Saturday, June 28, 2014

‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም›› (ማቴ16፡18)




ይህንን ኀይለ ቃል ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊሊጶስ ቂሳሪያ ለሊቀ ሐዋርያት ለቅዱስ ጴጥሮስ ተናግሮታል፡፡ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወለድ በተለየ አካሉ ጸጋና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ፡፡ (ዮሐ 1፡14)
ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም ነፍስና ሥጋን ነስቶ በፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆነ ‹‹ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ህፃን ሆኗልና፣ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘላለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ ኀጢዓትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት ይህን ወድዷልና፡፡ ክብሩ ተለይቶት የነበረ ሥጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው የጸጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ሥጋንም የባሕርይ ገዥ ሊያደርገው ወደደ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ››
(ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 220)



Monday, June 16, 2014

ክርስቲያናዊ ቤተሰብእ



 

 

ቤተሰብእ ማለት በቅዱስ ጋብቻ አማካይነት በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች (ወንድና ሴት) ግንኙነት የሚጀመረውና ቁጥራቸው ይነስም ይብዛም የሚወለዱትን ልጆች ጨምሮ በጋራ የሚመሰረተው ማኅበር ነው፡፡
እንዲህ ዓይነት ቤተሰብእ የሚመሰረተው በቅዱስ ጋብቻ በሥጋውና ደሙ አማካኝነት ነው  ይህም የጋብቻ ቡራኬና ጸሎት የሚፈጸመው አምላካችን እግዚአብሔር በሥነ-ፍጥረት ጊዜ ሰው እንዲበዛ ቅዱስ ፈቃዱ ስለሆነ ለመባዛቱም ምክንያት የሚሆነው የወንድና የሴት ግንኙነት ሲኖር መሆኑን በማረጋገጥ አዳምና ሔዋንን ፈጥሮ እንዲህ ሲል የፈጸመውን የመጀመሪያ የተክሊል ጸሎትና ቡራኬ መነሻ በማድረግ ነው ‹‹እግዚአብሔርም ሰውን ፈጠረ በመልኩ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠራቸው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው እግዚአብሔርም አላቸው ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት የባሕሩንም አሣ የሰማዩንም ወፍ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሰውን እንሰሳ ሁሉ ግዙ›› ዘፍ 1፡27



Tuesday, June 3, 2014

ክርስቲያናዊ ሥነምግባር



ክርስቲያናዊ ሥነምግባር
አጠቃላይ ፈተና

‹‹ንዌጥን በረድኤተ እግዚአብሔር››
1.  ከአስርቱ ትዕዛዛት ይመደባል
ሀ/ ህገ-ልቡና
ለ/ አትስረቅ
ሐ/ የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው
መ/ ሁሉም
2.  እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ስላረፈ ይህንን ቀን ቀደሰው………………….
ሀ/ ቀዳሚውን ሰንበት
ለ/ የመጀመሪያውን ቀን
ሐ/ እሁድን ዕለት
መ/ ሁሉም


ትምህርተ ሃይማኖት

 



ለቀዳማይ ክፍል የተዘጋጀ
አጠቃላይ ፈተና
‹‹ንዌጥን በረድኤተ እግዚአብሔር››
1.  እግዚአብሔር የሚለው መጠሪያ ስም
ሀ/ የተጸውኦ ስም ነው              ሐ/ የተቀበአ ስም ነው
ለ/ የግብር ስም ነው                 መ/ የባሕርይ ስም ነው
2.  ሀልዎተ እግዚአብሔር ……………………………. የምንማርበት የትምህርት ክፍል ነው
ሀ/ የመላእክትን አኗኗር              ሐ/ የእግዚአብሔር አኗኗር
ለ/ የሰውን ህልውና                 መ/ መልስ የለም