ክርስቲያናዊ
ሥነምግባር
አጠቃላይ
ፈተና
‹‹ንዌጥን
በረድኤተ እግዚአብሔር››
1. ከአስርቱ
ትዕዛዛት ይመደባል
ሀ/ ህገ-ልቡና
ለ/ አትስረቅ
ሐ/ የሚያስታርቁ
ብፁዓን ናቸው
መ/ ሁሉም
2. እግዚአብሔር
ከሥራው ሁሉ ስላረፈ ይህንን ቀን ቀደሰው………………….
ሀ/ ቀዳሚውን
ሰንበት
ለ/ የመጀመሪያውን
ቀን
ሐ/ እሁድን
ዕለት
3. የእግዚአብሔርን
ስም በከንቱ መጥራት ነው
ሀ/ በዓለማዊ
ዘፈን የእግዚአብሔርን ስም መጥራት
ለ/ ያለምክንያት
መጥራት
ሐ/ በአምልኮ
ጣዖት
መ/ በሐሳዊ
ትንቢት
ሠ/ ሁሉም
4. የሐሰት
አባት ተብሏል በመጽሐፍ ቅዱስ
ሀ/ ይሁዳ ለ/ ዴማስ ሐ/
ዲያብሎስ
መ/ አርዮስ
5. ከሚከተሉት
አንዱ ሐሰተኛ ምስክር ነው
ሀ/ ሐሳውያን
ነቢያት
ለ/ አርዮስ
ሐ/ መናፍቃን
መ/ ሁሉም
6. ይህ ሕግ
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ከእግዚአብሔር ያገኘው ሕግ ነው
ሀ/ የቤተመንግስት
ሕግ
ለ/ የፍታብሔር
ሕግ
ሐ/ ኢ.ጽሑፋዊ
ሕግ
መ/ ሁሉም
7. ጽሑፋዊ
ሕግ በመባል ይታወቃል
ሀ/ የብሉይ
ሕግ (አሥርቱ ትዕዛዛት)
ለ/ የሐዲስ
ሕግ (ስድስቱ ቃላተ ወንጌል)
ሐ/ ሕገ-ልቡና
፣ ሕገ- ህሊና
መ/ ሀ
ና ለ
8. የሚሰርቅ
ሰው ምክንያቱ ………………………….. ነው፡፡
ሀ/ የእምነት
(ሃይማኖት) አለመኖር
ለ/ እግዚአብሔርን
አለመፍራት
ሐ/ ስግብግብነት፣
ድኅነት፣ ልምድ
መ/ ሁሉም
ሠ/ ለ
ና ሐ
9. ጌታችን ትምህርቱን (አንቀጸ ብፁዓንን) ለምን
በተራራ ላይ አስተማረ
ሀ/ የቀድሞ
ህግ በተራራ ስለተሰጠ ያንን ሕግ የሰጠሁት እኔ ነኝ ሲል
ለ/ የክብሩን
ነገር ሊገልጽ
ሐ/ ተራራ
ከፍ እንዲል እነሱም ልባቸው ከፍ እንዲል በምድራዊ ነገር እንዳይታለሉ
መ/ ሁሉም
ሠ/ መልስ
የለም
10. የብፁዓን አዋጆች ብዛት ሲዘረዘር……………………
ሀ/ ስድስት ለ/ አሥር ሐ/
ሦስት
መ/ ዘጠኝ
11. አንቀጸ ብፁዓን የተባለው የትምህርት ክፍል የሚከተሉትን
ያካትታል
ሀ/ ምፅዋት፣
ጾም፣ ጸሎት
ለ/ ሕግጋተ
ወንጌል
ሐ/ የብፁአን
አዋጆች
መ/ ጠቃሚ
ሕጎች
ሠ/ ሐ
ና ለ
ረ/ ሁሉም
12. ‹‹የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው መጽናናትን ያገኛሉ›› (ማቴ 5፡4) የሚለው ምን ለማለት ነው?
