ክርስቲያናዊ ሕይወት

 


**++ በዘፈንም የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል**++(1ኛ ጴጥ 4:3)










የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም**++ በዘፈንም**++ ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:3የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥
መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥
መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። (ወደ ገላትያ ሰዎች 5:19)


... ... የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
... 1) zefen kidusanin yasadede seif new
ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤
ዮሐንስ። እርስዋ ለአንተ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደም ይለው ነበርና።

ሊገድለውም ወዶ ሳለ፥ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስለ አዩት ፈራቸው።
ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው **ዘፈነች **ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤
ስለዚህም የምትለምነውን ሁሉ እንዲሰጣት በመሐላ ተስፋ አደረገላት።
እርስዋም በእናትዋ ተመክራ። የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በዚህ በወጭት ስጠኝ አለችው።

ንጉሡም አዘነ፥ ነገር ግን ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ተቀምጠው ስላሉት ሰዎች እንዲሰጡአት አዘዘ፤
ልኮም የዮሐንስን ራስ በወህኒ አስቆረጠው።
ራሱንም በወጭት አምጥተው ለብላቴናይቱ ሰጡአት፥ ወደ እናትዋም ወሰደችው።
ማቴ14:2-10 azimariwochim zefagnoch zefnew yemiyazefinu hatiat seritew hatiat yemiyaseru menigiste semayat ayigebumወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ**ዘፋኞች፥**

ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6-11)
"" **ዘፋኞች፥**ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።(የዮሐንስ ራእይ22:15)
@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@@


 
ሰዎች ንስሐ ላለመግባት ከሚያቀርቧቸው ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ እና መፍትሄዎቻቸው

1- እኔ የሠራሁት ኃጢአት ሰው ሁሉ የሚሠራውን ነው እንጂ የተለየ አይደለም፡፡ 

አንዳንድ ሰዎች እነርሱ የሠሩት ብዙ ሰዎች የሚፈጽሙትን ኃጢአት ከሆነ በግል ልንጠየቅበት አይገባም በተናጠልም ንስሐ ልንገባበት አይገባም ብለው ያስባሉ፡፡ ለእነርሱ ኃጢአት መሥራት የኅብረተሰቡ ኃጢአትን መፈጸም ምክንያት እንደሆናቸው ይቆጥራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ኃጢአት ኃጢአት ነውና የፈጸመው ሰው ይጠየቅበታል፡፡ ስለዚህ ከኃጢአት መለየት አንጂ ሰው ኃጢአት ሠርቷል ብለን መልሰን እዚያ ውስጥ አንዘፈቅም፡፡
ለምሳሌ፡- በኖህ ዘመን ሰው ሁሉ በኃጢአት ውስጥ በነበረበት ጊዜ ኖህ በእግዚአብሔር ዘንድ ጻድቅ ነበር ዘፍ. 6፥5 ቅዱስ ጳውሎስም ይህን አለም አትምሰሉ ብሏል፡፡ ሮሜ. 12፥2
መላው የግብፅ ሕዝብ ጣኦት ሲያመልክ ጻድቁ ዮሴፍ የሚያመልከው እግዚአብሔርን ነበር፡፡
በባቢሎን የተማረኩት ሠልስቱ ደቂቅና ዳንኤል እንዲሁ እግዚአብሔርን ያመልኩ ነበር እንጂ በጣኦት አምልኮ ከባቢሎናውያን ጋር አልተባበሩም፡፡ ዳን. 2፥8
ማንኛውም ክርስቲያን በመንፈሳዊ ሕይወቱ የአለማውያንን ኑሮ ለመለወጥ ባይቻለውም እንኳ አለምንና አለማውያንን ከመምሰል ከእነርሱም ጋር ከመቀላቀል መጠንቀቅና መራቅ ይገባዋል፡፡
2- ውጫዊ ፈተና መደራረብ ምክንያት አድርገው ያቀርባሉ፡፡
ጠንካራና ልቦና ያለው ሰው በኃጢአት ለመውደቅ የፈተናን ብዛት ምክንያት አያደርግም፡፡ የውጭ ተጽዕኖን ለኃጢአቱ ምክንያት አድርጎ የሚያቀርብ ሰው ለትዕዛዛተ እግዚአብሔር ከበሬታ ለእግዚአብሔርም ፍቅር የሌለው ነው፡፡
ለምሳሌ፡- ዮሴፍ ኃጢአት ለመሥራት በቂ ምክንያት ነበረው፡፡ ያም ምክንያት ባርያ ታዛዥ ባይተዋር ስለሆንኩ ኃጢአትን ሠራሁ ለማለት በቂ ምክንያት ነበረው፡፡ እርሱ ግን እንዴት አድርጌ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢያትን አደርጋለሁ አለ፡፡
ሳኦል ያለምንም በደል ዳዊትን ባሳደደው ጊዜ እግዚአብሔር ሳኦልን በዳዊት እጅ አሳልፎ ሰጠው፡፡ ዳዊትም ሳኦልን ለመበቀል በቂ ምክንያት ነበረው ያም ምክንያት
 

