Monday, November 9, 2015

ፍቅሩ ግድ ይለናል

                                                                        +ፍቅሩ ግድ ይለናል+
                                                                   ===============
        

    ይህንን ስለቆረጥን
    ከእንግዲህ በኋላ
    በቀሪው ጊዜያችን
    በተሰጠን ዘመን...
    በሕይወት ያለነው
    በጌታ የምንኖር
    ጥምቀቱን ለመምሰል
    አብረን ከተጠመቅን
    ሞቱንም ለመምሰል


    አብረነው ከሞትን
    ደግሞም በትንሳኤው
    አብረን ከተነሳን
    ለሞተልን አምላክ
    ከብሮ ላስከበረን
    በደሙ ለገዛን
    ነፍሱንም ለሰጠን
    አንገቱንም ደፍቶ
    ቀና ላደረገን
    ፍቅሩ ግድ ይለናል
    ስለርሱ እንድንኖር
    እንደ ብርቱ ጻድቅ
    እንደ መባጽዮን
    መከራ ስቅለቱን
    በልቡ እንደሳለው
    በቀረለት ጊዜ
    ለጌታ እንደኖረው
    ዓለምን በመናቅ
    ቆርጠን እንነሳ
    አሁን እንሰብስብ
    የጽድቅን አዝመራ
    (፪ቆሮ፩ ፬፣፮ ፤ሮሜ፮፣፭)
    ተፃፈ፣ጥቅምት፪፯፣፪፼፰





No comments:

Post a Comment