Thursday, February 5, 2015

የቤተክርስቲያን ታሪክ



የቤተክርስቲያን ታሪክ ፈተና

ትክክለኛውን መልስ ምረጥ

 

  1. ጌታ ወንጌልን በሚያስተምርበት ወቅት ቤተክርስቲያን የሚለውን  ቃል ያወሣ ሰንት ጊዜ  ነው የሚገኘውስ በየትኛው ወንጌል ምእራፍና ቁጥር  ላይ ነው?
  2.  በቤተ ክርስቲያን  ታሪክ የመጀመሪያው ሰማዕት ማን ነው?
  3. ጌታ  በተወለደና በተሰቀለ ጊዜ  የነበሩት የሮማ ቄሳሮች እነማን ናቸው?
  4. የሐዋርያት  ዘመን  የሚባለው ከሰንት  እሰከ  ስንት ነው?
  5. የአስራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል አባት ያዕቆብ ሁለተኛ ስሙ ማን ነው ?
  6. በግዕዝ  ቋንቋ  ቤተ ክርስቲያን  የምንለው  በምስጠራዊና  በዛይቤያዊ  አፈታት  ምኑን ነው?
  7. ቤተ ክርስቲያን የለያየትና የከፋፈለት  የትኛው ጉባኤ ነው ? ምክንያቱሰ  ምንድን ነው ?
  8. የሐዋርያት  ጉባኤ የተደረገው መቼ ነው ? ዓለማውና  ውሣኔውስ ምንድን ነው?
  9. የመሸጋገሪያ ዘመን  የሚባለው ምንድን ንወ? ዘመኑስ  ከሰንት  እሰከ  ስንት ነው?
  10. ለኤፌሶን ጉባኤ  ምክንያት  የሆነው  መናፍቅ ፓትርያርክ ማን ነው ?  በዚህስ ጉባኤ  ላይ ታላቅ ታጋድሎ ያደረገው  ማን ነው ? ያገኘውስ የክብር  ቅጠል  ስም ምንድን ነው?
  11. ዘመነ ሰማዕት የሚባለው ምንድን ነው ? ዘመኑስ ከሰንት  እሰከ ስንተ  ነው?
  12. ከጨዋታ ሜዳ  ተመርጦ የተጣራና ለቤተክርስቲያን  ታላቅ ሐዋርያዊ ተጋድሎ  ያደረገ የቤተክርስቲያን  አባት ማን ነው?
  13. በትሪጃን ዘመን መንግስት ለቤተክርስቲያን የሰማዕታት ተጋድሎ  የፈጸመ  ማን   ነው?
  14. የቤተክርስቲያን  ራስ ማን ነው?
  15. በሮም ንግሥት  ጥርሱ የወለቁና  ጽሕሙ  የተነጨ የቤተክርስቲያን  ሰማዕት ማን ነው?
  16. ቤተ ክርስቲያን  ከአሕዛብ  ነገስታት  ጋር ያጣላት ምክንያት  ምንድን ነው?
  17. ክርስቶስን  ሁለት ባህሪ  በማለት የምታምነው  ቤተክርስቲያን  የትኛው ነው ?
  18.  ወንጌልን  በመጀመሪያ  የሰበከና ክርስትናን የመሰረተ  ሐዋርያ  ማን ነው?
  19. አብያተ ክርስቲናት ተዘግተው  አብያተ ታታት ይከፈቱ ብሎ አዋጅ ያወጣና  ፍጻሜው ያልተሣካለት    የሮማ  ቄሣር ድምጥያኖስ ነው ፡፤ እ/ሐ/ ለምን ?
  20. በቤተ ክርስቲያን  ታሪክ ውስጥ  የመጀመሪያው መናፍቅ አርዮስ ነው፡፡እ/ሐ/ ለምን ?
  21.  ቤተክርስቲያን የሚለው  ቃል የሌለው  ወንጌል የትኛው ነው ?
  22. ሐዋርያት  መንፈስ ቅዱስን   የተቀበሉት  ጌታ ባረገ በስንተኛው ቀን ነው ?

  23.     ድንግል ሆይ አንቺ ከኪሩቤልና ከሱራፌል የበለጠ ክብርት ነሽ የአብን ቃል ለመቀበል የተገባ ሆነሽ ተገኝተሻ ልና ሲል  ያመሰግናት የቤተክርስቲያን አባት የትኛው ነው ? በየትኛው መጽሐፍ ላይ ?
     
  24. የመጀመሪያውን ስደትና  ሰቃይ  በቤተክርስቲያን ላይ  ያወጀው ማን  ነው ?
  25. ቤተክርስቲያን በስደትና  በ  ትኖር  የነበረው እሰከ  ስንተኛው ክፍል ዘመን ነው?

1 comment: