Tuesday, September 29, 2015

በምስጢረ ጥምቀት ምስጢረ ሥላሴ ተገለጠ

በምስጢረ ጥምቀት ምስጢረ ሥላሴ ተገለጠ


በቅዱሳት መጻሕፍት በጉልህ ተመዝግቦ እንደምናገኘው አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ 30 ዓመቱ  ድረስ ለእናቱ ለ ቅድስት ድንግል ማርያም እየታዘዛትና እየተላላከ አደገ ( ሉቃ 2፣) በ30 ዓመቱ ግን ሰማይና ምድር በመሀል እጆቹ የተያዙ አምላክ እንደ ተራ ሰዎች በፈለገ ሄኖን በማዕዶት ዮርዳኖስ ለመጠመቅ ሄደ በጥንተ ፍጥረት የእግዚአብሔር መንፈስ በውሀ ላይ ሰፎ ነበር        (ዘፍ፩፣፪) በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ከሶስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ከባህርይ አባቱ ከአብ ከባህርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ የተካከለ እሱ መድሐኔዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በባህረ ዮርዳኖስ በመጠመቅ ለውኃ የበለጠ ኃይል ሰጠው :የባርነት ደብዳቤ በዮርዳኖስ ነበርና ዕዳ በደላችን  ይደመስስ ዘንድ በባህረ ዮርዳኖስ በትህትና በባሪያው እጅ ይጠመቅ ዘንድ ወደ ውሃው ገባ፡፡

