Thursday, February 27, 2014
Tuesday, February 25, 2014
‹‹ዓብይ ጾም››
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅድስ አሐዱ አምላክ አሜን
‹‹ዓብይ ጾም››
ጾም የቃሉ መሠረታዊ
ትርጉም መታቀብ መከልከል ማለት ነው በቤተክርስቲያናችን እምነትና ትምህርት ጾም ማለት የሰው ልጅ ሕይወቱን ለሰጠው የሕይወትን መመሪያ
ላዘጋጅለት ፈጣሪ እየታዘዘ ኃጢዓትን ለማስተሰረይ የምኞት ፍትወትን ኃይል አድክሞ ሥጋ ለነባቢት ነፍስ ትገዛለት ዘንድ በሕግ በታወቁ
ጊዜያት ከመብል መጠጥ በመከልከልና የመንፈስ ብርታት ማግኛ የጥበብ መንገድ ነው::
ጾም ጸሎት ምጽዋት
የተያያዙ የሥነ ምግባር ሰንሰለቶች ስለሆኑ በተግባር ተጠብቀው ሲተረጎሙ የእኛንም ሕይወት ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኛሉ በመጽሐፍ
ቅዱስ ተጽፎ እንደምናነበው አበው ማንኛውንም ሥራ ለመሥራት ሲያስቡና ሲያቅዱ፣ ሲጀምሩና ሲፈጽሙ በጾም በጸሎት ነው፡፡
Friday, February 21, 2014
ሶምሶንንና ዴማስን የማረከችው ደሊላ
ሕይወታቸውን
እስከ ሞት ድረስ ለወደዳቸው ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰጥተው ፀበ-አጋንንቱን ታግሰው ፈተናንና እንቅፋትን በጥበብና በብዙ ትዕግስት በእግዚአብሔር
አጋዥነት አልፈው አርአያና ምሳሌ በመሆን ክርስትናን ሕይወት አድርገው በንጽሕናና በቅድስና የኖሩት አበው፣ ክርስትና የመሰናክል
ሩጫ ከመሆኑም ባሻገር፣ ክርስትና ተዘናግተው እንዳይኖሩ ተኝተው እንዳያድሩ ተደላድለው እንዳይቀመጡ ዕረፍት የሚነሳ ሰላምን የሚያውክ
ሰይጣን ዲያብሎስን ያክል ክፉ ጠላትና የማይታረቁት ባለጋራ ያለበት ሕይወት እንደሆነ ያስተምሩናል በመሆኑም ክርስቲያን ዘወትር በመጠንና
በጥንቃቄ መኖር ይገባዋል፡፡ ‹‹ባለጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ በዙሪያችሁ ይዞራል እንዲል የጽድቅ ሐዋርያ
ጳውሎስ›› (1ጴጥ 5፡7)
Tuesday, February 18, 2014
‹‹ቃል ኪዳኔን ልጠብቅልሽ በራሴ ማልሁልሽ››
‹‹መሃልኩ ለኪ
በርዕስየ በከመ ኢይሔሱ ኪዳንየ››
‹‹ቃል ኪዳኔን
ልጠብቅልሽ በራሴ ማልሁልሽ››
(ስንክሳር ዘየካቲት ፣ ተአ/ማር ገጽ
76)
እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከፈጠረ በኋላ ቦታ ለይቶ ህግ ሠርቶ አኖረው
ህጉን ከተላለፈ ቅጣት እንደሚያገኘው አእምሮውን ዳኛ አድርጎ ሠየመለት ይሁን እንጂ ሰው የባሕርይው ደካማነት ይህን ፈተና እንዲያልፍ
አላስቻለውም ካለመቻሉም የተነሳ ምክረ ከይሲን (የሰይጣን ምክር) ሰምቶ ዕፀ በለስን በልቶ ከፈጣሪው ተጣልቶ ከገነት ወጥቶ መንጸፈ
ደይን (የጉስቁልና ቦታ) ወደቀ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ (በሥጋ ሞት ላይ የነፍስ ሞት) በርደተ መቃብር ርደተ ሲኦል (ወደ መቃብር
በመውረዱ ላይ ሲኦል መውረድን) ፈረደበት፡፡
Wednesday, February 12, 2014
Tuesday, February 11, 2014
‹‹መዳን በሌላ በማንም የለም›› (ሐዋ 4፡12)
‹‹የሉተራውያን ስህተት በሊቃውንት
አስተምህሮ ሲገለጥ ሲጋለጥ›› ክልፍ 3
ይህንን ኃይለ ቃል የተናገረው በዕድሜ በጸጋና በመንፈሳዊ አገልግሎት
