Tuesday, June 3, 2014

ትምህርተ ሃይማኖት

 



ለቀዳማይ ክፍል የተዘጋጀ
አጠቃላይ ፈተና
‹‹ንዌጥን በረድኤተ እግዚአብሔር››
1.  እግዚአብሔር የሚለው መጠሪያ ስም
ሀ/ የተጸውኦ ስም ነው              ሐ/ የተቀበአ ስም ነው
ለ/ የግብር ስም ነው                 መ/ የባሕርይ ስም ነው
2.  ሀልዎተ እግዚአብሔር ……………………………. የምንማርበት የትምህርት ክፍል ነው
ሀ/ የመላእክትን አኗኗር              ሐ/ የእግዚአብሔር አኗኗር
ለ/ የሰውን ህልውና                 መ/ መልስ የለም


3.  ምስጢረ ቁርባንን የመሠረተው ማነው?
ሀ/ ቅዱሳን ሐዋርያት                ሐ/ መግደላዊት ማርያም
ለ/ ዮሴፍና ኒቆድሞስ                መ/ ኢየሱስ ክርስቶስ
4.  ……………………… እግዚአብሔር በአርምሞ (በዝምታ) የፈጠራቸው ፍጥረታት ናቸው
ሀ/ ሰማይ       ለ/ መላዕክት        ሐ/ ምድር         
መ/ አራቱ ባሕርያተ ሥጋ      ሠ/ ሁሉም
5.  እግዚአብሔር የሚለው ቃል ከሚከተሉት ውስጥ ከየትኛው ቋንቋ የተገኘ ነው
ሀ/ ግሪክ        ለ/ ግዕዝ           ሐ/ ዕብራይስጥ      መ/ አማርኛ
6.  የእግዚአብሔር ባሕርይ ወይም የራሱ ብቻ መገለጫ ጠባይ ነው
ሀ/ ዘላለማዊነት        ለ/ ኤልሻዳይነት           ሐ/ ጥበበኛነት
መ/ ከ ‹‹ሐ›› በስተቀር ሁሉም
7.  ‹‹ቁርባን›› የሚለው ቃል ከ……………. ቋንቋ የተገኘ ነው
ሀ/ ግሪክ        ለ/ ግዕዝ           ሐ/ ሱርስት         መ/ አማርኛ
8.  በኢ.ኦ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልጅነት ጥምቀት በማን ስም ይከናወናል?
ሀ/ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ብቻ
ለ/ በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐ/ በሥላሴ ስም
መ/ ለ ና ሐ
ሠ/ ሁሉም
9.  ከሚከተሉት አንዱ የሥላሴ የባሕርይ ከዊን ስም ነው
ሀ/ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ
ለ/ ልብ፣ ቃል፣ እስትንፋስ
ሐ/ አባት (ወላዲ)፣ ልጅ (ተወላዲ)፣ ሠራጺ
10.  መንፈስ ቅዱስ ከ…………………….. ይሰርጻል
ሀ/ ከአባት             ለ/ ከአብ           ሐ/ ከወልድ
መ/ ከመንፈስ ቅዱስ     ሰ/ ሀ ና ለ
11.  የሥላሴ ‹‹ቃል››
ሀ/ የዓለምን ኃጢዓት የሚያስወግድ
ለ/ ሎጎስ
ሐ/ አካላዊ ቃል
መ/ ‹‹ለ›› ብቻ
ሠ/ ሁሉም
12.  ከሚከተሉት የትኛው የእግዚአብሔርን አንድነት ይገልጻል
ሀ/ አካል        ለ/ ህላዌ           ሐ/ ስም           መ/ ግብር
13.  ከሚከተሉት አንዱ እግዚአብሔር ሰው የሆነበት ዓላማ ነው
ሀ/ አባትነቱንና አምላክነቱን ለሁሉም መሆኑን ሊያስረዳ
ለ/ ሞትን ሊሽር ኃጢዓትን ሊደመስስ
ሐ/ በአባቱ ተገዶ
መ/ ሀ ና ለ
14.  ሊቃውንት (መጻሕፍት) አካላዊ ቃልን የሚጠሩበት ስም ነው
ሀ/ ጥበብ        ለ/ የአብ ክንድ            ሐ/ ሀ ና ለ
መ/ መልሱ የለም
15.  ቁርባን ማለት ምን ማለት ነው
ሀ/ መስዋዕት                      ለ/ መባዕ፣ ስጦታ
ሐ/ ሥጋወደሙ                    መ/ ሁሉም
16.  ምስጢረ ትንሣኤ ሙታንን የማያምኑ የትኞቹ ናቸው?
ሀ/ ኦርቶዶክሳውያን                 ለ/ ሰዱቃውያን
