Monday, January 6, 2014

‹‹በተወደደችው ዓመት››






በተወደደችው ዓመት እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከ የተነገሩ ትንቢቶች ተፈጸሙ የተቆጠሩ ሱባኤዎች ተጠናቀቁ በቤተልሄም ይሁዳ በእኩለ ሌሊት ፀሐይ ፍንትው ብላ ወጣች የተናቁት ሰዎች ከቁጥር የማይገቡት እረኞች የፀሐይን ብርሃን ፈጥነው አዩ ‹‹የሚያከብረውና የከበረው አከበራቸው ብርሃንን ቀድሞ አሳያቸው ስብሐት ለእግዚአብሔር በአርያም ወሠላም በምድር ስምረቱ ለሰብዕ›› በማለት ሰዎችና መላዕክት በአንድ ላይ ዘመሩ፣ የብርሃን አምድ ከሰማይ እስከምድር ተተክሎ ታየ፣ ለወትሮው በሥነፍጥረት ፀሐይ የታዘዘችው በቀን እንድትሰለጥን ነበር ነገር ግን በተወደደችው ሰዓት ጨረቃና ከዋክብትን ተባበረች በእኩለ ሌሊት ለምስጋና መጣች ለመኖሯ ዋስትና ፈጣሪዋ የማይጠልቀው ፀሐይ ባልተለመደ ሁናቴ ተወስኖ አይታለችና፣ ደግሞስ ዳዊት ‹‹ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ›› ብሎ የለ ሰማያት ያለው ሰማያዊ ፍጥረታትን ሰማያትን ጨምሮ እንዲህ ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብትን ነውና የከበረውን ለማክበር መጣች አዎ! የተወደደች ዓመት ስቃይ ያበቃባት መርገም የተደመሰሰባት ፍዳ የተፋቀባት የአመጽ መዝገብ የተገለጠባት መቃብር የተዘጋባት፣ ሞት የተሻረባት ሲዖል ተዘግቶ ገነት የተከፈተባት ምርኮ የተመለሰባት እውነትም የተወደደች ሰዓት የአልቃሾች እንባ የታበሰባት የደስታ ዘመን፣







Thursday, January 2, 2014

‹‹የዓለም ብርሃን ተወለደልን››




‹‹የዓለም ብርሃን ተወለደልን››
‹‹ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃነ››
ልዑለ ቃል ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔር የራቀውን ስላቀረበለት የረቀቀውን ስላጎላለት የመሲሁን መምጣት የክርስቶስን መወለድ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት መወሰን በትንቢት መነጽር ተመልክቶ ሲናገር ‹‹ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃን ዐቢየ ወለእለሂ ይነብሩ ውስተ ጽልመት ወጽላሎት ሞት ብርሃን ሠረቀ ሎሙ›› (ኢሳ 9፡2) በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃንን አየ በሞት ጥላ በጨለማ ሀገር ለኖሩ ሰዎችም ብርሃን ወጣላቸው አለ፡፡



Friday, December 27, 2013

‹‹ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ›› (ማር 13፡15)









     ቀድሞ ከእግዚአብሔር ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጣቸውና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ጸንታ የተመሠረተችው በሰማዕታትም ደም ያሸበረቀችው ቅዱስት ቤተክርስቲያን ከተመሠረተችበት ዕለት አንስቶ በውጊያ ላይ ብትሆንም እንኳ ሁል ጊዜ ድል ታደርጋለች እንጂ ተሸንፋ አታውቅም ታላቁ የቤተ ክርስቲያን አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለቤተክርስቲያን በገለጸበት ድርሳኑ ‹‹ሰውን በትታገልና በትዋጋ ታሸንፈዋለህ ወይም ያሸንፍሃል ቤተክርስቲያንን ግን ለማሸነፍ አይቻልም፤ ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ ትዋጋለች ተሸንፋ ግን አታውቅም ዲያብሎስ ዝናሩን አራገፈ፣ ቀስቱን ጨረሰ ቤተክርስቲያንን ግን አልጎዳትም›› ብሏል፡፡
ርቱዐነ አንደበት የሆኑ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መናፍቃንን በቃልም ሆነ በጽሑፍ ሲዋጉ ኖረዋል የአበውን አሰረ ፍኖት የተከተለ ይህ ትውልድም የአባቶችን አደራ ተቀብሎ በግብር ሊመስላቸው ይገባል፡፡







Thursday, December 26, 2013

"እነሱ በእምነት የእሳትን ኃይል አጠፉ" (ዕብ 11÷33)





