ቀድሞ ከእግዚአብሔር ለቅዱሳን አንድ
ጊዜ የተሰጣቸውና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ጸንታ የተመሠረተችው በሰማዕታትም ደም ያሸበረቀችው ቅዱስት ቤተክርስቲያን ከተመሠረተችበት
ዕለት አንስቶ በውጊያ ላይ ብትሆንም እንኳ ሁል ጊዜ ድል ታደርጋለች እንጂ ተሸንፋ አታውቅም ታላቁ የቤተ ክርስቲያን አባት ቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ ስለቤተክርስቲያን በገለጸበት ድርሳኑ ‹‹ሰውን በትታገልና በትዋጋ ታሸንፈዋለህ ወይም ያሸንፍሃል ቤተክርስቲያንን
ግን ለማሸነፍ አይቻልም፤ ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ ትዋጋለች ተሸንፋ ግን አታውቅም ዲያብሎስ ዝናሩን አራገፈ፣ ቀስቱን ጨረሰ ቤተክርስቲያንን
ግን አልጎዳትም›› ብሏል፡፡
ርቱዐነ አንደበት የሆኑ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን
መናፍቃንን በቃልም ሆነ በጽሑፍ ሲዋጉ ኖረዋል የአበውን አሰረ ፍኖት የተከተለ ይህ ትውልድም የአባቶችን አደራ ተቀብሎ በግብር ሊመስላቸው
ይገባል፡፡