በዚያች የተቀደሰች ዕለት የተፈጸመን ድርጊት ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ እንዲህ በማለት ይተርከዋል : መድኃኒታችን  ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ቅዱስ የሐንስ ያጠምቅ ወደ ነበረበት ሥፍራ ደረሰ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ጥምቀትን በዕደ ዮሐንስ ጠመቁ ነበር :ጌታችን መምህረ ትህትና ነውና ተራ ይጠብቅ ዘንድ ከላ ተሰለፈ  የሚቀድመው የሌለ እርሱ ተጠማቂዎችን አስቀደሞ ከላ ተሰለፈ  ;ፊተኛ የሌለው ፊተኛ የሆነ እርሱ ከፊት ለፊቱ ፍጡራንን አስቀድሞ ተራ ይጠበቅ ዘንድ ተሰለፈ  ሁሉም ከተጠመቁ በላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሊጠመቅ ተዘጋጀ ቅዱስ ዮሐንስ ግን ትህትናን ከእናቱ ከቅድስት ኤልሳቤጥና ከአባቱ ከካህኑ ከዘካሪያስ ተምሯልና ባየው ጊዜ የመድኃኔዓለም ትህትና አስደነቀው  እየፈራና እየራደ እጅ እየነሳ አንተ በእኔ እጅ ትጠመቅ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል ብሎ በትህትና ተናገረ ጌታችን መድኃኔዓለም ግን ጽድቅን ሁሉ እፈጽም ዘንድ ይገባልና ፍቀድልኝ ብሎ ባሪያውን አበረታታ፣ መጻህፍትና የነቢያት ቃል ይፈጸም ዘንድ ግድ ነውና እነሆኝ አጥምቀኝ አለው ቅዱሱም የፈጣሪውን ፍቃድ መፈጸም አለበትና ተያይዘው ወደ ማዕከለ ዮርዳኖስ ገቡ የዮርዳኖስ ውሃ ግን በእሳት እንዳፈሉት ፈላ ኃያሉን አምላክ በማዕከሏ መያዝ ተስኗት ዮርዳኖስ ወደ ላና ወደ ፊት በማለት ማዕበል እነዳናወጣት  ባህር ተናወጠች አስቀድሞ ቅዱስ ዳዊት በትንቢት እንደተናገረው ባህር ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ላ ተመለሰች’’  እንዲል ዮርዳኖስ ባህር ግዕዙ ፍጥረት እንኳ ለፈጣሪ ያለውን ክብር ለማሳየት ልሽሽ አለ ነገር ግን እንደገና ታዘዘና ቆመ (መዝ113-4) መች በዚህ አበቃና የፍጥረታት መደነቅ መደናገጥ በተራሮችና በኮረብቶችም ቀጠለ እንጂ ተራሮችና ኮረብቶች መድኃኔዓለም ሲመጣ ሲያዩ እናቱን እንዳዬ ሕፃን ልጅ በመቦረቅ ዘለሉ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ‘ ተራሮች  እንደ ኮርማዎች ኮረብቶችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ’’ (መዝ 113-5) በማለት እንደ ዘገበው ምድርም ከያዕቆብ አምላክ ፊት ከጌታ ፊት ተናወጠች በእጆቹ ያያዛትን መሸከም አልቻለችምና ( መዝ113-7) በመሬት ይህ ሁሉ ተአምር ሲፈጸም በሰማይ ደግሞ አስደናቂ ድንቅና በአይን የሚታይ ድርጊት ተፈጸመ፡፡ መድኃኒታችንና ቅዱስ የሐንስ ከዮርዳኖስ ሲወጡ ሰማያት ተከፈቱ፣ የሰማይ ምስጢር ተገለጠ ይኽውም ከፈጠራቸው ፍጥረታት ባለቤት የመድኃኔዓለምን ክብርና ልዕልና አምላክና ጌትነት የሚገልጥ ነበር፤ የአባቶች አባት ጽድቁ አብርሃም በአድባር: ዛፍ ሥር: ነቢያት ኢሳይያስና ሕዝቅኤል በንጉሥ ዙፋን ተቀምጦ ያዩት አንድ አምላክ ሦስት አካላት፣ ሦስት ስም፣ የአብ የወልድ፣የመንፈስ ቅዱስ አኗኗር ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት በፈለገ ዮርዳኖስ ዙሪያ ተገለጠ፡፡
ፈለገ ዮርዳኖስም ከአፍላጋት ሁሉ ታደለች የምስጢራት ጎርፍ ፈሰሰባት ድንቅ የሆነ ሰማያዊ ሥርዓት ታየባት የቅዱሳን ሁሉ አምላክ ሊቀ ቀዳስያን ክርስቶስ ተጠምቆባታልና ተቀደሰች በምስጢረ ጥምቀት ምስጢረ ሥላሴ ተገለጠ፤ አባትም ለልጁ ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነቱን በድምፅ አሰማ ‘’ የምወደው ልጄ ይህ ነውና እርሱን ስሙት’’ ሲል ለሕዝቡም እውነቱንና ፍቅርን ገለጸ ከሶስቱ አካል አንዱ አካል የሆነው መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ሆኖ በመድኃኒታችን ራስ ላይ ተቀምጦ ታየ፡፡ በመሆኑም እግዚአብሔር በአንድነቱ ሁለትነት፣ በሦስትነቱ አራትነት የሌለበት፤ ነገር ግን በባሕርይ በሕልውና በአገዛዝ፣ በፈቃድ በሥልጣን አንድ አምላክ ሲሆን በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስትነት ያለው መሆኑን አለም ሁሉ አወቀው የጥንታዊትና ሐዋርያዊት ቅድስት ቤተክርስቲያንም የነገረ መለኮት መሠረታዊ ትምህርት ምንጭ የተቀዳው ከዚህ ላይ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል መድኃኔዓለም ክርስቶስ እንደ አብና መንፈስ ቅዱስ የሚመለክና የሚሰገድለት የባሕርይ አምላክ እንጂ ነቢይ፣ አማላጅ፣ፍጡር አለመሆኑን በባሕረ ዮርዳኖስ ከተፈጸመው ሥርዓት ለመረዳት እንችላለን፡፡
ቤተክርስቲያ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ አዳም ልጆች ነፃነት ሲል መድኃኔዓለም የተጠመቀበትን በዓል በየዓመቱ ጥር፲፩ ቀን በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዓት ታከብራለች በዚህ ቀን አምላካችን ክርስቶስ በጥምቀቱ ጥምቀታችንን ባርኮና ቀድሶ የዕዳ ደብዳቤያችንን በመፋቅ ልጅነትን ሰጥቶናል የብርሃን ልብስን አጎናጽፎናል፡፡ በመሆኑም ወንዶች በአርባ ቀን ሴቶች በሰማንያ ቀን ከአብራክ መንፈስ ቅዱስ ከማህፀን ዮርዳኖስ ተወልደን የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆች ሆነናል፡፡ ተመልሰን በባርነት ቀንበር አንያዝም ክቡር ሰውነታችን የተቀደሰውን ሥጋችንን በዝሙት ፣ በርኩሰት፣ በጥል፣ በክርክር፣ የኃጢዓት ጎተራ ማድረግ የለብንም ፡፡
ባሕታዊውና ሐዋርያው ዮሐንስ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ማዕዶተ ዮርዳኖስ ከመምጣቱ በፊት ለቤተ አይሁድ መንግስተ ሰማያት ቀርባለች ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቷልና ከርኩሰታችሁ ተቀደሱ አባጣውና ጎርባጣው ይስተካከል ከክፋትና ከተንኮልም ራቁ ከኃጢዓታችሁም ተመለሱ ንስሐም ግቡ በማለት እንዳስተማረ እኛም የእግዚአብሔር ስም የተጻፈባቸን ጽላት የያዙትን የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበን በተቀደሱ ሥፍራዎች በመገኘት አበው የባረኩትን ጠበል እንረጫለን በመሆኑም ሐዋርያው ጳውሎስ ‘’ የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀደሰ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁመም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ግዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠብቁ’’ እንዲል ( 1 ተሰ 3፣23) ነውራችንን እየተውን ኃጢአታችንን እየተናዘዝን በፍቅር በመሆን በዓሉን ልንዘክረው ይገባል፡፡

No comments:

Post a Comment