ሀ/ ስለ
ኀጢዓት እያሰቡ ማዘን
ለ/ ስለ
ባልንጀራ ኀጢዓት እያሰቡ ማዘን
ሐ/ በሥጋ
ስለሞተ ሰው እያሰቡ ማዘን
መ/ ስለ
ምድራዊ ሀብትና ስልጣን መጥፋት ማዘን
ሠ/ ሀ
ና ለ ረ/ ሁሉም
13. ‹‹ፅድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው ይጠግባሉና›› ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ/ ፀሎትን
የሚናፍቁ
ለ/ ቃሉን
መስማት የሚናፍቁ
ሐ/ ወደ
እግዚአብሔር ቤት መሔድ የሚናፍቅ
መ/ ንስሐ
ለመግባት የሚናፍቅ
ሠ/ ሁሉም
ረ/ መልስ
የለም
14. ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚውሉ የእግዚአብሔር ሀልዎት መገለጫ የሚሆኑ የጽድቅ
ሥራዎች ………………… ናቸው
ሀ/ ጾም፣
ጸሎት፣ ምጽዋት
ለ/ ፈሪሃ
እግዚአብሔር ፣ ሃይማኖት፣ ተስፋ
ሐ/ ቅድስና፣
ንጽሕና፣ ፍቅር
መ/ ሀ
ና ለ ሠ/ ሁሉም
15. ከሰይጣን ፈተና ለመውጣትና ድል ለመንሳት……….ማድረግ ያስፈልጋል
ሀ/ ዘወትር
ተግቶ ከልብ መጸለይ (ማቴ 26፡41)
ለ/ ፈቃደ
እግዚአብሔር መገዛት (ያዕ 4፡7)
ሐ/ ነቅቶ፣
ተግቶና፣ ታጥቆ መቆም (1ጴጥ 5፡7)
መ/ ልማዳዊ፣
ስሜታዊ ኀጢዓትን በቶሎ መሠረዝ
ሠ/ ሀ
ና ለ ረ/ ሁሉም
16. ኀጢዓት
በአራት ይከፈላል እነሱም…………………………
ሀ/ ጥንተ
አብሶ
ለ/ የግል
ኀጢዓት
ሐ/ የጋራ
ኀጢዓት
መ/ ሥርየት
ያለውና ፣ ይቅርታ የሌለው
ሠ/ ሀ
ና መ ረ/ ሁሉም
17. …………………………… ሰዎችን
የሚመለከቱ የጽድቅ ሥራዎች ናቸው፡፡
ሀ/ ጥበብ፣
ንቃት፣ ትህትና፣ ትዕግስተኝነት
ለ/ ገርነት
(ደግነት)፣ አስተዋይነት፣ ጽጉዕነት (ጽናት)
ሐ/ ሰላማዊነት፣
ልግስና፣ እውነተኛነት
መ/ ልበ
ሰፊነት፣ ደስተኛነት፣ ታማኝነት
ሠ/ ጨዋነት፣
ህዳጌ በቀል (ይቅርባይነት) ፣ አማኝነት
ረ/ መ
ና ሠ ሰ/ ሁሉም ሸ/ ሀ ና ሐ
18. ኀጢዓት ………………………… ነው
ሀ/ አለመታዘዝ
ለ/ አመጽ
ሐ/ በጎ
ነገርን አውቆ አለመስራ ነው
መ/ ሁሉም
ሠ/ ሀ ና ለ ረ/ መልሱ የለም
19. ጽድቅ ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ/ በፍጹም
መንፈሳዊ ሕይወት መኖር
ለ/ በሰይጣን
ላይ መሰልጠን (ድል መንሳት)
ሐ/ በእግዚአብሔር
ምስጋና ጸንቶ መኖር
መ/ በእምነት
ጸንቶ መኖር
ሠ/ ሀ
ና ሐ ረ/ ሁሉም
20. የአመንዝራነት ሕይወት ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ/ ሴሰኝነት ለ/ የአምልኮተ ጣዖት
ሐ/ ዝሙት መ/ መልሱ የለም
21. ሐሰት የሚፈጸምበት መንገድ ነው
ሀ/ የተሳሳተ
ፊርማ ለ/ ጽሑፍ ሐ/ አንደበት
መ/ ሁሉም
ረ/ መልሱ የለም
22.
ሰው በሐሰት የሚመሰክረው ከሚከተሉት በየትኛው ምክንያት ነው?