ሐ/ ፈሪሳውያን                      መ/ ሁሉም
17.  ምስጢረ ጥምቀት ምንድን ነው?
ሀ/ የመንግስተ ሰማያት መግቢያ በር
ለ/ የሥላሴ ልጅነት የሚሰጥበት
ሐ/ ዳግመኛ የምንወለድበት
መ/ ሥርየተ ኃጢዓት የሚሰጥበት
ሠ/ ለ ና መ ብቻ
ረ/ ሁሉም
18.  እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከሚጠራባቸው ስሞች መካከል
ሀ/ አጽናኝ       ለ/ ልጅ                  ሐ/ አባት           መ/ ሁሉም
19.  ‹‹ሐዋርያው ጳውሎስ  እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ስለ ሾመ ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ›› (ሐዋ 20፡28)
እግዚአብሔር ያለው ……………………………………. ነው
ሀ/ አብን              ለ/ ወልድን               ሐ/ መንፈስ ቅዱስን
መ/ ኢየሱስን          ሠ/ ለ ና መ              ረ/ ሁሉም
20.  በእግዚአብሔር መንፈስ ተቀኝቶ ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት አድርጎ ‹‹እኔስ እግዚአብሔር ባልኩ ጊዜ የምናገረው ስለ አብ፣ ስለ ወልድ፣ ስለመንፈስ ቅዱስ ነው›› ሲል የተናገረው ሊቅ (አባት) ማነው?
ሀ/ ቅ/ጎርጎርዮስ ዘእንዜናዙ
ለ/ ቅ/ ዮሐንስ አፈወርቅ
ሐ/ ቅ/ባስሊዮስ
መ/ ቅ/አትናቴዎስ
21.  ሥላሴ የሚለው ቃል በሰማንያ አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በየትኛው ክፍል ተጽፎ ይገኛል?
ሀ/ መጽሐፈ ጥበብ                  ሐ/ መልእክተ ዮሐንስ
ለ/ መጽሐፈ ሲራክ                  መ/ ወንጌላት
22.  ከሃያ ሁለቱ ሥነ ፍጥረት የትንሣኤ ሙታን ባለቤት የትኛው ነው?
ሀ/ የሰው ልጅ                     ሐ/ የሰኞ ፍጥረታት
ለ/ የእሁድ ፍጥረታት               መ/ ለ ና ሐ
23.  የብሉይ ኪዳን ቁርባን የሚሰጠው ጥቅም …………………… ነው
ሀ/ ድኅነተ ሥጋ ና በረከተ ሥጋ ያሰጥ ነበር
ለ/ ከኀጢዓት ያነጻ ነበረ (በተወሰነ ደረጃ)
ሐ/ ከጥንተ አብሶ ያነጻ ነበረ
መ/ የዘላለም ሕይወት ያሰጥ ነበረ
ሠ/ ሀ ና ለ
24.  ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢር አይመደብም
ሀ/ ምስጢረ ቁርባን                       ሐ/ ምስጢረ ሜሮን
ለ/ ምስጢረ ጥምቀት                      መ/ ምስጠረ ሥጋዌ
25.  በብሉይ ኪዳን የምስጢረ ቁርባን ምሳሌ ነው
ሀ/ ለእስራኤል የወረደ መና
ለ/ የኖህ መርከብ ና የአብርሃም ድንኳን
ሐ/ መልከ ጼዴቅ ለአብርሃም ያቀረበው ኅብስትና ጽዋ አኮቴት
መ/ የኢዮብና የንዕማን በዮርዳኖስ መጠመቅ
ሠ/ መልሱ ሁሉም ነው              ረ/ ሀ ና ሐ
26.  እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ በመሆኑ ……………………..
ሀ/ ‹‹እስከ ሺህ ትውልድ ምህረቱን ያደርጋል››
ለ/ እርዱኝ እረዳችኋለሁ አለ
ሐ/ ሳይንስቲስቶች ተመራምረው ደረሱበት
መ/ በእውቀት ሁሉን ይጠብቃል የሚሣነው ነገር የለም
ሠ/ ሁሉም
ረ/ ሀ ና መ
27.  እግዚአብሔር ‹‹ቅዱስ›› ነው፣ ጻድቃን ቅዱሳን ናቸው፣ ቅዱሳን መላዕክት ቅዱሳን ናቸው ስንል ልዩነቱ ምንድን ነው?
ሀ/ የመላዕክት ቅድስና የተፈጥሮ ነው
ለ/ የጻድቃን ቅድስና የተፈጥሮ ነው
ሐ/ የእግዚአብሔር ቅድስና የባሕርይ ነው
