Saturday, January 30, 2016

ሞት የተሸነፈብሽ ሆይ ሞት እንዴት አገኘሽ


    ሞት የተሸነፈብሽ ሆይ ሞት እንዴት አገኘሽ
    =========================

                         " ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ
                            ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ
    ትርጉም ፦ ሞትማ ለሚሞት ሰው ይገባዋል
    የማርያም ሞት ግን እጅግ ያስገርማል"

    የመላዕክት እህት ሆይ መውጊያው የተሰበረ ሞት እንዴት በአንቺ ላይ በረታ፤
    የአዳም ተስፋው የአብርሃም ርስቱ ክብርት ሆይ ፍላፃው የተቆረጠ ሞት እንዴት በአንቺ ላይ ኃይል አገኘ፤
    የአመፃ መዝገባችንን የገለበጠውን ብርቱ የወለድሽ ሆይ ደካማው እንዴት ወደ አንቺ መጣ፤...
    በብርሃን ላይ ስልጣን ያለውን ብርሃንን የወለድሽ ሆይ የጨለማው አበጋዝ እንዴት አንቺን ደፈረ፤
    የፍቅርና የትህትና መምህርት ሆይ የጥልና የትዕቢት አባት ሞት እንዴት አገኘሽ፤
    ርግበ-ኖህ የተባልሽ የድኅነታችን ምክንያት ሆይ ከሐዲው ቁራ ወደ አንቺ ለምን መጣ፤
    መዓዛሽ የተወደደ የናርዶስ ቀጺመታት ሽቱ ሆይ ክፋ ጠረንና መጥፎ ሽታ ያለው እንዴት አንቺን ቀረበ፤
    የነቢያትን ናፍቆት የወለድሽ የኢሳይያስ ድንግል የሕዝቅኤል የተዘጋ ምስራቅ በር ሆይ በምን በኩል የተናቀው አገኘሽ፤
    የዮሐንስ እናት ደግሞም የጥበቡ ምንጭ ሆይ የማትሞቺ እንዴት አንቺ ሞትሽ፤
    ሐዘናችንን ያራቅሽ ሙኃዘ ፍስሐ የተባልሽ የደስታችን መፍሰሻ ሆይ የሐዘናችን ምክንያት መላከ ሞት አንቺን ይቀርብ ዘንድ እንዴት እድል አገኘ፤
    ሞት የተሸነፈብሽ አንቺ ሆይ ከቶ ሞት እንዴት ወደ አንቺ መጣ፤


    ጥር ፳፩ ቀን፳፻፰ ዓ.ም

የሰሞኑ የሚዲያዎች ግርግር


ሰሞኑን የተለያዩ ድረ ገፆችን ካጨናነቁት አርእስተ ጉዳዮች መካከል አንዱ “አቡነ” መልከጼዴቅ በኦርጋንና በተመሳሳይ ዘመናዊ የሙዚቃ መሣርያዎች ስለ መዘመር የተናገሩት ንግግር ነው። ንግግራቸውን ተከትለው ለብዙ ዓመታት ደብቀውት የነበረውን አቋማቸውን በርካታ የኾኑ “የአቡኑ” ደቀ መዛሙርት ጉዳዩን ወደ ቤተ ክርስቲያን አሾልከው ለማስገባት ምእመናንም ሀሳባቸውን እንዲቀበሏቸው በብዙ በመጣር ላይ ይገኛሉ።“አቡነ” መልከጼዴቅ ሃሳባቸው ተቀባይነት እንዲያገኝ ርእሰ ጉዳዩን ከሁለት የቅርብ ጊዜ ታሪካዊ ሁኔታ ጋር ለማቆራኘት ሞክረዋል። አንደኛው በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት የተተረጎመው መጽሐፍ ቅዱስ ኦርጋን ወይም አርጋኖን የሚለውን ቃል መጠቀሙን፣ ሁለተኛም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመነ ፕትርክና ዘመን ኦርጋን በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ መዋሉን በአጽንኦት ገልጠዋል። ሁለቱንም ሃሳበቸውን በማስተዋል ስንመለከተው ሚዛን የማይደፉ ሆነው እናገኛቸዋለን።

Friday, January 29, 2016

አስተርእዮ ማርያም (ጊዜ እረፍታ ለማርያም )





