Tuesday, September 19, 2017

መጻሕፍት የጥበብ ምንጮች ናቸው።

መጻሕፍት የጥበብ ምንጮች ናቸው።
======================


ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ዶግማና ቀኖና በጠበቀ መልኩ ለመምህራንና ለካህናት የጉባኤ ማስተማሪያ ለሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ማሰልጠኛ ለግቢ ተማሪዎች ማስተማሪያ መጽሐፍ/ Text book /ይሆን ዘንድ የተዘጋጀ ነው።
በተለይም በዚህ በአለንበት ዘመን ሐራጥቃ መናፍቃን የቤተክርስቲያኗን ቀኖና እና አስተምህሮ በተቃረነ መልኩ ብዙ ጥፋት እያጠፉ ባለበት አስቸጋሪ ወቅት የቤተክርስቲያንን መሠረታዊ የሆነ አስተምህሮ መጻሕፍትን አጣቅሶ ሊውቃንትን አማክሮ በጽሑፍ አዘጋጅቶ ለትውልድ ማስተላለፍ ወሳኝ ሆኖ በመገኘቱ ትውፊትን የመጠበቅና ለተተኪው ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነቴን ለመወጣት ይህን መጽሐፍ አዘጋጅቻለሁ።
በዚህ መጽሐፍ ላይ የተካተቱ በርካታ መልዕክቶች ከተለያዩ መጻሕፍቶች መምህራን የተውጣጡ በዓይነታቸውና በይዘታቸው... አዲስ ያልሆኑ ነገር ግን በአቀራረባቸው በቂ ግንዛቤ እንዲያስጨብጡ ተደርገው ተዘጋጅተዋል።
የቤተክርስቲያናችን ሥርዓትና ደንብ ለመጠበቅ ሲባል አንዳዶቹ መልዕክቶችም ቅርጻቸውን ና ይዘታቸውን ሳይለቁ እንዳለ በዚህ መጽሐፍ ላይ ተመዝግበዋል፤ነገር ግን በዋቢ ክፍል ውስጥ በተገቢው መልኩ ተጣቅሰዋል።
የአዘጋጁም ሆነ የጸሐፊው መልዕክት ለወደፊት ለተሻለ አገልግሎት ይሆን ዘንድ የቤተክርስቲያን የዶግማንና ቀኖና በጠበቀ መልኩ ከዚህ በተሻለ ይዘጋጅ ዘንድ የአንባቢያን አስተያየት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል እላለሁ።

1 comment:

  1. ሰላመ እግዚኣብሔር ለእናንተ ይሁን እነዚ ከላይ ያሉ መጻሕፍት ነው ማግኘት የምችለው?

    ReplyDelete