Sunday, September 28, 2014

“ዕፀ መስቀሉ ከየት መጣ”


“ዕፀ መስቀሉ የት መጣ”

የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔ ኃይል ነውና እንደተባለው በቆሮ 1÷18/ ክርስቲያኖች ኃይላችን፣ መመኪያችን፣ ነፍሳችን መዳኛና የምንጸናበት መስቀል እናምናለን፡፡ ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “እግሮቼ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን” እንዳለም /መዝ 131÷7/ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ውሎ እኛ ለሠራነው ኃጢአት ካሣ እንደሆነ እያሰብን እንሰግድለታለን፡፡ በልባችን፣ በሰውነታችንና በቤታችን እንስለዋለን፡፡ በአባቶቻችን እንባረክበታለን፡፡ እንደትምህርታችን የድኅነታችን ብርሃን የበራበት ይህ መስቀል የእንጨት ነው፡፡ እንጨት ከመሆኑ ጋርም አንድም ለመስቀሉ ካላቸው ፍቅር ወይም ታሪክን በተረት ቀርፀው ከማስቀረት ልማዳቸው የተነሣ ይህ መስቀል ከየት መጣ? ለሚለው አባቶች የሚተርኩት አንድ ታሪክ አለ፡፡ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

ሊቶስጥራ የሚባል የእንጨት አገር አለ፡፡ ከዚያ ስምንት ዕፅዋት ቆርጠው ቁመታቸውን ሰባት ክንድ ከስንዝር ወርዳቸውን ሶስት ክንድ ከስንዝር መስቀል ሥርናይ ስምንተኛ ዕፀ ከርካዕ ናቸው፡፡ አንድም ሰባት ናቸው፡፡ ዘይቱንና ወይራውን አንድነት ያጸድቁታል፡፡ ዘይቱን ቆርጠው ወደታች ልጠው ወይራውንም ቆርጠው ወደ ላይ ልጠው ዘይቱን ፈልፍለው ወይራውን አሹለው በዘይት ላይ ተክለው የዘይቱን ልጥ ወደ ወይራው የወይራውን ልጥ ወደ ዘይቱ አስረው ቢቱውት ጸድቆ ለምልሞ ከዘይቱ ጣዕም መዓዛ ዘለግታ ከወይራው ኃይል ጽንዕ፤ ሥርናይንም ቢተውት ሰሎሞን “ሐረገ ወይን ዘእምኃሢሦን ይትገዘም ወበጎልጎታ ይተከል” ብሎ ነበርና፡፡

ሰባተኛ ዕፀ በወይን ነው፤ በለሶችስ ከየት ተገኙ ቢሉ ሳኦል ልጁ ቢታመምበት ካህናቱን አስጠርቶ “እናንተ ሀገር አይደላችሁ አልገዛችሁ፤ ፈረስ አይደላችሁ አልጋልባችሁ፣ ልጄ ፈውሱልኝ” ቢላቸው ይህማ እንዴት ይቻለናል? ይልቅስ እንምከርህ፤ የንስሩን ግልገል ከግንብ ዝጋበት፡፡ ንስሩም ልጁን ወዳጅ ነውና ሀገር ለሀገር እየዞረ ሲጮህ ግልገሉም ከግንብ ውስጥ ሆኖ የአባቱን ጩኸት ሰምቶ ይጮሃል አባቱም የልጁን ጩኸት ሰምቶ ከገነት ዕፀ በለስን አምጥቶ በግንቡ ላይ ሲጥልበት ግንቡ
ይሰበራል፡፡ ልጁን ይዞ ይሄዳል፤ አንተም ከበለሱ አሽተህ ስትቀባው ይፈወስልሃል” ቢሉት አደረገ፡፡ ተፈወሰለት፡፡ በለሱንም ከተክል ቦታ ቢያስተክለው ጸደቀ፡፡ ሰሎሞንም በርካታ አገልጋዮች ነበሩትና እንጨት ቆርጣችሁ አምጡ ቢላቸው ሊቆርጧት ቢሄዱ እንደ እሳት ፈጀቻቸው፡፡ “እንዲህ ያለች እንጨት አግኝተን ልንቆርጣት ብንሄድ እንደ እሳት ፈጀችን” አሉት፤ ሰው ሰዶ አስቆርጦ አስመጣው፤ መድረክ ቢያደርገው ረዘመ፤ መቃን ቢያደርገው አጠረ፤ እንዳይቆርጠው አሳዝኖት ከአደባባይ አኖረው፡፡