    ጥር 21 በዚህች ዕለት ስለሰው ልጅ አንድ ጊዜ አይደለም ሰባት ጊዜ ልሙት ያለች ለፍጥረት ሁሉ የምታዝን ከርህራዬዋ ብዛት የተጠማን ውሻ በወርቅ ጫማዋ ያጠጣች አባቶች ቢወዷት ሶልያና ያሏት ተወዳጅ እናታች...ን ድንግል ማርያም በ 64 ትአመቷ ዐረፈች። ነፍሷ ከስጋዋ የምትለይበት ጊዜ ሲደርስ ሐዋርያትና ድንግል ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ለመኗት፤ እጁዋን በላያቸው ዘርግታ ባረከቻቸው። በዚያን ጊዜ ጌታችን ንፅህይት ነፍሷን ከስጋዋ ለይቶ ወሰደ። እንደሌላው ፍጥረት ሁሉ የድንግልን ሞት ተናግረን ዝም የምንል አይደለም ይልቁንም ሞትን ድል እንዳረገው እንደ ልጇ እርሷም መነሳቷን እንመሰክራለን እንጂ ። "ማርያም ሞተኪ ይመስል ከብካበ" እውነት ነው የድንግል ማርያም ዕረፍት በመልአክት በብዙ ዝማሬ የታጀበ ሥለነበር ደስታ ሠርግ ነው የሚመሥለው። የሕይወት የድህነት አለኝታ የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በጸሎቷም ከክፉ ነገር ይጠብቀን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

Wednesday, January 27, 2016

ሊቀ ሰማዕታት ፀሐይ ዘልዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ፡-


                                 
    ሊቀ ሰማዕታት ፀሐይ ዘልዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ፡-
     ጊዮርጊስ ማለት ‹‹ኮከብ ብሩህ፣ ፀሐይ›› ማለት ነው፡፡ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀገሩ ፍልስጤም ልዩ ስሟ ልዳ ሲሆን የተወለደው በ277 ዓ.ም ጥር 20 ቀን ነው፡፡ አባቱ ዞሮንቶስ ወይም አንስጣስዮስ የ...ልዳ መኳንንት ሆኖ ተሹሞ ይኖር ነበር፤ እናቱ ቴዎብስታ ወይም አቅሌስያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሌላ ማርታና እስያ የሚባሉ ሁለት ሴት ልጆችን ወልዳለች፡፡

Thursday, January 14, 2016

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብር


    የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብር
    ============================
     ስለ እመቤታችን ክብር በመጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈውን የእመቤታችንን ንግግር መጥቀስ በቂ ነው እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል። ሉቃ 1፥48
     በመጽሐፍ ቅዱስ እመቤታችንን ስለማክብር የተፃፉ ብዙ ጥቅሶች አሉ፣ ለምሳሌ በእመቤታችን እናት ዕድሜ የነበረችዋ ቅድት ኤልሳቤጥ እመቤታችንን “የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።” ሉቃ 1፥ 43-44 አለቻት እዚህ ላይ የሚያስደንቀን ነገር ኤልሳቤጥ የእመቤታችንን ሰላምታ በሰማች ጊዜ “መንፈስ ቅዱስ ሞላባት” የሚለው ሐረግ ነው። የእመቤታችንን ድምፅ መስማት ብቻ ኤልሳቤጥን መንፈስ ቅዱስ እንዲሞላባት አደረጋት።

ሐራጥቃ ተሃድሶን ልብ የሰጡ ሦስቱ ጽንፎች


“መቀበል፣መደገፍ እና መከተል! ሐራጥቃ ተሃድሶን ልብ የሰጡ ሦስቱ ጽንፎች” ውድ አንባብያን በዕረፍት አልባ ቀንና እንቅልፋ የለሽ ሌሊት ልንታገለው ስለሚገባው ሐራጥቃ ተሃድሶ(ፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ) በአንክሮ መነጋገሩ ጊዜው የሚጠይቀው ጉዳይ ነው፡፡ ሐራጥቃ ተሃድሶ ሕልም አይደለም! ቅዠትም አይደለም! እንደ ምድር ወገብ የሃሳብ መሥመርም አይደለም! ምዕናብም አይደለም! ሰዎች አልያም ማኅበራት የፈጠሩት ስምም አይደለም! ይልቁንም በዓይን የሚታይ፣በጆሮ የሚሰማና እና በእጅ የሚዳሰስ የዐደባባይ እውነት እንጂ፡፡ ዛሬ ለዚህ እኩይ አካል እዚህ መድረስ ጉልህ አስተዋጽኦ ስላደረጉና ለሐራጥቃ ተሃድሶ ግብዓት ስለሆኑት ሦስት ነገሮች መጻፍ አስገደደኝ፡፡ እነዚህ ሦስት ኩነቶች መቀበል፣መደገፍ እና መከተል ናቸው፡፡

Wednesday, January 13, 2016

የሰርጎ ገብ መናፍቃን/ሃራ ጥቃ መናፍቃን/ ዋና ዋና መለያ ባሕርያት/ምልክቶች (ክፍል ሁለት)