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሸመገለው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ሲሆን መጽንኢ (አጽናኝ)፣ መስተፈስሒ (አስደሳች)፣ መንጽሒ (የሚያነፃ)፣
መስተሰርይ (የሚያስተሰርይ)፣ እና ከሳቲ (ገላጭ) የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላ በዕለቱ በዙሪያው ተሰብስበው ለነበሩት
ለቤተ አይሁድ በ72 ቋንቋ ወንጌልን በመስበክ 3000 ነፍሳትን አሳመነ፡፡ በዘጠኝ ሰዓትም ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወደ
ቤተመቅደስ ሲሄዱ በቤተመቅደስ በር ላይ ተቀምጦ ሲለምን የነበረውን አንድ አንካሳ ሰው ወደ እኛ ትኩር ብለህ ተመልከት ብሎ በናዝሬት
በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ በማለት ፈወሰው፡
Monday, February 10, 2014
‹‹የክርስቶስ የማስታረቅ አገልግሎት በሞቱ ተፈጽሟል››
(ክፍል ሦስት)
‹‹የክርስቶስ
የማስታረቅ አገልግሎት በሞቱ ተፈጽሟል››
ቅዱሳን ሐዋርያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክነት በስፋት አስተምረዋል
መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር መሆኑን በሚገባ ይነግረናል ቅዱሳን አባቶቻችን ሊቃውንትና ቅዱሳት መጻሕፍትም ክርስቶስ ፈራጅ
ጌታ እውነተኛ አምላክ መሆኑን አመስጥረው ይነግሩናል፡፡ ታድያ ጌታ መድኅኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ፈጣሬ ዓለማት ፈራጅ ሕያው
አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እርሱን በሚመለከት ለምን የምልጃ ቃላት ሊነገሩለት ቻሉ? ይህን መሠረታዊ
ጥያቄ በዚህ ጽሑፍ አጠር አድርገን እንመልሳለን፡፡
Monday, February 3, 2014
ፈራጅ ወይስ አማላጅ?
ክፍል 2
‹‹የሉተራውያን ስህተት በሊቃውንት አስተምህሮ ሲገለጥ ሲጋለጥ››
‹‹የሉተራውያን ስህተት በሊቃውንት አስተምህሮ ሲገለጥ ሲጋለጥ››
ባለፈው ዕትማችን ሉተራውያን
በጽሑፎቻቸውና በቃላቸው ከልባቸው አፍልቀው ‹‹ኢየሱስ በሰማይ ሆኖ ይጸልይልናል፣ አማላጃችን ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል›› ይላሉ
ሃሣባቸው በአጭሩ ሲገለጥ ኢየሱስ አማላጃችን ነው ለማለት መሆኑ ይታወቃል እንግዲህ በቅዱስ መጽሐፉም የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር አባል
በመሆናቸው የራሳቸውን ስሜትና የፈጠራ አስተያየት በመጨመር ኢየሱስ አማላጅ፣ ጠበቃ ነው የሚሉ ጽሑፎችን አስገብተው ይገኛሉ ካቶሊኮች
የተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን መጻሕፍት በኑፋቄ መርዝ ትምህርታቸው ለመበከል እንደሞከሩ፣ ሉተራውያንም ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት፣
ፈጣሪነት ባለመረዳት ኢየሱስ አማላጃችን ነው በማለት ጌታችን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን ትክክልነትና አምላክነት ይክዳሉ፡፡
በተለያየ ጊዜ ባሳተሟቸው በራሪ ወረቀቶችና መጻሕፍት ስህተት እየጻፉ ይገኛሉ ከነዚህም መካከል የተወሰኑትን ጠቅሰን በቤክርስቲያናችን
ሊቃውንት አስተምህሮ ሲገለጥ ምን እንደሚመስል አይተናል፣ ዛሬም ቀጣዩን እነሆ፡-
Subscribe to:
Posts (Atom)