ሀ/ በይሉኝታ ለ/
በዘረኝነትና በጥቅም ሐ/ መጽሐፋዊ ስለሆነ
መ/ ሁሉም ሠ/ ሀ ና ለ
23. አታመንዝር የሚለው ሕግ የተሰጠበት ዓላማ ነው
ሀ/ በዋጋ
ስለተገዛን፣ በሥጋችን እግዚአብሔርን ማክበር ስላለብን
ለ/ አመንዝራነት
እንሰሳዊ ፀባይ ስለሆነ
ሐ/ አዕምሯችን
እንድንጠብቅ
መ/ አመንዝራነት
የክርስቲያኖች ግብር ስለሆነ
ሠ/ መልሱ
የለም
ረ/ ከ
‹‹መ›› በቀር ሁሉም
24. የአመንዝራነት መንስኤዎች ናቸው
ሀ/ መጠጥና
ምንዝር ጌጥ ለ/ ጾምና ጸሎት ማብዛት
ሐ/ ፓርቲ፣
ጭፈራ፣ ዘፈን መ/ ሁሉም
ሠ/ ሀ
ና ለ
25. ‹‹ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እናንተ ሚስቶች ጠጉርን
በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ›› 1ጰጥ 3፡3 ‹‹በውጭ የሆነ የማይገባ ሽልማት የተባለ ምንድን
ነው?››
ሀ/ ቅንድብን
መሸለምና የአፍንጫ ጌጥ፣ ፀጉር ቀለም
ለ/ ከመጠን
በላይ የሆነ ጌጣጌጥና ጥፍር ቀለም
ሐ/ ኢ-ክርስቲያናዊ
የሆነ ንቅሳት
መ/ ሁሉም ሠ/ መልሱ የለም ረ/ ለ ና ሐ
26. በህገ-ወጥ የዝሙት ሥራ (አመንዝራነት) ክቡር
የሆነ ሥጋውን የሚያረክስ ሁሉ
ሀ/ በሃይማኖት
ሕግ ይጠየቃል
ለ/ በፍትሐ
እግዚአብሔር ይመረመራል
ሐ/ ለህግ
አጥፊዎች የተወሰነው ቅጣት ይጠብቀዋል
መ/ ሀ
ና ለ ሠ/ ሁሉም ረ/ መልሱ የለም
27. አመንዝራነት የሚያስከትለው ጉዳት………………… ነው
ሀ/ ሞትና
ጋህነል እሳት
ለ/ መርከብና
መዋረድ
ሐ/ ባርነትና
የአካል፣ የአእምሮ ድክመት
መ/ መልሱ
የለም ሠ/ ሀ ና ለ ረ/ ሁሉም
28. ሰው አትስረቅ የሚለውን ሕግ ተላልፎ ከ …………………………… ይሰርቃል
ሀ/ ከራሱ
ይሰርቃል (ኅሊናን በመሸጥ) ሐ/ ከእናትና ከአባት
ለ/ ከባልንጀራው
ከእግዚአብሔር መ/ ከድኃው
ሠ/ ለ
ና ሐ ረ/ ሁሉም
29. የሰው ልጅ እንዳይሰረቅበት ሊንከባከባቸውና ሊጠብቃቸው
የሚገቡ ሦስት ነገሮች ምንድን ናቸው?
ሀ/ ሕይወት፣
ትዳርና፣ ንብረት
ለ/ ወርቅ፣
ብርና፣ ልብስ
ሐ/ መጽሐፍ፣
ጋዜጣና፣ መጽሔት
መ/ ሀ
ና ለ ሠ/ ሁሉም
30. ሰው የሌሎችን
ሐብትና ንብረት የሚሰርቅበት ጥበብ ነው
ሀ/ በሚዛን፣
በስፍር፣ በልውውጥ ማጭበርበር
ለ/ በመዝረፍ
ሐ/ አራጣና
ጉቦ በመቀበል
መ/ ለሠራተኛ
ከሚገባው በታች በመክፈል
ሠ/ ሀ
ና ሐ
ረ/ ሁሉም
31. ……………………………….. ሰዎች
ትዳርን (ሕይወትን) የሚሰርቅበት ዘዴ ነው
ሀ/ ጥቅማጥቅም
፣ ገንዘብ
ለ/ የተሳሳተ
መረጃ (በመዋሸት)
ሐ/ እምነት
ማጉደል
መ/ ጉልበትና
ስልጣን መከታ በማድረግ
ሠ/ ሀ
ና ለ ረ/ ሁሉም
32. ‹‹ጌታችን
ነፍሳትን የሚሰርቁትን ሌቦች ይላቸዋል››
(ዮሐ
10) ለመሆኑ
እንዴት ይሰርቃሉ?
