Wednesday, April 23, 2014

‹‹ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብሩ መጣች›› (ዮሐ ፳፩፣፩)

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን=>በዓቢይ ሃይል ወሥልጣን
ሮ ለሰይጣን => አግአዞ ለአዳም
ሰላም => እምእዘየሰ
ኮነ => ፍሰሃ ወሰላም።
+ ትረጉም +
--------------------
ክርስቶስ በታላቅ ሃይሉና ሥልጣኑ ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነሳ፤
ሰይጠንን አሰረው፤ አዳምን ነፃ አወጣው፤
ከእንግዲህ ወዲህ ፍሰሃ፣ ሰላም፣ ደስታ ሆነ:: አሜን! 

መግደላዊት ማርያም መጌዶል በሚባለው የትውልድ አገሯ መግደላዊት ማርያም ትባላለች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ማርያሞች ስላሉ መግደላዊት ማርያም በመባል ተለይታ ተጠቅሳለች በውስጧ ታላቅ የፍቅር ትንታግ የሚቀጣጠልባት መግደላዊት ማርያም እስከዚህ ቀን ድረስ እንዴት ታግሳ ተቀመጠች? ስንል ጌታችን የተቀበረው ዓርብ ማታ ነው ቅዳሜ እንዳትመጣ የአይሁድ ሰንበት ነው በሰንበት ከተወሰነ ኪሎ ሜትር በላይ መጓዝ ስለማይቻል በሕግ ገደብ ተይዛ ቅዳሜን ከሌሎች ቅዱሳን አንዕስት ጋር በጭንቀት አሳለፈች፡፡

Saturday, April 19, 2014

‹‹ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን መካከል ተነስቷል››

                                                                              
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ~~~~~~በዓቢይ ሃይል ወሥልጣን
ሮ ለሰይጣን ~~~~~~~ አግአዞ ለአዳም
ሰላም ~~~~~~~~ እምእዘየሰ
ኮነ ~~~~~~~ ፍሰሃ ወሰላም። አሜን!!!
+++ ትረጉም +++
ክርስቶስ በታላቅ ሃይሉና ሥልጣኑ ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነሳ፤
ሰይጠንን አሰረው፤ አዳምን ነፃ አወጣው፤
ከእንግዲህ ወዲህ ፍሰሃ፣ ሰላም፣ ደስታ ሆነ!!! አሜን!


ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ነውና መቃብር ይዞ አላስቀረውም፣ ትንሣኤ ነውና ሞት በእርሱ ላይ ስልጣን አልነበረውም በመሆኑም ከሦስት መዓልትና ሌሊት በኋላ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ሞትን ድል አድርጎ መውጊያውንም ሰብሮ በኃይሉ ተነስቷል፡፡ ‹‹ኦ መዊት አይቴ ሃሎ ቀኖትከ›› ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህ የታለ›› ተብሎ በትንቢት በተነገረው መሠረት ገዥውንና ኃያሉን አሸንፎ መውጊያውን ሰብሮ ጌታችን ተነስቷል፡፡



Thursday, April 17, 2014

‹‹ከክርስቶስ ጋር አብረን ከሞትን አብረን እንነሳለን››

‹‹ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሳኤውንም በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን›› ሮሜ 6፡5

 
 

‹‹ከክርስቶስ ጋር አብረን ከሞትን አብረን እንነሳለን››
ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተውን አዳም ለማዳን ሥጋን ተዋሕዶ እንደሚሞት የሚያውቀው ከዘመናት በፊት ነው፡፡ ቤተልሔም ከመወለዱም በፊት የሚሞትበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ፣ የሰውን ልጅ ሥጋ የለበሰውም ሞቶ ሞትን ለመግደል እንደሆነ ያውቃል የመጣበት ዓላማም ለሞመት ነው ለደቀመዛሙርቱም በተለያየ ጊዜ በምሳሌ ነገረ ሞቱንና ጊዜያቱን ነግሮአቸዋል፡፡ ‹‹በደብረታቦር ብርሃነ መለኮቱን ከገለጸበት ቀን ጀምሮ አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀመዛሙርቱ ይገልጥላቸው ነበር›› (ማቴ 16፡21) ለሚጠሉት ላሰቃዩት ለአይሁድ እንኳ ሳይቀር በምሳሌ ይነግራቸው ነበር ‹‹ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ›› አላቸው፡፡ (ዮሐ 3፡19)