የጽድቅ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ለቤዛነት ቀን ለታተሙት በሜሮን ለከበሩት በልጅነት ክብር ለተጠሩት በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኙ ለዕብራውያን ሰዎች በሃይማኖት እንዲቆሙ በክርስቶስ ደም በተዋጀችው በሐዋርያትና በነቢያት መሠረትነት ላይ በታነጸችው በመጀመሪያ እምነታቸው እንዲፀኑ ሲያስተምር ይህንን ቃለ ተናግሮታል፡፡ እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው አለ ሐዋርያው፤ አዎ እምነት የማይታየው እንደሚታይ የማይቻለው እንደሚቻል የማይገፋው እንደሚገፋ የሚያስረዳ ረቂቅ መሣሪያ ነው፡፡ እምነት የረቀቀውን የሚያጎላ የተሰወረውን የሚገልጽ የራቀውን የሚያቀርብ እጉሊ መነጽር ነው፡፡

Wednesday, December 25, 2013

‹‹እነሱ በእምነት የእሳትን ኃይል አጠፉ›› ዕብ 11፡33




‹‹እነሱ በእምነት የእሳትን ኃይል አጠፉ›› ዕብ 11፡33
የጽድቅ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ለቤዛነት ቀን ለታተሙት በሜሮን ለከበሩት በልጅነት ክብር ለተጠሩት በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኙት ለዕብራውያን ሰዎች በሃይማኖት እንዲቆሙ በክርስቶስ ደም በተዋጀችው በሐዋርያትና በነቢያት መሠረትነት ላይ በታነጸችው በመጀመሪያ እምነታቸው እንዲፀኑ ሲያስተምር ይህንን ቃል ተናግሮታል፡፡ እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው አለ ሐዋርያው አዎ እምነት የማይታየው እንደሚታይ የማይቻለው እንደሚቻል የማይገፋው እንደሚገፋ የሚያስራዳ ረቂቅ መሳሪያ ነው እምነት የረቀቀውን የሚያሳይ የተሰወረውን የሚገልጽ የራቀውን የሚያቀርብ አጉሊ መነጽር ነው ለዚህም ነበር አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዌ በሚያስተምርበት ዘመን ለሚያምን ሁሉ ይቻላል ያለው ማር 9፡23


Thursday, December 19, 2013

‹‹ፆምን ቀድሱ›› (ኢዩ1፡14)









‹‹ፆምን ቀድሱ›› (ኢ 1፡14)
አምላካችን እግዚአብሔር በነቢዩ በኢዩኤል ላይ አድሮ የእግዚአብሔር በረከት ከእስራኤል ጠፍቶ በምትኩ መቅሠፍትና መዓት ረሃብና ቸነፈር በመጣባቸው ጊዜ (ኢዩ 1፡1-13) ፆምን ቀድሱ ጉባኤውንም አውጁ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ ወደ እግዚአብሔር ጩኹ (ኢዩ 1፡14) አላቸው፡፡ ለመሆኑ ፆምን መቀደስ ማለት ምን ማለት ነው? እንዴትስ ይፈጸማል?





Saturday, November 30, 2013

"ስለ ጽዮን ዝም አልልም" (ኢሳ 62:1)




ይህንን የተናገረው ልዑለ ቃል ኢሳይያስ እግዚአብሔር የራቀውን አቅርቦለት የረቀቀውን አጉልቶለት ትንቢት በሚናገርበት ዘመን ሲሆን  ጽዮን የሚለው ስም እንደአገባቡ ይፈታል ልብስ በየፈርጁ እንዲለበስ የቅዱሳት መጽሐፍት ቃልም በስልት በስልቱ ይተረጉማል መጽሓፍ ቅዱስ በትርጉሜ ስልት ሲበለት መልክ መልክ አለው አንዱ ቃል እንደያገባቡ የተለያየ ትርጓሜ ይሰጣል በመሆኑም ከላይ በርዕሳችን የተጠቀሰው የነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት ብንመለከት ቃሉ ህብርነት ያለው ሆኖ ይገኛል ጽዮን የሚለው ቃል ኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መንግስተ ሰማያት ወይም ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል ኢየሩሳሌም ቤተእስራኤል (ቤተ ያዕቆብ) ቤተ መቅደስ ተብሎ የሚፈታበት ጊዜ አለ በሌላ ሥፍራ ደግሞ የቃሉ አገባብ ኢየሩሳሌም ድንግል ማርያም ወይም መስቀል ክርስቶስ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል እንግዲህ አርዕስትን ተመልክቶ ስለምን እንደተነገረ በማስተዋል ካላዩት ካልመረመሩት በዘፈቀደ እንተርጉም ቢሉት ምስጢሩ ሊገኝ አይችልም ትርጓሜውም የተሳሳተ ይሆናል ከምሥጢር ዳህፅ(መሰናክል) ለመጠብቅ መጻሕፍት መመርመር መምህራንን ማነጋገር በጸሎት በትህትና እግዚአብሔርን ግለጽልን በማለት: ይህን ቃል የተለያየ ትርጉም እንዳለው ለማሳየት በምሳሌ እንመልከት:-