ሀ/ በኑፋቄ፣
በሐሰት ትምህርትና ትንቢት
ለ/ ወደ
ኀጢዓት መንደር ወደ ሞት መንደር በመውሰድ
ሐ/ በማገትና
በአካል በመስረቅ
መ/ ሀ
ና ለ ረ/ ሁሉም
33. የሰው
ልጅ ከሚሰርቅባቸው ምክንያቶች አንዱ ነው
ሀ/ ከልምድና
ከችግር የተነሣ
ለ/ ከጥጋብና
ውንብድና የተነሣ
ሐ/ ለደባል
ሱስ ተገዥ በመሆን
መ/ በአልጠግብ
ባይነት
ሠ/ ሀ
ና ለ ረ/ ሁሉም
34. ‹‹ስለ ጽድቅ መሰደድ›› …………………ን ያጠቃልላል
ሀ/ ስለጽድቅ
መነቀፍን
ለ/ በውሸት
መታማትን
ሐ/ መጠላትን
መ/ መልሱ
የለም
ሠ/ ሁሉም
35. …………………………….. ከስድስቱ ቃላተ ወነወጌል አይመደብም
ሀ/ የሚምሩ
ብፁዓን ናቸው ይማራሉና
ለ/ የሚያዝኑ
ብፁዓን ናቸው መጽናናትን ያገኛሉና
ሐ/ ታምሜ
ጎበኛችሁኝ
መ/ ተርቤ
አበላችሁኝ
ሠ/ ሁሉም ረ/ ሀ ና ለ
36. ……………………. ከብፁአን አዋጆች አይመደብም
ሀ/ ተርቤ
አብልታችሁኛል
ለ/ የሚያስታርቁ
ብፁዓን ናቸው
ሐ/ ታርዤ
አልብሳችሁኛል
መ/ በመንፈስ
ድሆች ብፁዓን ናቸው
ሠ/ ሁሉም
ይመደባሉ
ረ/ ሀ
ና ሐ
37. አንቀጸ
ብፁአን የተባለውን ትምህርት ማን አስተማረ ይህ ትምህርት ………………. በሚል ስያሜም ይጠራል
ሀ/ ኢየሱስ፣
ህገ ኦሪት
ለ/ ጳውሎስ፣
የተራራው ስብከት
ሐ/ ክርስቶስ፣
አንቀጸ ወንጌል
መ/ ኢየሱስ፣
የተራራው ስብከት
ሠ/ ጴጥሮስ፣
አንቀጸ ብፁዓን
38. ከሚከተሉት አንዱ ትክክል አይደለም
ሀ/ አንቀጸ
ብፁዓን የሐዲስ ኪዳንን ሕግ የያዘነው
ለ/ የሐዲስ
ኪዳን ሕግ የመንፈስ ሕግ ይባላል
ሐ/ የሐዲስ
ኪዳን ሕግ ቱርፋት ይባላል
መ/ የሐዲስ
ኪዳን ሕግ በጻሐፍት የተሰጠ ስለሆነ ለብሉይ ኪዳን ሕግ መፈጸሚያ ነው
ሠ/ የሐዲስ
ኪዳንም ሆነ የብሉይ ኪዳን ሕግ በተራራ ላይ የተሰጠ
39. ‹‹በመንፈስ
ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው›› ማለት
ምን ማለት ነው?
ሀ/ በትህትና
የሚኖሩ
ለ/ ሁሉ
እያላቸው እንደ ሌላቸው የሚሆኑ
ሐ/ ዓለም
ከንቱ መሆኗን ተረድተው ዓለምን የተው
መ/ ሁሉ
የእግዚአብሔርና በእግዚአብሔር መሆኑን አምነው የሚኖሩ
ሠ/ ሀ
ና ለ ረ/ ሁሉም
40. ‹‹የዋሆች ብፁዓን ናቸው›› ማለት …………………….. ነው
ሀ/ መብትን
ለሌላው አሳልፎ መስጠት ለራስ አለመሟገት
ለ/ ቂም በቀል አለመያዝ
ሐ/ በክርስትና
ሕይወታቸው ጠቢብ የሆኑ
መ/ ዓላማ
ያላቸው ሠ/ ሀ ና ለ ረ/ ሁሉም
41. አስርቱን ትዕዛዛት ዘርዝረህ ጻፍ
42. የብፁዓን አዋጆችን ዘርዝር
43. ሕገ-
ወንጌልን (ቃለተ-ወንጌል) የሚባሉትን ዘርዝር
ወስብሐት
ለእግዚአብሔር
መልሲ እንፈልጋለን
ReplyDelete