Thursday, April 10, 2014

‹‹የአሸናፊነት የድል ጩኸቶች››




ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለ በኋላ በመስቀል ላይ ሆኖ የተናገራቸው 7ቱ አጻርሐ መስቀል በመባል የሚታወቁት የአሸናፊነት የድል ጩኸቶች ናቸው፡፡
1. ‹‹ኤሎኼ ኤሎኼ ኤልማስ ላማ ሰብቅታኒ››
አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ማለት ነው (ማቴ 27፡46) ይህን አሰምቶ የተናገረው በ9 ሰዓት ነው እርሱ አምላክ ሆኖ ሳለ አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ ብሎ የተናገረው ለምንድን ነው፣ ቢሉ ከሕገ-እግዚአብሔር ርቆ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የተተወ አዳምን ሥጋ ተዋሕዶ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጥ ነው፡፡
ይህንን ቃል አምላካችን ስለ ብዙ ነገር ተናግሮታል

አቤቱ እባክህ አሁን አድን-ሆሳዕና



የዛሬ 1970 ዓመት አካባቢ በነገስታቱ ዘንድ ታይቶ የማይታወቅ አዲስ ነገር በኢየሩሳሌም ታየ፣ ነገስታት በጠባቂ ወታደር ታጅበው በልዩ ፈረስ ሲሰግሩ ለንጉስነታቸው ዘውድ ሲደፋላቸው የአበባ ምንጣፍ ሊነጠፍላቸው ሲገባ አዲሱ ንጉሥ የነገስታት ንጉስ ሆኖ ሳለ በተለየ ሁኔታ ለነገስታት ክብር ባልተለመደ ዘይቤ ወደ ኢየሩሳሌም ብቅ አለ፡፡



Monday, April 7, 2014

የቀድሞው ስምዖን ዛሬ በእኔ ውስጥ እንዴት ይቀየር?

 



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ይድረስ የእግዚአብሔር መንግስት ቁልፍ በእጁ ላለ ስለ ሞተልህም ስለ ክርስቶስ ስም በሮም አደባባይ ቁልቁል ለተሰቀልህ ታማኝ ምስክር ለሆንከው ለቅዱስ ጴጥሮስ፡፡ በጌታ ፊት በምስጋና ለጸናች ነፍስህ ሰላም እላለሁ፡፡ ጴጥሮስ ሆይ ከዚህ ምድር ከተለየህባት ጊዜ ጀምሮ ስለ ነፍሴ እየተጋህ እንደሆነ እምነቴ ነው፡፡ ጴጥሮስ ሆይ የፈተናው ዓለም ሕይወት እንዴት ይዞሃል? ብትለኝ ልክ አንተ በመንፈስ ቅዱስ ታድሰህ በእምነትና በቅድስና ከመመላለስህ በፊት ያለውን የቀደመ ሕይወትህን ይመስላል እልሃለሁ፡፡

ሁለተኛው ሻማህ ካልጠፋ ሌሎቹ ይበራሉ

 

 


(አባት ልጃቸውን ሲመክሩ)
ጥንት ነው አሉ አንድ ሰው ከሰማይ ወደዚህ ና ! ተመልከትም የሚል እንደ ውሃ የሚፈስ ድምጽ ሰማ፡፡ ሄደ! አየም እነሆ በአንድ እጅግ ጠባብ በሆነ መንገድ ላይ ሶስት ሻማዎች ይበሩ ነበር፡፡ የሚገርመው የመጀመሪያው ሻማ እምነት ሁለተኛው ተስፋ ሶስተኛውም ፍቅር የሚባሉ ስሞች ነበሯቸው፡፡