Monday, November 9, 2015

ቅዱሳን ምን አሉ

                                                            +ቅዱሳን ምን አሉ+
                                                          ==============


    እስኪ ጠይቋቸው ቅዱሳን ምን አሉ
    ምግባራቸው ቀንቶ በጎውን የሰሩ
    እምነታቸው ጸንቶ ተዋሕዶ ርትዕት
    ንጽሕት ና ብርህት ቅድስት ናት ያሉ
    ክብራቸውን ትተው ከዓለም የተለዩ...
    በዱር በሸንተረር በየፍርክታው
    በግበበ ምድር በዋሻ የኖሩ


    ርሃብና ጥሙን ቁርና ሐሩሩን
    የአጋንንቱን ጸብ ችለው ተቋቁመው
    ድንጋይ ተንተርሰው ዳዋ ቅጠል ለብሰው
    ስለ ክርስቶስ ፍቅር ጥዑሙን የናቁ
    እውነትን መስክረው ስለ እውነት የኖሩ
    መናፍቅ ተነስቶ ክህደቱን ሲዘራ
    የአባቶችን ርስት ሊወስድ ሲነሳ
    የቀድሞውን ድንበር የጥንቱን ምልክት
    ላድስ ነው በማለት ወሰኑን ሲያፈርሰው
    እስኪ ጠይቋቸው ሰማዕታት ምን አሉ
    ስለ አምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር
    በአናብስት ጉርጓድ በግፍ የተጣሉ
    በሰይፍ በስለት የተቆራረጡ
    በአራዊት ተበልተው በእሳት ተቃጥለው
    መስዋዕት የሆኑት በድንጋይ ተወግረው
    እስኪ እንጠይቃቸው ምን ይሆን መልሳቸው
    ቅጥራችን አፍርሰው ባድማ ሊያደርጉ
    የበግ ለምድ ለብሰው በጉን ተመሳስለው
    በንጹሁ እርሻ ላይ እንክርዳድ ሲዘሩ
    ከእኛ የቀደሙት በእምነት የጸኑት
    ዛሬ ይጠየቁ ይመስክሩ እውነቱን
    ተፃፈ፣ጥቅምት፪፯፣፪፼፰


No comments:

Post a Comment