Sunday, September 28, 2014

“ዕፀ መስቀሉ ከየት መጣ”


“ዕፀ መስቀሉ የት መጣ”

የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔ ኃይል ነውና እንደተባለው በቆሮ 1÷18/ ክርስቲያኖች ኃይላችን፣ መመኪያችን፣ ነፍሳችን መዳኛና የምንጸናበት መስቀል እናምናለን፡፡ ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “እግሮቼ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን” እንዳለም /መዝ 131÷7/ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ውሎ እኛ ለሠራነው ኃጢአት ካሣ እንደሆነ እያሰብን እንሰግድለታለን፡፡ በልባችን፣ በሰውነታችንና በቤታችን እንስለዋለን፡፡ በአባቶቻችን እንባረክበታለን፡፡ እንደትምህርታችን የድኅነታችን ብርሃን የበራበት ይህ መስቀል የእንጨት ነው፡፡ እንጨት ከመሆኑ ጋርም አንድም ለመስቀሉ ካላቸው ፍቅር ወይም ታሪክን በተረት ቀርፀው ከማስቀረት ልማዳቸው የተነሣ ይህ መስቀል ከየት መጣ? ለሚለው አባቶች የሚተርኩት አንድ ታሪክ አለ፡፡ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

Thursday, September 25, 2014

ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠኃቸው

                            


ከላይ በርእስነት ያነሣነውን ኃይለቃል በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ነቢዩ ዳዊት ተናግሮታል፡፡ አባቶች ነገሮች ከመፈጸማቸው በፊት አስቀድሞ ትንቢት አላቸው ሲሉ ትንቢት ይቀድሞ ለነገር" እንዲሉ፡፡ (መዝ. ፶፱÷፬)

የእግዚአብሔር ወዳጅ፣ መዝሙረኛው ዳዊት በትንቢት መነጽርነት የተረዳው ምስጢር ቢኖር መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተሰቀለበት ክቡር መስቀል የሚያድን፣ ከሰይጣን የሚታደግ፣ ከክርስቲያኖች ጋሻ ሆኖ የተሰጠበ በረከት መሆኑን ነው፡፡ ነቢዩ የመስቀሉን አዳንነት የተገነዘበው በተሰጠው የትንቢት ጸጋ ነው፡፡ በቀራንዮ መሥዋዕት የሆነው ቸሩ አምላክ ክቡር መስቀሉን ሊቀድሰው ስለፈለገ ቅዱስ ሥጋውን ቆረሰበት ክቡር ደሙን አፈሰሰበት፡፡

Wednesday, September 10, 2014

‹‹አዲስ ልብንና አዲስ መንፈስን ለእናንተ አድርጉ›› (ሕዝ 18፡31)



መልካም አዲስ ዓመት

ኃይለ ቃሉን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሚመክርበት ዘመን ከአበይት ነቢያት አንዱ በሆነው በነቢዩ በሕዝቅኤል በኩል ስለብዙ ነገር ተናግሮታል፡፡ ለጊዜው ለእስራኤል ዘሥጋ ይነገር እንጂ ፍጻሜው ግን እኛም እንማርበት ዘንድ ተመዝግቦልናል፡፡ በመሆኑም የዚህ ጽሑፍ ዋና መልዕክትና መሠረታዊ ዓላማ በምድራዊው የኮንትራት ኑሯችን በዘመን ተሰፍሮና ተወስኖ በተሰጠን ዕድሜ በተለይም በቀሪ ጊዜያችን አሮጌውንና የዛገውን ልብ አውጥተን አዲስ ልብን ገንዘብ እንድናደርግና በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ማሳሳብ ነው፡፡

Saturday, June 28, 2014

‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም›› (ማቴ16፡18)




ይህንን ኀይለ ቃል ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊሊጶስ ቂሳሪያ ለሊቀ ሐዋርያት ለቅዱስ ጴጥሮስ ተናግሮታል፡፡ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወለድ በተለየ አካሉ ጸጋና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ፡፡ (ዮሐ 1፡14)
ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም ነፍስና ሥጋን ነስቶ በፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆነ ‹‹ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ህፃን ሆኗልና፣ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘላለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ ኀጢዓትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት ይህን ወድዷልና፡፡ ክብሩ ተለይቶት የነበረ ሥጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው የጸጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ሥጋንም የባሕርይ ገዥ ሊያደርገው ወደደ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ››
(ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 220)



Monday, June 16, 2014

ክርስቲያናዊ ቤተሰብእ



 

 

ቤተሰብእ ማለት በቅዱስ ጋብቻ አማካይነት በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች (ወንድና ሴት) ግንኙነት የሚጀመረውና ቁጥራቸው ይነስም ይብዛም የሚወለዱትን ልጆች ጨምሮ በጋራ የሚመሰረተው ማኅበር ነው፡፡
እንዲህ ዓይነት ቤተሰብእ የሚመሰረተው በቅዱስ ጋብቻ በሥጋውና ደሙ አማካኝነት ነው  ይህም የጋብቻ ቡራኬና ጸሎት የሚፈጸመው አምላካችን እግዚአብሔር በሥነ-ፍጥረት ጊዜ ሰው እንዲበዛ ቅዱስ ፈቃዱ ስለሆነ ለመባዛቱም ምክንያት የሚሆነው የወንድና የሴት ግንኙነት ሲኖር መሆኑን በማረጋገጥ አዳምና ሔዋንን ፈጥሮ እንዲህ ሲል የፈጸመውን የመጀመሪያ የተክሊል ጸሎትና ቡራኬ መነሻ በማድረግ ነው ‹‹እግዚአብሔርም ሰውን ፈጠረ በመልኩ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠራቸው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው እግዚአብሔርም አላቸው ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት የባሕሩንም አሣ የሰማዩንም ወፍ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሰውን እንሰሳ ሁሉ ግዙ›› ዘፍ 1፡27



Tuesday, June 3, 2014

ክርስቲያናዊ ሥነምግባር



ክርስቲያናዊ ሥነምግባር
አጠቃላይ ፈተና

‹‹ንዌጥን በረድኤተ እግዚአብሔር››
1.  ከአስርቱ ትዕዛዛት ይመደባል
ሀ/ ህገ-ልቡና
ለ/ አትስረቅ
ሐ/ የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው
መ/ ሁሉም
2.  እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ስላረፈ ይህንን ቀን ቀደሰው………………….
ሀ/ ቀዳሚውን ሰንበት
ለ/ የመጀመሪያውን ቀን
ሐ/ እሁድን ዕለት
መ/ ሁሉም


ትምህርተ ሃይማኖት

 



ለቀዳማይ ክፍል የተዘጋጀ
አጠቃላይ ፈተና
‹‹ንዌጥን በረድኤተ እግዚአብሔር››
1.  እግዚአብሔር የሚለው መጠሪያ ስም
ሀ/ የተጸውኦ ስም ነው              ሐ/ የተቀበአ ስም ነው
ለ/ የግብር ስም ነው                 መ/ የባሕርይ ስም ነው
2.  ሀልዎተ እግዚአብሔር ……………………………. የምንማርበት የትምህርት ክፍል ነው
ሀ/ የመላእክትን አኗኗር              ሐ/ የእግዚአብሔር አኗኗር
ለ/ የሰውን ህልውና                 መ/ መልስ የለም