Sunday, November 4, 2012

የሎዶባር ምርኮ








የእስራኤል ልጆች ከጠላት ጋር በጦር ቀጠና ዉስጥ ሲፋለሙ የ አምስት አምቱ የዮናታን ልጅ ሜንፊቦስ በተፋፋምዉ የጦር ክልል ዉስጥ ነበረ፡፡
ሜንፊቦስ ማለት የቃሉ ትርጉም ወድቆ የተሰበረ ማለት ነዉ፡፡የህጻኑን ነፍስ ለማትረፍ ሞገዚት በትከሻዋ አዝላዉ ካደጋዉ ቀጠና ለማምለጥ በፍጠነት ስትሮጥ ሜንፊቦስቴ ክፉኛ ወደቀ ሽባም ሆነ፡፡

በሰ ው ትከሻ ያለ ስጋ ለባሹን ክንድ ያደረገ ሁሉ ይወድቃል ፤ ይሰበርማል። የማይወድቅ  በእግዚአብሔር የተደገፈ ብቻ ነዉ፡፡መጽሃፍ “ በሰዉ የሚታመን ስጋ ለባሹን ክንዱ የሚያደርግ ልቡን ከእግዚአብሔር የሚመልስ ሰዉ እረጉም ነዉ”(ኤር 17፤5 )ይላል፡፡ በሰዉ ትከሻ መኖር ምን ይሰራል ? በሰዉ መመካትስ ምን ይጠቅማል? የተሸከሙንስ ሰዎች ትከሻቸዉ የ እግዚአብሔርን ያህል ተመችቶልን ይሆን? በጭራሸ እንኳንስ ሊመች የተደገፍናቸዉ ሰዎች ጭራሽ ለስብራትና ለከፋ ሃዘን የዳረጉን ብዙዎች ነን፡፡  ለመሆኑ ሰዉ ምንድን ነዉ ? ነቢዩ ኢሳይያስ  “ለመሆኑ ሰዉ ምንድን ነዉ? እስትንፋሱ በ አፍንጫዉ ያለበትን ሰዉ ተዉት “ (ኢሳ 2፤22) ይላል፡፡


