Monday, November 9, 2015

መልዕክቶች እንሁን ሁሉም የሚያነበን


    ክርስቲያን ለመሆን መንገድ ላይ ለቆምነው
    ጉዞ ሳንጀምር ሁሉን ለፈጸምነው
    "ሳይገባን" ምስጢሩ የክርስቲያን ግብሩ
    ፊደልም ሳንቆጥር ሳንማር ጠንቅቀን
    መጻሕፍትንና ኃይሉንም ላላወቅን...
    እዚህኛው ጥልቅ እዚያኛው ዘው ላልን
    ንብ መሆንን ትተን እንደ እርጎ ዝንብ ለሆን
    ራሳችን ከሳሽ እኛው ዳኛ ሆነን
    በፍርድ አደባባይ ሁሉን ለወነጀልን
    ከውስጣችን ጠፍቶ ትህትናና ትዕግስት
    ማክበር መከባበር ከቶ ለተሳነን
    እንደ ባለ አእምሮ በማስተዋል ሆነን
    ቆም እንበልና ጉዞውን እንጀምር
    በፊደልም ሳይሆን በትርጉም እንኑር
    ፀጋችን እናብዛ በቃሉ ተሞልተን
    መልዕክቶች እንሁን ሁሉም የሚያነበን
    ተፃፈ፣ጥቅምት፪፯፣፪፼፰


No comments:

Post a Comment