Monday, September 21, 2015

ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ


†††ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ†††
አንድ አምላክ በሚሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምነንና ጸንተን ንጉሠ ሰማይ ወምድር ኢየሱስ ክርስቶስ በአማላጅነቷ ይቅርታን የምታሰጥ ለመሆኗ ቃል ኪዳን የገባላትን የክርስቶስ ሠምራን ገድል እንጽፋለ...ን፡፡ የእናታችን የክርስቶስ ሠምራ የትውልድ ሀገሯ ሸዋ ቡልጋ ልዩ ስሙ ቅዱስ ጌየ የተባለ ቦታ ነው፡፡ የአባቷ ስም ደረሳኒ የእናቷ ስም ዕሌኒ ይባላል፡፡ እኒህም ቅዱሳን ሰዎች ደጋጎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ በሐይማኖት የጸኑ በበጎም ምግባር የከበሩ ነበሩ፡፡ ይህችንም ከእግዚአብሔር የተመረጠችና የተመሰገነች ልጅ ከወለዱ በኋላ በክብርና በስርዓት አሳድገው የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ትእዛዝ እያስጠኑ ብሉይ ከሐዲስ አስተማሯት፡፡ከዚያም የመኳንንት የመሳፍንት ልጅ ናትና ለኢየሱስ ሞዓ ልጅ ሠምረ ጊዮርጊስ ለሚባል ሰው አጋቧት፤ እሷም ዐስር ወንዶች ሁለት ሴቶች ልጆች ወለደች እኒያንም ልጆቿን በክብር በስርዓት አሳድጋ አስተማረቻቸው፡፡ በዘመኑ ዐጼ ገብረ መስቀል የሚባል ደግ ንጉሥ ነበረና ደግነቷን ዐይቶ ዝናዋን ሰምቶ አትርሽኝ ብሎ ፪፻፸፪ አገልጋይ ላከላት እርሷም ይህማ ከንቱ ውዳሴ ሊሆንብኝ አይደለምን መጽሐፍ ቢሆን ይነበብበት ይጸለይበት ገንዘብ ቢሆን ይመጸወት ነበር ብላ ወደ እግዚአብሔር አመለከተች፡፡

ዕረፍቱ ለሊቀ ነቢያት ሙሴ


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
መስከረም 8-የሊቀ ነቢያት ሙሴ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም 40 ዓመት በሆነው ጊዜ አንዱ ግብጻዊ ዕብራዊውን ሲገድለው አይቶት ለወገኑ ተበቅሎ ግብጻዊውን ገድሎ ወደ ምድያም አገር ማለትም ወደ ኢት...ዮጵያ መጥቶ የካህኑን የዮቶርን ልጅ አግብቶ ሁለት ልጆችን ወለዶ በኢትዮጵያ 40 ዓመት ከኖረ በኃላ የዮቶርን በጎች እየተበቀ ሳለ እግዚአብሔር በቁጥቋጦ ውስጥ በታላቅ ራእይ ተገልጦለት እስራኤልን ከግብጽ እንዲያወጣ ነግሮት ሄዶ በተአምራት 10 መቅሰፍታት አምጥቶ ነጻ ያወጣቸው ነው፡፡
ዳግመኛም ዛሬ የመጥምቁ ዮሐንስ አባት የበራክዩ ልጅ ካህኑ ዘካርያስ በሰማዕትነት ያረፈበት ዕለት ነው፡፡
"ክርስቶስን አምላክ አትበል" በማለት አንድ ከሃዲ መኮንን በእጅጉ ካሠቃየው በኋላ አንገቱን በሰይፍ የቆረጠው የሰማዕቱ የቅዱስ ሉክዮስም ዕረፍቱ መስከረም 8 ነው፡፡

Tuesday, June 23, 2015

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ



ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ

በቤዛ ብዙኀን ቅድስት ኪዳነምህረት ካቴድራል (ጎፋ ካምፕ)
ሰኔ 18, 2007 ዓ.ም
በደብረ ከዋክብት ቅዱስ ገብረክርስቶስና አብነአረጋዊ ቤተክርስቲያን
ሰኔ 21, 2007 ዓ.ም
በደብረ ቢታንያ ቅድስ ተክለሀይማኖት ቤተክርስቲያን
ሰኔ 27, 2007 ዓ.ም


ተጋባዥ መምህር
መምህር ቸርነት ይግረም

Tuesday, June 16, 2015

‹‹መንፈስን ሁሉ አትመኑ››




‹‹መንፈስን ሁሉ አትመኑ››
ቅዱስ ዮሐንስ በመልዕክቱ ‹‹አኃዊነ ለኩላ መንፈስ ኢትአመኑ አላ አመክርዋ ለመንፈስ ለእመ እምኀበ እግዚአብሔር ይእቲ፣ ወንድሞች ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ለእግዚአብሔር ሆነው እንደሆነ መርምሩ›› (1ዮሐ 4፡1) ይለናል፡፡

Friday, April 24, 2015

ሰማዕትም ሆኑ ማዕተብን አስረው






በዚህ ሳምንት እንኳን
እባካችሁ ተውን
የኢትዮጵያዊነት ክብራችን ተነክቶ
የሥላሴ ህንፃ ፈርሶ ተንኮታክቶ
እምነት በሌላቸው በአህዛብ ተዋርደን
ተንቀናልና መሳለቂያ ሆነን

አስብ የሆነብን





ጊዜ የሰጠው ቅል ዓለቱን ሠበረ
የዓለቱን ልጆች እጅና እግር አሰረ
ርስታችን ሁሉ ገብቶ መዘበረ
ኀያላንን ገድሎ በይፋ ፎከረ