Monday, February 3, 2014

ፈራጅ ወይስ አማላጅ?

ክፍል 2
 ‹‹የሉተራውያን ስህተት በሊቃውንት አስተምህሮ ሲገለጥ ሲጋለጥ››


ባለፈው ዕትማችን ሉተራውያን በጽሑፎቻቸውና በቃላቸው ከልባቸው አፍልቀው ‹‹ኢየሱስ በሰማይ ሆኖ ይጸልይልናል፣ አማላጃችን ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል›› ይላሉ ሃሣባቸው በአጭሩ ሲገለጥ ኢየሱስ አማላጃችን ነው ለማለት መሆኑ ይታወቃል እንግዲህ በቅዱስ መጽሐፉም የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር አባል በመሆናቸው የራሳቸውን ስሜትና የፈጠራ አስተያየት በመጨመር ኢየሱስ አማላጅ፣ ጠበቃ ነው የሚሉ ጽሑፎችን አስገብተው ይገኛሉ ካቶሊኮች የተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን መጻሕፍት በኑፋቄ መርዝ ትምህርታቸው ለመበከል እንደሞከሩ፣ ሉተራውያንም ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት፣ ፈጣሪነት ባለመረዳት ኢየሱስ አማላጃችን ነው በማለት ጌታችን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን ትክክልነትና አምላክነት ይክዳሉ፡፡ በተለያየ ጊዜ ባሳተሟቸው በራሪ ወረቀቶችና መጻሕፍት ስህተት እየጻፉ ይገኛሉ ከነዚህም መካከል የተወሰኑትን ጠቅሰን በቤክርስቲያናችን ሊቃውንት አስተምህሮ ሲገለጥ ምን እንደሚመስል አይተናል፣ ዛሬም ቀጣዩን እነሆ፡-




1.   ‹‹እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል››
‹‹የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው?  የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፣ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው›› (ሮሜ 8፡33-34)
ከዚህ በላይ የተገለጸውን ኃይለ ቃል አንባቢ ሁሉ ቢያስተውለው፤ እርስ በእርሱ የማይስማማ ንባብ መሆኑን ለመረዳት አያዳግትም ቁጥር ሠላሣ ሦስት ላይ ‹‹እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል›› ይላል ይህ ኃይለ ቃልም የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስን አምላክነት የሚያመለክት መሆኑን ማንም ሰው እንደሚረዳው እናምናለን እግዚአብሔር የሚለው ሦስቱም የሚጠሩበት ስም ነውና፡፡ ከዚያም በማያያዝ ‹‹የሚያፀድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው?›› ይላል ይህም ኃይለ ቃል የሚገልጸው በገነትና በሲኦል፣ በገሃነምና በመንግስተሰማያት ሥልጣን ያላቸው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ነው በሥልጣን አንድ ናቸውና፡፡
ነገር ግን ‹‹የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞም ስለእኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው›› በማለቱ ከላይ የተገለጸው የሦስቱን አካላት የስልጣን ትክክልነትና አንድነት እንደሚያዛባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከአምላክነት ዝቅ አድርጎ ከቅዱሳን እንደ አንዱ እንደሚያደርገው ግልጽ ነው
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ግን የቅዱሳንን ምልጃ ተቀብሎ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚፈርድ እንጂ አማላጅ ተብሎ ሊጠራ አይገባውም፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ‹‹አብ ሙታንን እንደሚያስነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም›› የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይለ ቃል መመልከቱ በቂ ይሆናል፡፡ (ዮሐ 5፡22-23)
ስለዚህ ከላይ መናፍቃን ያዛቡት ጥቅስ ‹‹የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞም ስለ እኛ የሚፈርደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው›› ተብሎ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡
አዲስ ኪዳን ተብሎ 1946 ዓ.ም በአፄ ኃይለስላሴ መልካም ፈቃድ የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ፣ በአብዛኛዎቻችን እጅ ያለውን የተዛባውን የሮሜን 8፡34 ኃይለ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው አስተካክሎ ያስነብበናል ንባቡ የበለጠ ግልፅ ይሆንልን ዘንድ ርዕሱንና ኅዳጉን እንመልከት፡፡




እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች የሚነቅፋቸው ማነው? እርሱ ካጸደቀ ማነው የሚኮንን? ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ በአብ ቀኝ ተቀምል ስለ እኛ ይፈርዳል (ሮሜ 8፡33-35)  ይላል፡፡
የሊቃውንት ጉባኤ ባሳተመው ግዕዝና አማርኛ ወይም ነጠላ ትርጉም አዲስ ኪዳን እንደሚከተለው ተገልል፡፡
‹‹ወመኑ ውእቱ እንከ ዘይትዋቀሦሙ ለኅሩያነ እግዚአብሔር ለእመ ለሊሁ ያጸድቅ፡፡ ወመኑ ዘይኬንን ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ወተንስአ እምውታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር ወይትዋቀሥ በእንቲአነ›› (ሮሜ 8፡33-34) ትርጉሙም ‹‹እርሱ ካጸደቀ እንግዲህ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች የሚቃወማቸው ማነው? የሚፈርድ ማን ነው? ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ፣ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምል፣ ስለ እኛም ይፈርዳል››
እንግዲህ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያላት አስተያየት ከሉተራውያን፣ ከካቶሊክ፣ ከመሐመዳውያን የሚለይ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ፣ ወይም አማላጅ ወይም ከነቢያት እንደ አንዱ አይደለም፡፡
ነገር ግን ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ በተዋሕዶ የከበረ የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ ፈራጅና ገዥ የነቢያት ፈጣሪና አምላክ ነው፡፡


በምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርታችን ግልፅ ሆኖ ተቀምጧል ምስጢረ ሥጋዌ አምላክ ሰው መሆኑን የምንረዳበት ምሥጢር ነው በተድላ ገነት ብርሃን ልብሰን ተጎናፅፎ የነበረው የሰው ልጅ የፈጣሪውን ትዕዛዝ በጣሰ ጊዜ ከምድረ ገነት ተባረረ፡፡ ቸር አምላክም የሰውን ልጅ ሊተወው አልወደደምና ከሰማየ ሰማያት መጣ ከቅድስት ድንግል ማርያምም ተወለደ ቃል ሥጋ ሆነ፡፡
ቃል ስጋ የሆነው እንዴት ነበር?
ቃል ሥጋ ሆነ በእኛም አደረ ክብሩንም አየነው ይላል መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ወደ እመቤታችን ተልኮ መጣ፡፡ ትጸንሻለሽ ወልድንም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ እርሱም ገናና አምላክ ነው የልዑል ባሕርይ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል አላትም፡፡
እመቤታችንም የገናናው መልአክ ሠላምታና የምስራች ኃይለ ቃል ቢከብዳት ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም በማለት መልአኩ ሲነግራት የእግዚአብሔር ባሪያ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ ብላ የእግዚአብሔርን መልዕክት ተቀበለች መድኃኒታችንም ቃሏን ምክንያት አድርጎ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በማህፀኗ አደረ፡፡ መዋዕለ ሕፃናትን ሳያፋልስ በመጠነ ሕፃናት የእለት ጽንስ ሆነ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሆነ ከቅድስት እናቱም ተወለደ ወደ ምድረ ግብፅ ከእናቱ ጋር ከተሰደደ በኋላ እስከ 30 ዓመቱ ለድንግል እናቱ እየታዘዘ አደገ፡፡ በ30 ዓመቱ በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠመቀ ራሱንም ስለ እኛ መስዋዕት አድርጎ አቀረበ በፅንስ የተጀመረው ዓለምን የማዳን ሥራ በዕለተ አርብ ሊፈጸም ይገባ ነበርና ጌታችን በስቅለቱ ዕለት እንዲህ ሲል ተናገረ ‹‹ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ተጠማሁ አለ በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ መልተው ወደ አፉ አቀረቡለት ኢየሱስም ከተቀበለ በኋላ ተፈጸመ አለ›› (ዮሐ 19፡28-29) ይላል፡፡
መድኃኒታችን በመጨረሻ ፤ ተፈፀመ፤ በማለት የተናገረው ኅይለ ቃል ዓለምን ለማዳን ስለመጣበት ቤዛነት የሚያመለክት ኅይለ ቃል መሆኑ ግልጽ ይሆን ዘንድ ይገባል፡፡
ስለ ዓለም ድኅነት አንድ ጊዜ የተወደደ መስዋዕት ሆኖ ራሱን ያቀረበው ወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ እንዲሁም ከራሱ ጋር አንድ ጊዜ ስላስታረቀንና ስለታረቀን የማዳን ሥራውን በዕለተ አርብ እንደፈጸመልን ሊታወቅ ይገባል ከዚህ ውጪ ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤ በኋላ በአባቱ ቀኝ ቆሞ ይማልድልናል ማለት ስህተት ብቻ ሳይሆን ወደ ሲኦል የሚያወርድ ክህደት መሆኑን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ታምናለች የካዱም በንስሐ እንዲመለሱ ታስጠነቅቃለች፡፡
የሚፈረድ ማነው? ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል ስለ እኛም ይፈርዳል፡፡
‹‹አትፍራ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርኩ እነሆም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፣ የሞትና የሲኦል መክፈቻ አለኝ›› (ራዕ 1፡18)
አብ ፣ ወልድ ፣ መንፈስ ቅዱስ በሥልጣን አንድ መሆናቸውን አስተውል ‹‹የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ፣ የእግዚአብሔርም ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን፡፡›› (2ቆር 13፡14)
‹‹የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥልጣን እንደ አብና እንደመንፈስ ቅዱስ ነው›› እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኳችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀመዛሙርት አድርጓቸው እነሆም እኔ እስከዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ›› ይላል (ማቴ 28፡19)
በሌላው በኩል እነዚህ ወገኖች በቅዱስ መጽሐፍ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ ሰረጸ የሚለውን ኅይለ ቃል ‹‹ዳሩ ግን ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል (ዮሐ 15፡26) በሚል አገላለጽ በግልጽ ተቀምጦ እያለ ተቃዋሚዎች በልብ ወለድ ፈጠራ ከአብና ከወልድ ሰርጽዋል ይላሉ፡፡
በመሠረቱ በግልጽ ከሚነበበው ጽሑፍ ውጪ እንደ ራስ ሃሳብ መተርጎምና የሌለ ንባብ ማምጣት አንዱ የማሳሳቻ መንገዳቸው ነው፡፡
ይቀጥላል