መ/ የመላዕክትና የጻድቃን ቅድስና ከእግዚአብሔር ነው
ሠ/ ሐ ና መ
ረ/ ሀ ፣ ሐ፣ መ ልክ ናቸው
28.  የእግዚአብሔርን ፍቅር በምን እናውቃለን
ሀ/ በቸርነት     ለ/ በትዕግስት             ሐ/ በጸጋው        መ/ ሁሉም
29.  ‹‹ያህዌ›› ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ/ ያለና የነበረ እንደ ባሕርይው የሚሠራ
ለ/ ኀያል አምላክ
ሐ/ አምላከ አማልክት
መ/ ሁሉን ቻይ
30.  ዓለመ መላዕክት ያልሆነውን ለይተህ አውጣ
ሀ/ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት
ለ/ መንበረ መንግስት
ሐ/ ሰማይ ውዱድ
መ/ ጽርሐ አርያም
ሠ/ ሁሉም
31.  አዳም የተፈጠረባት ሥፍራ ……………………… ትባላለች
ሀ/ ገነት        ለ/ ኤረር           ሐ/ ራማ           መ/ ኤልዳ   
ሠ/ ሁሉም
32.  እግዚአብሔር የሚለውን ስም በሦስት ከፍለን ስንተረጉም……………………… የሚለውን ይሰጠናል፡፡
ሀ/ ጌታ፣ አባት፣ ቸር                         
 ለ/ ዓለማትን ፈጥሮ  የሚገዛ አምላክ    
ሐ/ እግዚእ፣ አብ፣ ደግ (ኁርኁ)
መ/ ጌታ ፣አባት ፣  ሩኅሩኅ
ሠ/ ሁሉም                  ረ/ ከ ‹ለ› በቀር
33.  ለአዳም ሔዋን የተፈጠረችበት ዓላማ
ሀ/ ለውበትና ለጌጥ
ለ/ በዝተው ምድርን እንዲሞሉ
ሐ/ ከፈተና እንዲጠበቅ
መ/ በሚያስፈልገው ሁሉ ረዳት ትሆነው ዘንድ
ሠ/ ሁሉም
ረ/ ከ ‹ሀ› በቀር
34.  ፍጥረታት በስንት ቀን ውስጥ ተሠርተው ተከናወኑ
ሀ/ በ22         ለ/ በ7       ሐ/ በ6      መ/ በዕለተ ረቡዕ    ሠ/ ሁሉም  
35.  ሰው (ሰብዕ) ከ ………………………. ባሕርያት ተሠራ
ሀ/ ከሰባት ባሕርያተ ሥጋ
ለ/ ከባሕርያተ ሥጋና ከባሕርያተ ነፍስ
ሐ/ ከሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ
መ/ ለ ና ሐ
ሠ/ ሁሉም
36.  እግዚአብሔር ከፍጥረቱ (ሰውና መላዕክት) የሚጋራው ባሕርይ ………………. ነው
ሀ/ ጥበብ        ለ/ ሁሉን ቻይነት          ሐ/ ቅድስና         መ/ አዋቂነት
ሠ/ ሁሉም            ረ/ ከ ‹ለ› በስተቀር ሁሉም
37.  የእግዚአብሔር ‹‹ቃል›› ሥጋን በተዋሐደ ጊዜ የተጠራበት ስም
ሀ/ አማኑኤል፣ ኢየሱስ፣ መሲህ፣ ክርስቶስ
ለ/ ኤልሻዳይ፣ እግዚአብሔር፣ ያህዌ
ሐ/ ኢየሱስ፣ ያህዌ፣ መሲህ
መ/ አማኑኤል፣ ኢየሱስ፣ ኤልሻዳይ
ረ/ ሁሉም
38.  ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙን መቀበል ያለበት ማን ነው?
ሀ/ አዛውንትና ሽማግሌዎች ብቻ
ለ/ የታመሙ ሰዎች ብቻ
ሐ/ ሕፃናት ብቻ
መ/ በተክሊል (በቁርባን) የሚያገቡ ብቻ
ሠ/ ካህናት ብቻ
ረ/ ንስሐ ገብተው የተዘጋጁ ሁሉ
39.  ‹‹ይህንን ለመታሰቢያዬ አድርጉት›› ሉቃ 22፡20 ሲል መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ማለቱ ነው?
ሀ/ ለእኔ እንዳልረሳ ማስታወሻ
ለ/ ጸሎተ ሐሙስን ማስታወሻ (ማቴ 26፡40)
ሐ/ በተቀበላችሁ ጊዜ ሞቴን፣ ግርፋቴን፣ 13ቱን መከራ እያሰባችሁ
መ/ ዕለተ ሞታችሁን እያሰባችሁ
40.  ፃድቃን በበግ ኀጥአን በፍየል ለምን ተመለሱ (10 ነጥብ)
41.  ክርስትና ስምህን፣ ንስሐ አባትህን ፃፍ (ጻፊ)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

No comments:

Post a Comment