ካለፈዉ የቀጠለ….
እናም ትንቢቶቹ በመሀመድ ወይም በሉተር አልያም ከእነርሱ ወዲህ ለተመሰረተ ሃይማኖት የተነገሩ ናቸዉ ተብሎ እንኳን ቢታሰብ ፍጹም የማይመስል ነገር ነዉ፡፡ምክንያቱም መስራቾቹ እነርሱ እስከሆኑ ድረስ ከመሀመድ ወይም ከሉተር በፊት ሃይማኖት አልነበረም እንዴ ? ተብሎ ቢጠየቅ መልስ አይኖርም፤ምናልባት ላለማመን ተብሎ ሌላ ነገር ካልተነገረ በቀር ማለት ነዉ ወይም በሌላ በኩል ከእነ መሀመድ እና ሉተር በፊት የነበሩ ሐዋያት ቅዱሳን ጻድቃን ሰማእታት በሙሉ እነ ሉተር ዘመን ላይ ስላልደረሱ እነዚህ ሁሉ ሃይማኖት አልነበራቸዉም ማለት ነዉ? ሰዉነታቸዉ እንደ ሽንኩርት በሰይፍ የተቀረደደዉ ፤ በእሳት የተቃጠለዉ ፤ አጥንታቸዉ እየተፈጨ በንፋስ የተበተነዉ ፤ ቆዳቸዉ ተገፎ አቅማዳ እስኪሆን ድረስ ያደረሳቸዉና ያን ሁሉ ሰማእትነት ይከፍሉ የነበረዉ ገና ወደፊት ፍጡር ለሚመሰርተዉ ሃይማኖት ነበር ማለት ነዉ?