8 comments:

  1. ኢየሱስ:- ፈራጅ ወይንስ አማላጅ?
    አንድ ወንድሜ፥ “ጌታ በመስቀል ላይ ሁኖ ዓለሙን ከፈጣሪ ሲያማልድ በዚያው ቅጽበት በዙፋኑ ላይ ሁኖ የዚህ ዓለም ገዥም ፈራጅም ነው። ዛሬም በዙፋኑ ላይ ሁኖ ይህን ዓለም ሲገዛ ለጠፋው ዓለም አማላጅም ፈራጅም ነው። ነገም በዙፋኑ ላይ ሁኖ በዚህ ዓለም ሲፈርድ ለቀረው ዓለም አማላጅም ገዥም ነው።” አለኝ። እንዴት ፈራጅም አማላጅም... መሆን ይቻላል? ስለው “የአምላክን ሥራ በጊዜና በቦታ ወስነን የምናየው አይደለም። በእርሱ ዘንድ ሁሉ ነገር አሁን ነው። ትላንት፥ ነገ የሚባል የለም። እንደሰው ግን ዛሬም ለዘለዓለሙም፤ አማላጅም ፈራጅም ነው እንላለን” አለኝ። ምን ልመልስለት...?

    ReplyDelete
    Replies
    1. እንዲህ ብለህ መልስ ፦ እስከ ዛሬ አማላጅ ነው ትሉን ነበር ቀስ ብለላቺሁ ፈራጅም አማላጅም ነው አላችሁ። ደግሞ እግዚአብሄር ከፈቀደ ከትንሽ አመታት በሁላ ፈራጅ ነው ትላላችሁ በለው። አንተ እንዲህ ብለህ ጠይቀው ፦ “ጌታ በመስቀል ላይ
      ሁኖ ዓለሙን ከፈጣሪ ሲያማልድ
      በዚያው ቅጽበት በዙፋኑ ላይ ሁኖ
      የዚህ ዓለም ገዥም ፈራጅም ነው።" የሚል ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በቀጥታ አሳየኝ በለው ካላሳየህ እናንተ በራሳችሁ ፈልስፋችሁ ትናገራላችሁ በልና እለፈው ።

      Delete
    2. ልክ ነው እይሱስ ፈረጅ ነው!!!
      መስቀል ላይ ሆና ያማልድም ይፈርድም ነበረ ያስተማረ ሐዋርያ የለም ያንተ ይቅዥት ትምህርት ነው::

      Delete
    3. እየሱስ እራሱ ፈጣሪ ነው ሌላ ፈጣሪ የለም!!

      Delete
    4. 2ኛ ቆሮ 5
      ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
      ¹⁸ ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤
      ¹⁹ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።
      ²⁰ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።
      ²¹ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።

      Delete
  2. 1937 bible keyet maggnet yichalal

    ReplyDelete
  3. ከአብ ቀኝ ተቀምጦ ስለኛ ይፈርዳል ሚለው ከየትኛው መጽሐፍ ቅድስ ነው ወደ አማረኛ የተተገጎመው በ1937 ?

    ReplyDelete
    Replies
    1. ✅ ሮሜ 8:34 ቃሉ እራሱ ከ 1940 በፊት የተፃፍ መፅሐፍት አማላጅ ሳይሆን ፈራጅ ነው የሚለው: በእንግሊዘኛም Oxford Dictionary or dictionary.com intercession የሚለውን ቃል Vito/ለ ፈራጅ ነው የሚጠቀሙት So በምንም አይነት መንገድ ይህ ጥቅስ ስለ አማላጅነት አያውራም
      ✅ 1ኛ - በሮማውይን (Rom) ዘመን ትርጉም
      ✅ 2ኛ - በግእዝ ቆንቆም
      ✅ 3ኛ - በ አማረኛ ከ 1940 በፊት በተፃፍ መፅሐፍት
      ✅ 4ኛ - በ Oxford Dictionary/dictionary.com intercession የሚለውን ቃል Vito/በስልጣኑ የሚፍርድ) ነው የሚለው
      ✅ 5ኛ - በግራመር(grammar)ከለይ ጀምረክ ስታነበው የሚክስ ማን ነው? እንጂ የሚያማልድ ማነው? ብሉ አይጠይቅም: ግራመሩ grammatically ልክ አይመጣም::

      Delete