"ማህተብህን
በአንገትህ እሰረው ስትሔድ ይመራሃል
ስትተኛ ይጠብቅሃል"
ምሳ 6÷21
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች በአንገታቸው ላይ ክር
ያስራሉ ለሕፃናቶቻቸውም ክርስትና ሲነሱ ክር ያስሩላቸዋል በሕፃናቱም ሆነ በአዋቂዎቹ ክርስቲያኖች የሚታሰረው ክር በግዕዝ
ማዕተብ በአማርኛ ማተብ ይባላል፡፡ ቃሉ የወጣው ዐተበ ካለው ግዕዛዊ ግሥ ሲሆን ዐተበ ፍቺው አመለከተ ባረከ ማለት ነው፣
ማዕተብ ከዚህ ይወጣል ምልክት ማለት ነው፡፡ ለተጠመቁ ክርስቲያኖች የክር ማዕተብ ለሃይማኖት ምልክትነት ወይም መታወቂያ ከመሆኑ
በፊት በብሉይ ኪዳን ዘመን የሃይማኖት አባቶች ከጣዖት አምላኪዎች ተለይተው የሚታወቁበት ምልክት ነበራቸው፡፡