ክፍል ሁለት
የሰርጎ ገብ መናፍቃን/ሃራ ጥቃ መናፍቃን/ ዋና ዋና መለያ ባሕርያት/ምልክቶች

እነዚህ ክፉ ሠራተኞች በእውነተኞቹ መምህራንና ዘማርያን ስም የሚያታልሉ አገልጋይ ነን ባዮች የዲያብሎስ መልእክተኞች መሆናቸውንም በንግግራቸውና በጽሑፋቸው አረጋግጠዋል ‹‹እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይ የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ (ራዕ 13፡6) ተብሎ እንደተጻፈ ቤተክርስቲያንን እናድሳለን ብለው የተነሱት እነዚህ ተጠራጣሪዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ኢየሱስ ክርስቶስ አልተሰበከም ብለው በድፍረት ከመናገራቸው ባሻገር ፣ የፈጣሪ ማደሪያ ሁለተኛ ሰማይ የሆነችውን.፣ ሰማይ ዙፋኑ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆነውን አምላክን የወለደችውን ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዲሁም እግዚአብሔር ያከበራቸውን ቅዱሳን መላዕክትን ጻድቃንና ሰማዕታትን በመሳደብ ፣ በሚገባ የጠላት ሰይጣን ማደሪያዎች ታማኝ አገልጋዮቹ መሆናቸውን ገልጠዋል፡፡ ቅዱሳንን ለጆሮ በሚቀፍና በሚዘገንን ስድብ ከአብጠለጠሉ በኋላ ስለራሳቸው ማንነት ሲገልጡ ግን የበቁና የነቁ የፈጣሪን ማንነት ጠንቅቀው ያወቁ እንደሆኑ አድርገው በትዕቢት ይናገራሉ፡፡

የሰርጎ ገብ መናፍቃን/ሃራ ጥቃ መናፍቃን/ ዋና ዋና መለያ ባሕርያት/ምልክቶች (ክፍል አንድ)




ክፍል አንድ

የጽድቅ ሐዋርያ ቅ/ጳውሎስ አንድ ሃይማኖት አንድ ጥምቀት አለ፣ ከሁሉም በላይ የሚሆን በሁሉ የሚሰራ አንድ ጌታ ደግሞ አለ (ኤፌ 4፡9) እንዲል ንጽሕትና ጽድልት፣ ጥንታዊትና ሐዋርያዊት የሆነችው የቀደመችው ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት ከዓለመ መላዕክት እስከ ገነት፣ ከምድር እስከ ሰማይ የፍጥረት ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር የሚመለክባት ብቸኛዋ መንገድ ተዋሕዶ ናት፡፡ ነገር ግን የበጎ ሥራ ጠላት ዲያብሎስ የሰው ልጆችን ወደ ሞት መንገድ ለመውሰድ ዘወትር ስለማያንቀላፋ በእውነተኛዋ ሃይማኖት አንጻር፣ እውነት የመሰሉ ድርጅቶች ፈጥሮ በሽንገላና በጥርጥር በወሰዳቸው የግብር ልጆቹ በመጠቀም አንደበታቸውን አንደበት አድርጎ በእጃቸውም እየጻፈ በክህደት ንግግርና ጽሑፍ እውነተኛይቱን ሃይማኖትና የተቀደሰ ሥርዓቷን በማፋለስ የቀናውን እያጣመመ ትውትን እያጣጣለ በጠላትነት ከተነሳባት ዘመናት ተቆጠሩ፡፡

Tuesday, January 12, 2016

የሰርጎ ገብ መናፍቃን/ሃራ ጥቃ መናፍቃን/ ዋና ዋና መለያ ባሕርያት/ምልክቶች (ክፍል 3)


     


    የሰርጎ ገብ መናፍቃን/ሃራ ጥቃ መናፍቃን/ ዋና ዋና መለያ ባሕርያት/ምልክቶች

    1. ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ስለቅዱሳን መላእክት እንዲሁም ቅዱሳንና ሰማእታት ርእስ አድርገው አያስተምሩም አይሰብኩም።
    2. በስብከቶቻቸው ውስጥ ለ...ምሳሌ ስለ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ስደት ስቅለት ትንሳኤ ወዘተ ሲያስተምሩ ከእርሱ ተለይታ ስለማታውቀው እናቱ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ፈጽሞ አያነሱም።
    3. ስለጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሲያስተምሩ የጌታን ስሙን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ብዙው ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚጠሩት ባለ ይትበሃል አይጠሩትም። በአብዛኛው የሚጠቀሙት በመናፍቃኑ ይትበሃል ብቻ ነው።