Monday, March 24, 2014
‹‹የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱ ምንድን ነው?›› (ማቴ 24፡3)
ይህንን ጥያቄ
የጠየቁት ለጊዜው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዋለበት የዋሉት ካደረበት ያደሩት የእጁን ታምራት ያዩት የቃሉን ትምህርት የሰሙት ቅዱሳን
ሐዋርያት ሲሆኑ ከደብረዘይት አቀበት ቁልቁል በማለዳ ፀሐይ የሚያብረቀርቀውን የኢየሩሳሌምን ከተማና በውበቱ እጅግ ያማረውን የዘሩባቤልን
ሕንፃ ቤተመቅደሱን በመልካም ድንጋይና በተሰጠው ሽልማት እንዳጌጠ ሲነጋገሩ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህ የምታዩት ሁሉ ድንጋይ በድንጋይ
ላይ ሳይፈርስ በዚህ የማይቀርበት ዘመን ይመጣል ባላቸው ጊዜ ነበር ‹‹መምህር ሆይ ይህ ሁሉ መቼ ይሆናል?›› ይህስ ይሆን
ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድን ነው? ያሉት፡፡ (ማር 13፡3)
Tuesday, March 18, 2014
Saturday, March 15, 2014
‹‹ለክፉው ዘመን የማምለጫ መርከብ››
ንዋየ ኅሩይ ቅዱስ ጳውሎስ ዘመኑን ዋጁ ይላል በተለይም ክርስቲያኖች የዓለም
ብርሃን የዓለም ጨው ተብለናልና በውጭ ባሉት ዘንድ በጥበብ እየተመላለስን ዘመኑን ልንዋጅ ይገባል፡፡ ያለንበት ዘመን ደግሞ እውነት
በሐሰት የተዋጠበት ግፈኞች ደም አፍሳሾች የበዙበት ፍርድ የተጓደለበት ግብረ ሰዶማዊነት በዓለም ላይ ያለ ዕፍረት የሚሠራበት፣ ትዕግስት
ትህትና፣ ይቅርታ፣ ከሰዎች ጠፍቶ ትዕቢት፣ ጭካኔ ፣ ቂም በቀል የነገሠበት ክፉ ዘመን ነው ‹‹ለዚህም ነው ነቢየ እግዚአብሔር ሚክያስ
በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ ከዚያም አንገታችሁን አታነሱም ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም›› (ሚክ 2፡3) በማለት
ስለዚህ ጉቦኛ፣ ግፈኛ፣ አመንዝራ አላስተዋይ ትውልድ ይናገራል፣
Friday, March 14, 2014
Thursday, March 13, 2014
የኋላውን እየተውን ወደፊት መጓዝ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
ልጄ ሆይ እነሆ በመንፈሳዊ ሕይወትህ ወደ ፊት እንዳትጓዝ ተብትቦ የያዘህ ብዙ
ያለፈ የትዝታ ገመዶች ይኖራሉ፡፡ እነዚህም በጎም ሆነ ክፉ ትዝታዎች ሊሆኑ ይችላሉ አስተውል ተደርገው ወይም ሆነው ያለፉ ናቸው፡፡
ነገር ግን በልብህ ውስጥ ስላሉ ስትተኛ ስትነሳም ስትቀመጥም ስትሄድም ከአንተ ጋር ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዘወትርም ይታሰቡሃል ታዲያ
ያለፈውን በጎም ይሁን ክፉ ስራህን እያሰብክ ባለፈው ታሪክህ ተዘፍቀህ የምትኖር ከሆነ ወደ ፊት እንዴት መጓዝ ይሆንልሃል?
Monday, March 10, 2014
Subscribe to:
Posts (Atom)






