሰይፉ ጨረሳቸው፡፡ ዮሴፍንም በእጆቹ ዳሰሰውና ፈወሰው፡፡ እመቤታችንም ዮሴፍን ባየችው ጊዜ ‹‹ይህ ሁሉ መከራ ያገኘህ በእኔና በልጄ ምክንያት ነው›› ብላው አንገት ለአንገት ተቀቅፈው ተላቀሱ፡፡ መልአኩም ‹‹ይሄ ሀዘናችሁ በደስታችሁ ጊዜ ይረሳል…›› እያለ አረጋጋቸውና ዐረገ፡፡ የሀገሩ ሰዎችም ይወጓቸው ዘንድ ወጡና ክፉ ውሾችን ለቀቁባቸው፡፡ ነገር ግን ውሾቹ በሰው አንደበት እመቤታችንን እያነጋገሯት ሰግደው የእግሯን ትቢያ ልሰው በመመለስ ባለቤቶቻቸውን መልሰው መናከስ ጀመሩ፣ ብዙዎቹንም ገደሏቸው፡፡ አገራዊ ዮሴፍም ‹‹እመቤቴ ሆይ በዚህ ሀገር ከምንኖርስ በዱር በበረሀ ብንኖር ይሻለናል›› ብሏት ወደለሌላ ትርጓሜዋ የሰላም ሀገር ወደሆነች ዲርዲስ ሀገር ደረሱ፡፡ ሰዎቹም ‹‹ይህችስ የነገሥታት ወገን ትመስላለች በላያችን ላይ ትነግሥብናለች›› ብለው በክፉ ሲነሱባቸው በማግስቱ ደመና ነጥቃ ወስዳ ኤልሳቤጥ በሞት ካረፈችበት በረሀ አደረሰቻቸው፡፡ ዮሐንስ በእናቱ በድን ላይ ሆኖ እያለቀሰ ሳለ ዮሴፍንና ሰሎሜን ባያቸው ጊዜ ደነገጠ፡፡ ጌታችንም አረጋጋው፡፡ እመቤታችንም ስለ ኤልሳቤጥ ሞት እጅግ መሪር የሆነ ልቅሶን ስታለቅስ ልጇ ድንቅ ምሥጢርን ከነገራት በኋላ አረጋጋት፡፡ እመቤታችንም ‹‹እናቱ ሞታበታለችና በዚህም በረሀ ማንም የለመውና ዮሐንስን ከእኛ ጋር እንውሰደው›› ስትለው ጌታችን ‹‹ዕድሉ በዚህ በረሀ ነው›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ከዚህም በኋላ ደመና ነጥቃ ወስዳ ወደ ጋዛ ምድር አደረሰቻቸውና በዚያ አተር የሚያበራዩ ሰዎችን አግኝታ እመቤታችን ‹‹ለልጄ አተር ስጡኝ›› አለቻቸው፡፡ እነርሱም ክፉዎች ነበሩና ‹‹ይህ አተር ሳይሆን ድንጋይ ነው›› አሏት፡፡ ሕፃኑ ልጇም ‹‹እናቴ ሆይ እንደቃላቸው ይሁንላቸው ተያቸው›› አላት፡፡ ያንጊዜም አተሩ ድንጋይ ሆነ፣ ይህም እስከዛሬም ድረስ አለ፡፡
      ዳግመኛም ዛሬ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 49ኛ የሆነ ቅዱስ አባት አባ ያቃቱ ዕረፍቱ ነው፡፡ ከእርሱ በፊት የነበረው አቡነ ብንያሚን በሞት ባረፈ ጊዜ ይህን ቅዱስ አባት መርጠው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት፡፡ ነገር ግን በዘመኑ ከሃዲያን ብዙ ያሠቃዩት አባት ነው፡፡ ስሙ ቴዎዶስዮስ የሚባል መለካዊ ካሃዲ ሰው ነበር፡፡ እርሱም ወደ ደማስቆ ንጉሥ ዘይድ ዘንድ ሄዶ ብዙ እጅ መንሻን ሰጥቶ ለእስክንድርያ አገረ ገዥ ሆኖ ተሾመ፡፡ ከተሾመም በኋላ አባ ያቃቱንን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ በየዓመቱ ግብር እያለ ሰባት ሺህ የወርቅ ዲናር ከአባታችን እየተቀበለ እግዚአብሔር እስካጠፋው ድረስ አባታችንን እጅግ አሠቀያቸው፡፡
      በአባታችን ዘመን የብዙዎች ቅዱሳን አባቶች አባት የሆነው የአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃዋ ተፈጸመ፡፡ በአንዲት ሌሊት ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለአቡነ ያቃቱን ተገለጠላቸውና ፍዩጥ በሚባል አገር በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ዮሐንስ የሚባል ጻድቅ መነኮስ እንዳለ ነገራቸው፡፡ ዳግመኛም መልአኩ ዮሐንስን አስመጥተው በእሳቸው ቦታ እንዲሾሙት ነገራቸው፡፡ አባታችንም ሰዎችን ልከው ቅዱስ ዮሐንስን ካስመጡት በኋላ ሥራቸውን ሁሉ አስረክበውት በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፈዋል፡፡ በረከታቸው ይደርብን፡፡
