Monday, December 19, 2016

የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና

Image result for ethiopian mary
የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(John Chrysostom. C.349-407) Archbishop of Constantinople
=====================================
ቅዱስ ዮሐንስ በዘመኑ ለተነሱት መናፍቃን የድንግል ማርያምን ዘላለማዊ ድንግልና እውነታውን አስረግጦ አስተምሮአል። መናፍቃን "ዮሴፍ የበኩር ልጇን እስከ ምትወልድ አላወቃትም የሚለውን "ማቴ1፣25። ተብሎ ስለተጻፈ ድንግል ማርያም ጌታን ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር በትዳር ኖራለች ብለው ለተነሱበት የተሳሳተ ሃሳብ ሲመልስ፣እስከ የሚለው ሃረግ ወይም ቃል " ዮሴፍ የበኩር ልጇን እስከምትወልድ አላወቃትም ማለት አንድም ወንድ እንደማታውቅ አንድም እስከ የሚለው ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው ፤ በመሆኑም ጌታን እስከምትወልድ የምትወልደው መድኃኔዓለምን እንደሆነ አላወቀም፣ የድኅነት ምክንያት ሆና እንደተመረጠች አያውቅም ነበር፣ በሉቃስ ወንጌል ላይም ማርያም ነገርን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ስለነበር ከቅዱሳን የከበረች ከመላዕክትም የበለጠች እንደነበር አያውቅም ነበር ። በሌላው ጌታን በፀነሰች ጊዜ ገጽዋ ይለዋወጥ ነበር ይህንንም ሲያይ ዮሴፍ ጻድቅም ስለነበር ሳይገልጣት ተዋት።

 ሌላው መናፍቃኑ ያነሱ የነበሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ " የጌታ ወንድሞች ተብሎ በማቴ12፣46-50፤ ማር3፣31-35 ፤ሉቃ 8 ፣19-21 ላይ የተመዘገበውን ፅንሰ ሃሳብ በመያዝ ማርያም ሌላ ልጆች አሉዋት ከዮሴፍ የተወለዱ ለሚሉትም ዮሐንስ አፈወርቅ መልስ ሲሰጥ ፤ በመስቀሉ እግር ሥር የከናወነውን ምስጢር አራቆ በመተርጎም እንዲህ አስተምሯል
ማርያም ጌታን ከወለደች በኋላ መናፍቃን እንደሚሉት ከዮሴፍ ጋር በሚስትነት ኖረች ካሉ። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን በመስቀል ላይ ሆኖ በዕለተ አርብ ከመስቀል ሥር ለነበረችው እናቱ እነሆ ልጅሽ አላት ፣ ልጆች አሏት ካሉ ለምን በመስቀል ሥር አልተገኙም ፣ ለሚወደው ደቀ መዝሙርስ ለምን በአደራነት ሰጠው ወደ ቤቱስ እንዲወስዳት ያዘዘው ብቸኛ ስለነበረች አይደለም እንዴ ይህንን ልብ ብለን እናስተውል በማለት አስተምሯል።በሌላው ለምን ወንድሞቹ ተባሉ የሚል ጥያቄ ከተነሳ በመንፈሳዊ ሕይወት አንድ ኅብረት ያላቸው ወንድማማች ስለሚባሉ፤ በሌላው ዮሴፍ ከቀድሞ ትዳሩ ባለቤቱ የወለዳቸውና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረው ያደጉ የዮሴፍ ልጆችም ነበሩና ፤ከምንም በላይ ግን ዮሴፍን በምስጢር የድንግል ማርያም እጮኛ ጠባቂ እንዳደረገ የምስጢረ ሥጋዌንም ነገር ያለጊዜው ላለመግለጥ ምስጢር ለማድረግ ነው ። አበው እንስተማሩን እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ፣ በተዋሕዶ ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣልና።
ድንግል ማርያም ጌታን ከመፅነሷ በፊት በፀነሰች ጊዜ ከፀነሰችም በኋላ ድንግል ናት። ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ ድኅረ ፀኒስ ድንግል። እንዲሁም ከመውለዷ በፊት በወለደችም ጊዜ ከመውለዷም በኋላ ድንግል ናት። ይህንንም በትንቢት እግዚአብሔር ስለገለጸለት ከአበይት ነቢያት መካከል አንዱ ሕዝቅኤል (በምዕራፍ 44 ቁጥርም 1-4) ወደ ምስራቅ ወደሚመለከተው በር አመጣኝ ይህ በርም ዝግ ነበር ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ለዘላለም ዝግ ሆኖ ይኖራል። ምስራቅ ያላት ድንግል ማርያምን ነው ፀሐይ ከምስራቅ እንዲወጣ ጨለማውንም ዓለም ብርሃን እንዲያደርግ፤ ፀሐዬ ፅድቅ ክርስቶስም ከአማናዊት ምስራቅ ከድንግል ማርያም ተልወዶ በኅጢያት ለጨለመው ዓለም የጽድቅ ብርሃን ሆኖ ተገልጧልና (ዮሐ1፣5) ጠቢቡ ሰሎሞንም በመኃልዬ መኃልይ መዝሙሩ "እህቴ ሙሽራዬ ሆይ የተዘጋ ገነት የታተመ ፈሳሽ ነሽ" በማለት ስለዘላለማዊ ድንግልናዋ ጽፏል።(መኃ4፣12)
Image result for john chrysostom icon


እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዘሀገረ ሳላሚስ፣ ቆጵሮስ ሊቀ ጳጳስ( C.310- d.407)
==============================================================
አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በተለየ ሁኔታ የቤተ ክርስቲያን አበው ሥነ ጽሑፍ ከፍተኛ ዕድገት ያሳየበት ወርቃማ ዘመን በመባል ይታወቃል። በዚህ ክፍለ ዘመን ውስጥ ተነስተው በሃይማኖት ጸንተው መጻሕፍትን ጽፈው በተለይም ደግሞ በ325ዓ.ም በጉባኤ ኒቂያ በነበረው የሲኖዶስ ውይይት ላይ ፣በአደባባይ ተከራክረው መናፍቃንን ካሳፈሩ ሊቃውንት መካከል አንዱ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ አንዱ ነበረ።
የጌታችንን የመድኅኒታችንን መለኮታዊ ባህርይ ለሚጠራጠሩ አርዮሳውያን እና በተዋሕዶ ሰው ሆኖ መክበሩን ለሚክዱ ( Apollinarians) መናፍቃን ፡ ቅዱስ ኤጲፋኒዮስ ስለ ተዋሕዶ ምሥጢርና ድንግል ማርያም የመለኮት እናት ስለመሆኗ እንዲህ አስተምሮአል፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውና አምላክ ወይም ሰው ሲሆን አምላክ ፣ አምላክ ሲሆን ሰው በተዋሕዶ የከበረ ነው ፣ በአምላክነቱ መለኮታዊ ባሕርይ ቢኖረውም እንደ ሰውነቱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለዘርአ ብዕሲ ተፀንሶ በድንግልና ተወልዷል። እንደ ኤጲፋንዮስ ገለጻም በነቢዩ በኢሳይያስ ትንቢት መሠረት (ኢሳ 7፣14) እግዚአብሔር ምልክት ይሰጠናል ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው ፣እርሱም ድንቅ መካር ኃያል የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። በመሆኑም እመቤታችን የአምላክ እናት የእግዚአብሔር እናት (Theoto'kos)God-bearer ትባላለች ።
በቅዱስ ጳውሎስም መልዕክት እንደተገለጸው (ገላ4፣4) የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ያለ ዘርአ ብእሲ ያለ ወንድ ዘር ከሴት( ከድንግል ማርያም ከአምላክ እናት Theoto'kos Mary የተወለደውን አንድያ ልጁን ላከልን ፣ የእኛን ባህርይም ባህርይ አድርጎ ተወለደ ። እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ ከህግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ፤ልጆችም ስለሆናችሁ እግዚአብርሔ አባ አባት ብሎ የሚጮህ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።" በመሆኑም በለበሰው ስጋ አምላኬ እግዚአብሔር ብሎ ይጣራል ፣ በዘላለማዊ መለኮታዊ ባህርይውም የባህርይ አባቱን አባቴ ብሎ ይጠራዋልና።"
ቅዱስ ኤጲፋንዮስ የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና ጽኑ እምነት አለው ለሚቃወሙትም እናንተ ግብዞች ተካራካሪ መናፍቃን ለመሆኑ ቅድስት ድንግል ማርያምን "ድንግል የሚለውን ሐረግ ሳይጨምር የሚጠራ ካለ እርሱ የማያስተውል ነው እላለሁ ምክንያቱም መጻህፍትና የእግዚአብሔር ኃይል አልተገለጸለትም። አረጋዊው ዮሴፍን እግዚአብሔር ድንግል ማርያምን እንዲጠብቅና በእስራኤል ባህል እንደሚሆነው ሴት ያለ ትዳር ፀንሳ ብትገኝ ትወገራለች በአደባባይም ትዋረዳለችና ፣ ይህንን ክብሯን እንዲጠብቅላት እንጅ ድንግል ያለ ዘርአ ብእሲ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ነው የወለደችው። በወንጌልም የጌታ ወንድሞች የተባሉት ዮሴፍ ከቀድሞ ትዳሩ የወለዳቸው ልጆቹ ሊሆኑ ይችላሉ፤አንድም ከጌታችን ጋር በሥጋዌ ዘመኑ አብረው ያደጉ የቅርብ ዘመዶች ና አብሮ አደጎች ናቸው በማለት አብራርቶ አስተምሯል። 
No automatic alt text available.
ትርጉም ፦በመምህር ቸርነት ይግረም ( PhD candidate)
(Mary and the Fathers of church)

No comments:

Post a Comment