የኢትዮጵያ ንግሥት ማክዳ የምትባል ዘንዶ ስታስገድል ደሙ ቢነካት በእግርዋ እንደፍየል ቀንድ ያለ ወጥቶባት ነበርና የሰለሞንን ጥበብ አይቼ እግሬን ተፈውሼ ልምጣ ብላ ብዙ ሠራዊት አስከትላ ኢየሩሳሌም ሄደት፡፡ ወሓረት ንግስት አዜብ ከመ ትርአይ ጥበቢሁ ለሰሎሞን እንዲል፡፡ ከአደባባዩ ድንኳን አስተክላ ስትኖር የንጉሡ ባለሟል ንገርልኝ አለችው፡፡ እሱም የእግርዋን መዞር የመልኳን ማማር አይቶ “ጃንሆይ ከአንተ የማይመጣ የለም፡፡ መልኳ ያማረ እግርዋ እንደፍየል የዞረ ሴት መጥታለች” አለው፡፡ ይህ ባይገኝባት ትቀጣለህ አስኪ ጥራት ብሎ ስትገባ ያ በእግርዋ የነበረው ወደቀላት፤ ለገረድዋ ይህን ያዥው ብላት ገባች፤ ሰሎሞንም ምን ብለኸኝ ነበር? ንሳ ባለወግ ጥራ ብሎ ቢቆጣ ጃንሆይ አዎን ነበረብኝ፡፡ ከደጅህ የወደቀ ዕንጨት ሲነካኝ ወደቀልኝ አሁን እንዲህ ያለውን ፈዋሽ እንጨት ይጥሏልን? ብላ እንጨቱን እሷ አንድ ብር ሰሎሞን አንድ ብር አውጥተው በሁለት ብር አስለበጡት፡፡ ከሰሎሞን በኋላ የነገሡት ነገሥታትም 28 ናቸው፡፡ በዘመናቸው አንድ አንድ ተአምር እየሠራላቸው አንድ አንድ ብር እያወጡ ይለብጡት ነበር፡፡ በ30 ብር ለብጠው ይህንን የነካ ርጉም ይሁን ብለው ከቤተመቅደስ አኖሩት፡፡ ጌታችን የተሸጠ ዕለት አይሁድ ቀርፈው ለይሁዳ ሰጡት ርግማኑም በይሁዳ ደረሰ፡፡ አንድም ሰሎሞን ጠላት ተነሥቶበት ዘመቻ ሲሄድ አዕዋፉን ሁሉ በጥበቡ ይገዛቸው ነበር፤ ፀሐይ እንዳይመታው ክንፋቸውን ጋርደውለት ሲጓዝ አንድ ንስር አልገዛለት ብሎ ሄደ፡፡ ሰሎሞንም የንስሩን ግልገል ከግንብ ውስጥ ዘጋበት፡፡ አባትየውም ንስር ከገነት ዕፀ በለስን አምጥቶ ከግንቡ ላይ ቢጥልበት ግንቡ ተናደ፡፡ ልጁን ይዞ ሄደ፡፡ ከዚህም በኋላ በሀገረ ሎጥ የነበሩ ሰዎች ጎን እየቀደዱ ጥርስ እያወለቁ ያወስቡ ነበር፡፡ የሎጥም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩትና ከሊህ ከክፉዎች እንዳይጋቡ ብሎ ከወንድ ጋር ከልክሏቸው ሲኖሩ እነርሱም አባታቸው ልጅ እንዳንወልድ ከወንድ ከልክሎን ሊኖር ነው ጠጅ አረቄ አጠጥተው ከመካከላቸው አስተኙት፡፡ በግብረ ሥጋ ቢገናኛቸው ሁለቱም ፀነሱ፤ ሎጥም ወደ አብርሃም ሄዶ እንዲህ ያለ መከራ አግኝቶኛል ምከረኝ ቢለው በለሱን ቆርጠህ በእሳት አክስለህ ተክለህ አልቅስበት ጸድቆ ለምልሞ ቢገኝ እግዚአብሔር እንደታረቀህ በዚህ ዕወቀው፡፡ ሶስተኛ እስክንድር ገነትን ሊያይ በወደደ ጊዜ ንስር ግልገል ከባዝራ ፈረስ አላምዶ አዋለደ፡፡ ፈረሱም እንደርስዋ አራተኛ እግር እንደ አባቱ ሁለቱ ክንፍ ያለው ንስር ብትወልድ በሥጋ አሳደገው፡፡ እስክንድርም 40 ቀን ሱባኤ ገባ፡፡ ንስሩን ሶስት ቀን ከምግብ ከለከለው፡፡ ሥጋ በዘንግ አስሮ በንስሩ እያለ ገነት ይዞት ገባ፡፡ ንስሩን ከዕፀ በለስ አሥሮ ወደ መሐል ሲገባ ጠባቂዋ ሱራፌል መልአክ ማነህ የት ትገባለህ? ቢለው እኔ እስክንድር ነኝ፡፡ የእናት አባቴን አገር ላያት ቢለው በጾም በጸሎት ተጠምደው የሚኖሩ አበው ቅዱሳን ሳይገቡ አጠገቧ ይኖራሉ፡፡ አንተ በፍልስፍና በጥበብ ገባህ ብሎ የብርሃን ሰይፍ ቢያሳየው ደንግጦ ከንስሩ ላይ ወጣ፡፡ በዘንግ ያለውን ሥጋ አቆልቁሎ ቢያየው ንስሩ እስክንድርንና ዕፀ በለሱን ይዛቸው ወደ ኢየሩሳሌም አደባባይ ወረደ፡፡ ዕፀ በለሱም ዕፁብ ድንቅ ዕፁብ ድንቅ እየሸተተ ሰውን ሁሉ ሥራ ቢያስፈታ በዮርዳኖስ ወስዳችሁ ጣሉት አላቸው፡፡ ቢጥሉት አቆልቁሎ መውረዱን ትቶ አሻቅቦ ወጣ፡፡ እስክንድርም ይህ ዕፀ በለስ ነገር ያለው ነው ብሎ ካታክልት ቦታ ቢያስተክለው ጸደቀ፡፡ አራት ዕፀ አምስት ዕፀ ዘይት ስድስተኛ ዕፀ ከርካዕ ሰባተኛ ዕፀ ወይን ጌታችን የተሰቀለባቸው ዕፀዋት እኝህን ናቸው፡፡ አይሁድም እሊህን በሙሸ ዘር አንድ አድርገው በብረት ቸንክረው ጌታችንን አሸክመው ወደ ቀራንዮ ሲወስዱት በኋላም ያሉት ቶሎ ቶሎ አትሄድም ብለው ሲገፉት በልቡ ይወድቃል፡፡ በፊቱ ያሉት ዝግ ብለህ አትሄድም ምን ያስቸኩልሃል ብለው ሲገፉት በጀርባው ይወድቃል፡፡ እንዲህ እያደረጉ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ድረስ 136 ጊዜ በምድር ላይ ጣሉት፡፡ መስቀሉ እጅግ እርጥብ ነበርና ጌታችን እጅግ ደከመው፡፡

 

No comments:

Post a Comment