      ዳግመኛም ዛሬ የአቡነ አሮን ዘአርምሞ በዓለ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ይኸውም አቡነ አሮን ዘአርምሞ መጽሐፍ አሮን ዘከትሞ ወዘአርምሞ ይላቸዋል፡፡ የትውልድ ሀገራቸው ትግራይ ተንቤን ነው፡፡ ለ48 ዓመታት ከሰው ጋር ምንም ሳይነጋገሩ በዝምታ ብቻ የኖሩ ታላቅ አባት ሲሆኑ ቀዳማዊ ዘኢትዮጵያ ከተባሉት የመጀመሪያዎቹ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ ቤተ መቅደስ ገብተው ሲያጥኑ ርግብ ዕጣን ታመጣላቸው ነበር፡፡ ምግባር ቱሩፋታቸው እጅግ ያማረው እኚህ አባት በዘመናቸው ድርቅ በሆነ ጊዜ የእህል እጦት ድርቅ ሆኖ ሕዝቡን ሰብስበው እግዚኦታ ካደረሱ በኋላ የሀገሩን ሁሉ ጎተራ በተአምራት በእህል ሞልተው አትረፍርፈውታል፡፡ በዚህም አስገራሚ ተአምራቸው ሕዝቡንም ከችግርና ከርሃብ አድነውታል፡፡
      አቡነ መድኃኒነ እግዚአ ዘደብረ በንኮል አህያቸውን የበላባቸውን አንበሳ በአህያው ምትክ 7 ዓመት ውኃ እንዳስቀዱት ሁሉ አቡነ አሮንም ነብርን 7 ዓመት ውኃ እያስቀዱ እንዲያገለግላቸው አድርገውታል፡፡ ሌሎች የዱር አራዊትም ያገለግሏቸው ነበር፡፡ በአንድ ወቅት በሀገሩ ድርቅ ሆኖ ሰው ግማሹ ተሰዶ ግማሹ ደክሞ ስለነበር ጻድቁ ግን የዱር አራዊትን ጠርተው ሠራተኛ አድርገው በማዘዝ ጥንቸልን ውኃ በማስቀዳት፣ ጅብን ጭቃ በማስረገጥ፣ አንበሳን በአናጺነት እንዲሠራ፣ ነብርን ደግሞ አቀባይ በማድረግ እያዘዙ በማሠራት በእመቤታችን ስም እጅግ አስደናቂ ቤተክርስቲያን መስከረም 10 ቀን ሠርተዋል፡፡ የአቡነ አሮን ዘአርምሞ የአንድነት ገዳማቸው ትግራይ ሽሬ ውስጥ ይገኛል፡፡ በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን፡፡
      የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ከስደቷ ረድኤት በረከት ትክፈለን! ዓለምን ሁሉ ፈጥሮ የሚገዛ ሁሉን ማድረግ የሚችል የተወደደ ልጇን መድኃኔዓለምን ይዛ በመሰደድ ብዙ የተሠቃየች ክብርት እመቤታችን እኛንም የምታመንባት ልጆቿን ከኃጢአትና ከዓለም ፍቅር የምንሰደድ ታድርገን!!!
      (ምንጭ፡- ገድለ አቡነ ዮሴፍ አረጋዊ፣ ስንክሳር ዘወርሃ ጥቅምት፣ የቅዱሳን ታሪክ፣ ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን)

ቅዱሳን ምን አሉ

                                                            +ቅዱሳን ምን አሉ+
                                                          ==============


    እስኪ ጠይቋቸው ቅዱሳን ምን አሉ
    ምግባራቸው ቀንቶ በጎውን የሰሩ
    እምነታቸው ጸንቶ ተዋሕዶ ርትዕት
    ንጽሕት ና ብርህት ቅድስት ናት ያሉ
    ክብራቸውን ትተው ከዓለም የተለዩ...
    በዱር በሸንተረር በየፍርክታው
    በግበበ ምድር በዋሻ የኖሩ

ፍቅሩ ግድ ይለናል

                                                                        +ፍቅሩ ግድ ይለናል+
                                                                   ===============
        

    ይህንን ስለቆረጥን
    ከእንግዲህ በኋላ
    በቀሪው ጊዜያችን
    በተሰጠን ዘመን...
    በሕይወት ያለነው
    በጌታ የምንኖር
    ጥምቀቱን ለመምሰል
    አብረን ከተጠመቅን
    ሞቱንም ለመምሰል