ክብረ ቅዱሳን






ቅድስት እንባመሪና









የቅድስት እንባመሪና እናት ማርያም ትባላለች ገናም ህጻን እያለች ነበር በሞት የተለየቻት ከዛም አባቷ ለአቅመ ሔዋን እስክትደርስ ድረስ በጎ ትምህርቶችን ሲያስተምራት አሳደጋት በኋላም ለአቅመ ሔዋን ስትደርስ አጋብቷት እሱ ወደ መነኮሳት መኖሪያ ሄዶ ሊኖር እንደ ወደደ ሲነግራት እጂግ አልቅሳ "አባቴ ያንተን ነፍስ አድነህ የኔን ነፍስ ማጥፋት እንዴት ይሆንልሃል ?" አለችውና አባቷም እኔ የምሄደው ወደ ወንድ መነኮሳት ነው አንቺ ደግሞ ሴት ነሽ አያስገቡሽም ሲላት እንደ ወንድ ሱሪ አድርጌ ጸጉሬን ተቆርጬ ወንድ መስዬ ካንተ ጋር ሄዳለው አለችውና :ያላቸውን ንብረት ሁሉ ሽጠው እና ለደሃ መጽውተው ተያይዘው ገዳም ይ...ገባሉ:: በዚአም ገዳም እጅግ እየተጋደሉ ኖሩ በኋላም አባቷ በጸና ታመመና አበ ምኔቱን አስጠርቶ ልጄን አደራ በምንም መልኩ ከገዳም እንዳይወጣብኝ ይልና አበ ምኔቱን አደራ ይለውና ያርፋል: ቅድስት እንባመሪናም ተጋድሎዋን ከቀድሞ እጅግ አብዝታ ትተጋ ጀመር:ከረጅም ግዜ በኋላም የገዳሙ መነኮሳት ይሄ መነኩሴ ከኛ ጋር ለምንድን ነው ከገዳም ውጪ ለተልዕኮ የማይወጣው እያሉ አበ ምኔቱን አስጨነቁት በኋላም አበ ምኔቱ ከመነኮሳቱ ጋር አብሮ ይሰዳት ጀመር የሚሄዱትም የገዳሙን ምግብ በየግዜው ከሚሰበስብላቸው አንድ ሰውዬ ቤት ነበር:እንዳስለመዱት በየግዜው ሲሄዱ አንድ ቀን ምግቡን የሚሰጣቸው ሰውዬ አንዲት ልጅ አለችውና ጎረቤት የሆነ አንድ ጎረምሳ ተደብቆ ይገባና የሰውዬውን ልጅ ድንግልናዋን ያፈርሳል በኋላም አባትሽ ማነው እንዲህ ያደረገሽ ብሎ ከጠየቀሽ እንባመሪና ነው በይ ይላትና ይሄዳል ልጅቷም ታረግዛለች ፣ አባትየውም ከማን እንዳረገዘች ሲጠይቃት ከመነኩሴው ከእንባመሪና ነው አለችው:ከዛም ያ ሰውዬ ወደ ገዳሙ ይመጣና ባአደባባይ መነኮሳቱን ይረግማቸው ጀመር ከዛ አበ ምኔቱ መጣና ምን ሆነህ ነው ቢለው ልጄን ያንተ መነኩሴ ደፈረብኝ ሲለው ታድያ ባንድ ሰው ጥፋት እነዚን ሁሉ ቅዱሳን ለምን በአደባባይ ትረግማለህ አለውና እንባመሪናን አስጠራት መጣችና አቤት አባቴ ስትል ሁሉም ይሰድቧት ጀመር ለምን እንደሚሰድቧት ባታቅም ሰይጣን የሰራባት ነገር እንዳለ ገብቷት ዝም አለች በኋላም ነገሩን ነገሯት እና አበ ምኔቱ "እንባመሪና ይህ የመነኩሴ አይደለም የአለማውያንም ባህሪ አይደለም የሰይጣን እንጂ ይህን ለምን አደረክ?"ብሎ ቢጠይቃት እሷም አባቴ ይቅር በለኝ ወጣትነት አታሎኝ ነው አባቴ ይቅር በለኝ ብላ አበ ምኔቱ እግር ስር ወደቀች በኋላም አበ ምኔቱ ከገዳሙ አባረራት እና ከገዳሙ ውጪ ሆና ትጋደል ጀመር ያቺም ልጅ ስትወልድ አባቷ ልጁን አምጥቶ ለእንባመሪና ሰጣት እንባመሪናም ለልጁ የሚሆን ወተት እና ምግብ በአካባቢው ያሉትን እረኞች እየለመነች አሳደገችው:ከ3 አመት በኋላም መነኮሳቱ አበ ምኔቱን ለመኑት ባይሆን ከባድ ቀኖና ይሰጠውና ወደ ገዳም ይግባ አሉት:አበ ምኔቱም ልመናቸውን ተቀብሎ ከባድ ቀኖና ሰጣት እና ስትጨርስ ወደ ገዳሙ ተቀላቀለች ከዛም ገዳሙ ውስጥ ያሉትን ከባድ ስራዎች ያሰራት ጀመር ከዛም በኋላ ገዳም ውስጥ ጭንቅ የሆኑ ስራዎችን ያሰሯት ጀመር የመነኮሳቱን ቤት ጠርጋ ተሸክማ ወስዳ ከገዳም ውጪ አውጥታ ትጥላለች:ያም የተወለደው ልጅ አድጎ እዛው መነኮሰ 40 አመትም ከተፈጸመ በኋላ ቅድስት እንባመሪና 3ቀን ታማ አረፈች:ከዛም የገዳሙ መነኮሳት ደውል ደውለው ተሰበሰቡ ሊገንዟትም ፈልገው ልብሷን ሲያዎልቁት ሴት ሆና ሲያገኟት እጅግ አዝነው አበ ምኔቱን አስጠሩት:አበ ምኔቱም የተፈጠረውን አይቶ እጅግ አዝኖ አለቀሰ ያለበደሏ የሰጣትን ቅኖና እና የተናገራትን ተግሳጽ እያሰበ አምሪሮ ያለቅስ ጀመር:ከዛም ያን የልጅቷን አባት አስጠርቶ የሆነውን ሁሉ ነገረው ከዛም በድኗን ተሸክመው አቤቱ ይቅር በለኝ እያሉ ዋሉ ማምሻውን ላይ የቅድስት እንባመሪና አስክሬን "እግዚአብሄር ይቅር ይበላቹ" ሲላቸው አውርደዋት በታላቅ ክብር ከስጋዋም ተባርከው ቀበሯት ከመቃብሯም እጅግ ብዙ የሆነ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተደረጉ ለእግዚአብሄር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚች ጻድቅ ጸሎት ይማረን:የቅድስት እንባመሪና በረከት አይለየን አሜን.......ቸር ያቆየን!!!!!
ምንጭ መጽሃፈ ስንክሳር ነሃሴ 15


የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፤ (ምሳ10:6)





እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።
ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።
ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም። >>ማቴ10:40-42
በሐዋርያት ሥራም እንደምናነበው የመጀመርያዎቹ ክርስቲያኖች በኢየሩሳሌም ከሐዋርያት ጋር በነበሩበት ጊዜ ጥሪት ቅሪታቸውን፣ ርስት ጉልታቸውን እየሸጡ እያመጡ ለ...ሐዋርያት ያስረክቡ ነበር /ሐዋ.2፡45-46/፡፡ በፍቅር ሆነውም በአንድነት ይመገቡት ነበር፡፡ በኋላ ግን ምእመናን እየበዙ ስለ ሄዱ ክርስቲያኖቹ ጌታ ሞትን ድል አድርጐ በተነሣበት ዕለት በዕለተ-ሰንበት፣ የሃይማኖት አርበኞች ወንድሞቻቸው ሳይፈሩ እና ሳያፍሩ በክርስቶስ ያላቸውን እምነት መስክረው በአላውያን ሸንጐ የተሰየፉበትን ዕለት መታሰብያ በሚያከብሩበት ዕለት ሁሉ ቤቱ ያፈራውን እያመጣ ከጸሎቱ ፍጻሜ በኋላ በቤ/ክ. ገረገራ ውስጥና በየምእመኑ ቤት እየተሰበሰቡ ከጸሎተ ቅዳሴ በኋላ የአንድነት ማዕድ ይሳተፉ ነበር፡፡ ይኸው ክርስቲያናዊ ትውፊት ቀስ በቀስ መልኩን እየለወጠ ሄዶ ዛሬ በሌሎች የክርስቲያን ዓለማት በወረቀት ላይ ብቻ ሰፍሮ “ነበር”ን ይዞ ቀርቷል፡፡ በእኛ በኢ/ያ ግን እስከ አሁን ድረስ ይሠራበታል፡፡ በተለይ በቤ/ክ. ዐውደ ምሕረት ሲደረግ በቤት ከሚቆረጠው ጮማ ይልቅ ይጣፍጣል፤ ይስማማል፤ ረድኤትም አለው፡፡ በፍቅር በእግዚአብሔር ስም የሚደረግ ነው፡፡ በዚሁ ማዕድ ደሀ ሀብታም ተብሎ አይለይም፡፡ ምእመናኑ የአንድ ክርስቶስ አባል መሆናቸውን የሚገልጽ ምሥጢር አዘል ትምህርትም አለው /1ቆሮ.11፡18-22/፡፡ ስለዚህ በጌታ፣ በእመቤታችን፣ በመላእክት፣ በቅዱሳንና በሰማዕታት ስም በዓላቸው በሚከበርበት ዕለት ድግስ ተደግሶ ደሀ ሀብታም ሳይባል ብድራትም ሳይሻ ሁሉንም ተጠርቶ ይጋብዛል፡፡ ዝክር (መታሰብያም) ይባላል፡፡

በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።
ያገለግሉት ዘንድ የእግዚአብሔርንም ስም ይወድዱ ዘንድ ባሪያዎቹም ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚጠጉትንም መጻተኞች፥ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን ቃል ኪዳኔንም የሚይዙትን ሁሉ፥ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤>>
(ኢሳ56:4-7)

1 comment:

  1. EGIZIHABERE KEZIH YEBELTE TIBEB ENA MASTEWALUN YEGLATESLEN KALE HIWOTE YASEMALEN E/R YISTLEN

    ReplyDelete