  • ኃጢአተኛ ስለሆነ
  • ክፉ ስለሆነ
  • እግዚአብሔርን ንቆ ከሥልጣን ስለ አወረደው
  • ለዳዊት ጠላት ስለሆነ ወዘተ… 1ሳሙ. 16፥14
ዳዊትም እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን አላነሳም አለ፡፡
በአጠቃላይ ማንኛውንም ኃጢአት ለመሥራት የእግዚአብሔር ፍቅር በልቡ የታተመ ሰው ምክንያት አይደረድርም፡፡
3- እኔ ደካማ ነኝ የእግዚአብሔር ትዕዛዛትም ከባድና አስቸጋሪ ናቸው ምን ላድርግ? ይላሉ፡፡
የእግዚአብሔር ዕርዳታ የረሳን እንደሆነ በእርግጥ ደካሞች ነን እግዚአብሔርን የሚያመልክ ሰው ብቻውን አይደለምና፡፡ ሰው በባህሪው ደካማ ቢሆንም በእግዚአብሔር እርዳታ የማይቻለው ነገር የለም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ›› ፊል. 4፥13 እንዳለ:: ዳዊት እኔ ደካማ ነኝ እግዚአብሔር ግን ይረዳኛል ባይል ኖሮ ጎልያድን ባልተዋጋም ነበር፡፡ የእርሱ የባህሪ ደካማነት በእግዚአብሔር ትዕዛዝና በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ከሚሠራው ሥራ ሊያስቀረው አልቻለም ይህም ሲባል፡-
1ኛ. ዳዊት በመጀመሪያ ለውጊያ ስላልተመለመለ ሊመለስ ይችል ነበር፡፡
2ኛ. ጎልያድ ግዙፍ ተዋጊና ባለ ብዙ መሣሪየ  በመሆኑ ሰው ሁሉ ስሚፈራው ዳዊትም ሊፈራው ይችል ነበር፡፡
3ኛ. ዳዊትን ማንም እንዲዋጋ አልጠየቀውም ነበር፡፡
4ኛ. የጦር መሪዎቹ ሁሉ ሳኦልን ጨምሮ ጎልያድን ፈርተውት ነበር ስለዚህ ዳዊት እኔ ትንሽና ደካማ ነኝ ለማለት በቂ ምክንያት ነበረው፡፡ ዳዊት ግን በእምነት ለድል በቃ፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን ልንፈጽመው የማንችለውን እንድንፈጽም አያዝዘንምና የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ከባድና አስቸጋሪ እንደሆነ ማሰብ የለብንም፡፡ ፈጣሪያችን ያዝዘናል የምንፈጽምበትንም ኃይል ይሰጠናል፡፡ ከትዕዛዙም ጋር ደግሞ ፀጋው አለ፡፡ መንፈስ ቅዱስም በእኛ አድሮ ተግባሩን ለመፈጸም ያበረታናል፡፡ ያለበለዚያ ሊውጠን እንደሚያገሳ አንበሳ ሆኖ የሚመጣውን ሰይጣን መቋቋም ባልተቻለም ነበር፡፡ 1ጴጥ. 5፥8
በመጨረሻ ነፍስን በመንከባከብና በመጠበቅ የሚከተሉትን ትዕዛዛት ዘወትር ማስታወስ ይገባል፡፡
            1ኛ. በመንፈስ ብንመላለስ የሥጋን ምኞት አንፈጽምም፡፡ ገላ. 5፥16
            2ኛ. መንፈስ የሞላብን መንፈስ ቅዱስ ያደረብን እንሁን፡፡ ኤፌ. 5፥18
            3ኛ. በመንፈስ የምንቃጠል እንሁን ሮሜ. 12፥11
በዚህም እግዚአብሔርን በመንፈስ እናመልከዋለን ፊል. 3፥3 በመንፈስ እንጸልያለን በመንፈስም እንዘምራለን 1ቆሮ. 14፥15 የመንፈስ ፍሬዎችም እናፈራለን ገላ. 5፥22
ስለዚህ ከንስሐ በኋላ ከእግዚአብሔር ፍቅር እንዳንለይ ከእቅፉም እንዳንወጣ የናቅናት ዓለምና የተውነው ኃጢአታችን እንዳይናፍቀን ወደ ነበርንበትም እንዳንመለስ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የገባንለትን ቃል ኪዳን እንዳናፈርስ በእጅጉ ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ኃጢአትንም እንድንጠላው ተግተን መጸለይ ንሰሐ አባታችንንም በየቀኑ እያገኘን በመንፈሳዊ ሕይወት የምናድግ መሆን ይገባናል፡፡
ሕይወታችን በእግዚአብሔር ተቃኝቶ የስሙ ቀዳሽ የክብሩ ወራሽ እንዲያደርገን የእግዚአብሔር አብ ጸጋ  የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን ተራዳዒነት አይለየን አሜን፡፡

No comments:

Post a Comment