እነ  ኢያሱ  በእምነት የኢያሪኮን ግንብ አፈረሱ “ ግንቡ በ እምነት ወደቀ “ እንጂ እነሱ አልወደቁም  አልተሰበሩም ፡፡(ዕብ11፤30) ታዲያ እንዴት ሰዉ ነገ በሚወድቅ ሰዉ ይደገፋል ? እንዴት ሰዉ ነገ የሚለወጥ ጊዜን መከታ ያደርጋል? ባናዉከዉ እንጂ “ ከሰማይ በታች ሁሉ ከንቱ ነዉ” ምንም የሚያስመካ ነገር የለም ፡፡እናም እንደ ቆመ የሚመስለዉ እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ፡፡1ኛ ቆሮ10፤12
ህጻኑ ሜንፊቦሰቴ ግን እግዚአብሄር አንድ ቀን ደርሶለት ዳዊት በስልጣን ኮርቻ ላይ በወጣ ጊዜ ለሚያሳድደዉ ለሳዖል ቤተሰብ ምህረት ሊያደርግ ተነሳ ፡፡(2ኛ ሳሙ9፡1) ዛሬ እንደ ዳዊት አይነት ንጉስ መሪ በመብራትስ ተፈልጎ ይገኝ ይሆን? አለም ምህረት በሌላቸዉ እርቅን በማይሰሙ እና በማያሰተዉሉ ሰዎች ተሞልታለች። ብቻ የሰዉ ጭካኔ በዝቷል ፡፡እኛም እንኳን እንደ አቅማችነ የቤት ሰራተኞቻችን ላይ ጨካኞች ነን፡፡ስንቶቻችን እንሆን ሰራተኞቻችንን በሰንበት ኢንኳን ቤተክርስቲያን ሄዳ አስቀድሳ እና ተባርካ እነድትመጣ የምንፈቅድላት? እግዚአብሔርም” ሰራተኞቻችሁን ሁሉ ታስጨንቃላችሁ ””እስኪለን ድረስ ነፍሳችን በቃሉ ስትመዘን ከገለባም ቀለን የተገኘን ንንቶቻችን ንን? (ኢሳ58፤3)
ዛሬ ደግነት ከ እኛ ርቋል፡፡እኔ ስለ አብርሃም ደግነት ሳስብ ብቃቱ ይገርመኛል፡፡እንግዳ ቤቱ ካልመጣ እህል የማይበላ ጻድቅ ሰዉ ነበር፡፡ አሁን ግን የአባቶቹን ፈለግ የረሳ ትዉልድ እየተነሳ ነዉ ፡፡ ዳዊት በደግነቱ ለሳኦል ቤተሰብ ምህረት ሲያደርግ ከሳዖለል ቤተሰብ አንድ ሰዉ ጠፋ ፡፡ ይህ  የጠፋዉ ሰዉ ሜንፊቦስቴ ነበር፡፡ለካስ አለም ለከተማ ዉበት አይመቹም የምትላቸዉን ሰባራ እና ለብቻ የምታጉርበት ሎዶባር የሚባል ግንብ ወይም ቅጥር ዉስጥ ሜንፊቦስቴም ታጉሯል ፤ ሎዶባር የገባ ደግሞ አይወጣም፡፡
ዳዊት ግን ሜንፊቦስቴን ከሎዶባር ሊያወጣ ገባ፡፡ ሲባ የሚባለዉን ሰዉ ሲጠይቀዉ በ አሚር ልጅ በማኪር ቤት አለ ብሎ ህጻኑ ያለበትን ቤት ጠቆመዉ፡፡ሲሄድም አገኘዉ ፡፡ህጻኑም አለ   “ የሞተ ዉሻ ወደ ምመስል ባሪያህ እንዴት ተመለከትህ “ ብሎ እጅ ነሳ  ዳዊትም “ ከገበታየ እንጀራ ትበላለህ  አትፍራ” የገባ የማይዎጣበትን ሎዶባርን መዝጊያዋን ስባብሮ ነጻ አወጣዉ፡፡ በቤተ መንግስትም አኖረዉ፡ ፡
ይህ ምሳሌ ነበር  ዳዊት የክርሰቶስ ፤ ሜንፊቦስቴ ያዳም  ፤ሎዶባር የሲኦል ፤እንጀራ የስጋ ወደሙ ፤ቤተመንግስት የገነት መንግስተሰማያት ምሳሌ ናቸዉ፡፡ ሎዶባር የገባ እንደማይወጣ ሲዖልም የገባ አይወጣም ፡፡ይሁን እንጂ ዳዊት ንጉስ ነዉና ሎዶባር ገብቶ ሜንፊቦስቴን ማርኮ ማዉጣቱ ኢየሱስ ክርስቶስም የባህሪይ አምላክ ነዉና በሓጢያት የተሰበረዉን አዳምን የሲዖልን መዝጊያ ሰብሮ ነጻ አዉጥቶታል ፡፡ከዚያም በቤተመንግስት ወደምትመስለዉ ገነት አሰገብቶታል፡፡
እግዚአብሔር የወደቁትን አይተዉም የተሰበሩትን አይረሳም፡፡በ እግዚአብሔር ከተደገፍን የማንሻገረዉ ወንዝ የለም፡፡በችግርና በስደት በረሀብና በጦርነት የተሰበረችዋን ኢትዮጵያን በንስሃ ከተመለሰች እግዚአብሔር ይተዋታል የሚል ቅንጣት ታህል ጥርጥር የለኝም፡፡ዛሬ ሕይወት  ሲዖል የሆነችበት ሰዉ ብዙ ነዉ፡፡የሎዶባር ምርኮና ስቃይ  በዝቶብናል፤ ግን ልባችንን ሰብረን ከተመለስን እንደ ዳዊት እግዚአብሔር የወደቅንበት ድረስ ይመጣል፡፡ በማኪር ቤት ድረስ ይፈልገናል፡፡ ለዚህ እንዲአበቃን እሰቲ ወደ እግዚአብሄር በንስሐ  እንመለስና እንጸልይ፡፡

No comments:

Post a Comment