ንፅህት ብርሕት የሆነችው ጥንታዊትና ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለ2000 ዓመታት ፈተናን ያሳለፈች መከራን የተጋፈጠች ሃይማኖት ናት።
ሀ) ከውስጥ በቢፅ ሐሳውያን ወይም በሐሰተኞች ወንድሞች ለቤተክርስቲያን ክብር የቆሙ በመምሰል የራሳቸውን ጥቅምየሚያስከብሩ እንደ ይሁዳ በገንዘብ የሰከሩ ገንዘብ ከተከፈላቸው ዲያንሎስንም ቢሆን የሚያመልኩ
ሌሎቹም ውሻ በበላበት ይጮሃል እንዲሉ ከዚህ ጥቅም የተነካኩ የፈጠራቸውን ጌታ ሳይቀር የሸጡ ...
ለመንጋው ግድ የሌላቸው እውነትን በሐሰት መጋረጃ ሸፍነው ብርሃን በወጣበት ዘመን በጨለማ የሚኖሩ የቤተክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች የስሜት ክርስቲያኖች
ለ) እንዲሁም በቤቱ እየኖሩ እውነቱን ወደ ማወቅ የማይደርሱ የስሜት ክርስቲያኖች
ሐ) እግዚአብሔርን እያገለገሉ የሚያገለግሉትን እግዚአብሔር ግን በባሕሪው የማያውቁት አፍኒንና ፊንሐሶች
መ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የአባቶችን ትምህርት የሚያጣጥሉ የተዋህዶን አስተምህሮ የሚያቃልሉ
ዶግማዋን ለማፍረስ ቀኖናዋን ለመጣስ ከእውነተኞች አገልጋዮች ጋር በመመሳሰል የሚንቀሳቀሱ የጥፋት መልዕክተኞች እነዚህ
1) ተረፈ አርዮሳውያን ምስጢረ ሥላሤን ያልተረዱ የነገረ መለኮት ትምህርት ያልተገለጸላቸው ይልቁንም የወልድን አምላክነት የሚጠራጠሩ
2) ተረፈ ንስጥሮሳውያን የድንግል ማርያም ክብር ያልገባቸው ለማመስገንም ሆነ ስሟን ለመጥራት የማይፈልጉ
3) ተረፈ መቅዶንዮሳውያን መንፈስ ቅዱስን ያቃለሉ ቤተክርስቲያን መታደስ አለባት ብለው የተነሱ
በውጭ...
ሀ) መናፍቃን ተረፈ ሉተራውያን የአምልኮት መልክ ያላቸው ኃይሉን ግን የካዱ
ለ) አሕዛብ ኢ -አማንያን የወልድን አምላክነት የካዱ በመግደልና በማሳደድ ጽድቅ ይገኛል ብለው የሚያምኑ
ሐ) አላውያን ነገሥታት አብያተ ክርስቲያናትን ያዘጉ ቅዱሳንን ያሳደዱ
መ) ህዝብ ያስጨነቁ የሀገርን ቅርስ ያወደሙ ፈረኦናውያን መሪዎች
እነዚህ ሁሉ የገሀነም ደጆች በክርስቶስ ደም የተመሰረተችውን ቤተክርስቲያን አይችሏትም::
በቤተክርስቲያናችን መሰረታዊ ጉዳይ ላይ እንደ አንድ ልብ እየመከርን እንደ አንድ ቃል እየተናገርን በነገር ሁሉ ክርስቲያናዊ ህብረታችንን እግዚአብሔር እየጠበቀልን ብዙ ፈተናዎችን ማለፋችን ይታወቃል። በአሁኑ ሰአትም ቤተክርስቲያንን እየበረዘ ያለው የተሃድሶ ወይም የምንፍቅና ትምህርት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ ድንገት የመጣ ሳይሆን በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን በተደረገው የተኅድሶ እንቅስቃሴ ወቅት ተጀምሮ በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በሉተርና ግብረ አበሮቹ ተጠናክሮ ቤተክርስቲያንን እያወከ ከእኛ ዘመን የደረሰ ከመሆኑም ባሻገር የመውጊያ ቀስት ስልትና ጥበባቸውን በየጊዜው የሚቀያይሩ ከመሆናቸው የተነሳ ምንም እንኳን እኛን መስለው በሚንቀሳቀሱ ነገር ግን የበግ ለምድ በለበሱ ተኩላዎች ተመሳስለው ቢመጡም እኛ ግን በተማርንበት ነገር ፀንተን በመቆም ሃይማኖታችን እንጠብቅ። አባቶቻችን ካስተማሩን ትምህርት የተለየ እና የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ያልሆነን ትምህርት በማጋለጥና በክርስቲያናዊ አካሄድ በመቃወም ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በህብረት እንድንጠብቅ አሳስባለሁ::
የቤተ ክርስቲያን አምላክ ይጠብቀን::
No comments:
Post a Comment