“ዕፀ
መስቀሉ ከየት መጣ”
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ
ለምንድን ግን የእግዚአብሔ ኃይል ነውና እንደተባለው በቆሮ 1÷18/ ክርስቲያኖች ኃይላችን፣ መመኪያችን፣ ነፍሳችን መዳኛና የምንጸናበት
መስቀል እናምናለን፡፡ ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “እግሮቼ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን” እንዳለም /መዝ 131÷7/ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ውሎ እኛ ለሠራነው ኃጢአት ካሣ እንደሆነ እያሰብን እንሰግድለታለን፡፡ በልባችን፣ በሰውነታችንና
በቤታችን እንስለዋለን፡፡ በአባቶቻችን እንባረክበታለን፡፡ እንደትምህርታችን የድኅነታችን ብርሃን የበራበት ይህ መስቀል የእንጨት
ነው፡፡ እንጨት ከመሆኑ ጋርም አንድም ለመስቀሉ ካላቸው ፍቅር ወይም ታሪክን በተረት ቀርፀው ከማስቀረት ልማዳቸው የተነሣ ይህ መስቀል
ከየት መጣ? ለሚለው አባቶች የሚተርኩት አንድ ታሪክ አለ፡፡ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