Sunday, October 21, 2012

ተዋሕዶ መጠርጠር የሌለባት ሃይማኖት



ትንቢቶች ሁሉ መፈጸማቸዉ ግድ ነዉ፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ህግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለእኔ የተጻፈዉ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል (ሉቃ24፤44) እንዳለ ስለርሱ የተነገሩ ትንቢቶችን በሙሉ እርሱ ፈጽሟቸዋል፤ ነቢያትና ሐዋርያት ስለመጪዉ ጊዜ  የተናገሩትም ትንቢት ቅንጣት ታክል እንኳን ሳትፈጸም አትቀርም፡፡ ስለ ሰዎች እምነትና ክህደት የተነገሩ ትንቢቶች ተፈጽመዋል፡፡እየተፈጸሙም ነዉ ገና ወደ ፊትም ይፈጸማሉ፡፡
ሐዋርያት “በግልጽ በለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በዉሸተኞች  ግብዝነት የተሰጠዉን የ አጋንንትን ትምህርት እያደመጡ ሃይማኖትን ይክዳሉ”  (1ጢሞ4፡1) <<በቅዱሳን ነቢያትም ቀድሞ የተባለዉን ቃል በሐዋርያቶቻችሁም ያገኛችሁትን የጌታንና  የመድሃኒታችንን ትዕዛዝ እንድታስቡ በሁለቱ  እያሳሰብኳችሁ ቅን ልቡናችሁን አነቃለሁ፡፡በመጨረሻዉ ዘመን እንደራሳቸዉ ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ>>(2ጴጥ3፤2) የሚሉት ትንቢቶች ሁሉ የግድ መፈጸም አለባቸዉ፡፡<<ክህደት  ትጠፋለች ሃይማኖት ግን ለዘላዓለሙ ትጸናለች>>ሲራ40፤12




 
ይህቺ ሃይማኖት ደግሞ ሌላ አይደለችም ነቢያት<< በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመችዉን መንገድ ጠይቁ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእርሷም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ  እነርሱ ግን አንሄድባትም አሉ>>(ኤር6፤16) እያሉ የተነበዩላት ሐዋርያት << ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ>>( ይሁ1፡3) <<አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት >>ኤፌ4፤5  እያሉ የሰበኳት ተዋሕዶ ሃይማኖት ናት፡፡ እነዚህ ጥቅሶች እነ መሀመድ እስልምናን በ622ዓ.ም  እነ  ሉተር ፕሮቴሰታንተኒዚም በ16ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ለመሰረቱት የእምነት ድርጂት ሊነገር አይችልም፡፡ አመተ ምህረት አንድ ተብሎ መጠር ሲጀምር ወይም ከዛሬ 2000 ዘመናት በፊት የአዲሰ ኪዳን ክርስትና በክርስቶስ እንደተመሰረተ ሁሉ በ 570 ዓ.ም የተወለደዉ መሐመድም እስልምናን በ622ዓ.ም ነዉ የመሰረተዉ፡፡ ከዚያም ከመካ ወደ መዲና ተሰዶ ብዙ ተከታዮችን ካፍራ በዋላ ነዉ ሃይማኖቱን በሃይልና በሰይፍ ያስፋፋዉ፡፡(ዘ ዎርልድ ቡክ ኦፍ ኢንሳይክሎፒዲያ ቮሉዩም 13 ገጽ 533) እንዲሁም በቀለሙም የታሪክ ተምህርት የተማርነዉና የምናነበዉ ይህንኑ ነዉ፡፡ እስልምናን የመሰረተዉ መሀመድ መሆኑን ራሱ ቁራኑም ይነግረናል ፡፡ በሱረቱ አል አንዓም 6፤163 ላይ “ እኔም የሙስሊሞች የመጀመሪያ ነኝ “”እንዲሁም በሱረቱ አልዙመር 39፤12 ላይ “” የሙስሊሞችም መጀመሪያ እነድሆን ታዘዝሁ”” ብሎ መሐመድ ስለራሱ እንደተናገረ ቁራኑ በግልጽ ያስቀምጠዋል፡፡
(ይቀጥላል….)

No comments:

Post a Comment