Sunday, December 30, 2012

የእግዚአብሔር ወልድ ጥምቀት




ጥምቀት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ ሕዝብና አህዛብን አንድ አደረገ፡ የዕዳ ደብዳቤያችንን ደመሠሠልን፡፡
 «ጥምቀት» የሚለው ቃል ተጠምቀ ተጠመቀ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ቃል በቃል ሲተረጐምም መጠመቅ፣ ውሃ ውስጥ ገብቶ መነከር፣ መዘፈቅ ይሆናል፡፡
ሳምንቱ ዘመነ አስተርእዮ ይባላል፡፡ ስያሜውም ለወሩና ለሳምንቱ የተሠጠበት ምክንያት፡-

THE SEVEN SACRAMENTS



 



           THE SEVEN SACRAMENTS

Ethiopian Orthodox Tewahido Church


DN.CHERINET YIGREM


Sacraments

The Seven Sacraments of our church
The Ethiopian Orthodox Tewahido Church serves the faithful through the seven sacraments. These sacraments are called mysteries because the invisible grace of the Holy Spirit is granted through them.

«ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን ለሰውም በጐ ፈቃድ»











«ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን ለሰውም በጐ ፈቃድ»
ዓለም በኃጢአት ጨለማ ተውጦ፣ ሰውና እግዚአብሔርም ተለያይተው፤ ሰላም ከሰው ልጆች መካከል ጠፍቶ በምትኩ ጥል፤ ክርክር፣ ምንዝር፣ ነፍስ መግደል አምልኮ ባዕድ ሌላውም ኃጢአት በዓለም ላይ ተስፋፍቶ፤ ለአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ያህል እንደኖረ  የቤተክርስቲያን ታሪክ ይነግረናል፡፡

ዓለምን የፈጠረው ተወለደ




ዓለምን የፈጠረው ተወለደ


ጠንካሮች የሃይማኖት አባቶቻችን «እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ በጥፋቱ ወድቆ የነበረውን ዓለም ያዳነበት ጥበቡ ይደንቃል» ይላሉ፡፡ አነጋገሩ አርቆ አራቅቆ ከማሰብ የመነጨ መሆኑን እኛም እረጋ ብለን ስናጤነው እናገኘዋለን፡፡ እርግጥም ዓለማትን የፈጠረ ከረቂቃኑ ፍጡራን አስከ ግዙፋኑ ድረስ በየቦታቸው ያደራጀ፣ አንዱንም ፍጥረት ያለ ምግብ ያልተወው አምላክ በግእዘ ሕፃናት በቤተ ልሔም መወለዱ እጹብ ነው፡፡
በሰማያዊ መንበሩ በዘባነ ኪሩብ እያለ በጎለ እንስሳ በጨርቅ ተጠቅልሎ ተገኘ፡፡ ምንኛ ሰውን ቢወድደው ነው? ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከአብ ድኅረ ዓለም ያለ አባት ከእመቤታችን ሁለት ልደትን ተወለደ፡፡

«ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ»




«ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ»


የጌታችን የመድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት የሰው ልጆች መዳን መሠረት የተጣለበት፣ መላእክት በደስታ የዘመሩበት፣ በጨለማ ለነበረው ዓለም ብርሃነ የወጣበት ዲያብሎስ የተጨነቀበት ሰብአ ሰገል በደስታ የዘለሉበት ሰማያዊው አምላክ ስለ ሰው ልጆች ሰው ሆኖ ተወልዶ ከእናቱ ጡት ወተትን እየለመነ ያለቀሰበት ታላቅ እለት ነው፡፡
ስለዚህ በዓል ምንነት ትርጉምና ምስጢር ለመናገር ጥልቅ መንፈሳዋነትና ብሩህ የሆነ ውሳጣዊ ዓይን ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህም ስለ ልደቱ መናገር በእኛ ከሚጻፍ ይልቅ እንዲህ ያለውን ብሩህ ዓይን ገንዘብ ያደረጉ ቅዱሳን አባቶች የተናገሩትና የጻፉት ቢቀርብ እንደሚሻል ግለጽ ነው፡፡ ስለዚህም ቀጥለን ቅዱስ ኤፍሬም እና ቅዱስ ያሬድ የጌታችንን ልደት አስመልክተው የተናገሩትን /ያዜሙትን/ መርጠናል፡፡

Friday, December 7, 2012

ፃዲቁ አቡነ አረጋዊ ዘሮም









የፃዲቁ የአቡነ አረጋዊ አባት ይስሐቅ እናቱም እድና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የተባረከ ልጅ ሰጣቸው እሱም አቡነ አረጋዊ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት፣ ህገ ኦሪትን ትምህርተ ነቢያትንና ቅዱሳት መፃህፍትን እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ እሱም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየፀና እየበረታ አደገ፡፡
ሚስት ያገባ ዘንድ አጩለት፡፡ ፃዲቁ አባታችን አቡነ ዘሚካኤል/አረጋዊ/ ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡ ከብዙ ዘመን በኋላ ከሮም ወደ ግሪክ ሀገር አባ ጳኩሚስ የሚኖርበት ደውናስ ወደምትባል ገዳም የምንኩስናን ልብስ ይለብስ ዘንድ ሄደ፡፡ አባ ጳኩሚስንም አገኘው፡፡ አባ ጳኩሚስም ልጄ ሆይ አንተ የንጉስ ልጅ እንደ መሆንህ መጠን

Wednesday, December 5, 2012

ኢትዮጵያዊው ፃዲቅ አቡነ ሀብተማርያም






ወር በገባ በ 26 በቤተክርስቲያናችን ታስበው ከሚውሉት እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳን ከገባላቸውን ከሰጣቸው ቅዱሳን አባቶቻችን አንዱ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ፃዲቅ አቡነ ሀብተማርያም ይገኛሉ ታዲያ ጻድቁ ፃዲቅ አቡነ ሀብተማርያም ማን ናቸው ? ምን ቃል ኪዳን ተሰጣቸው? እናም ያደረጉትን ተጋድሎ በጥቂቱ እንመልከት
አምስቱን መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን የተሰጠው ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም የነበረበት ዘመን 1486 ዓ.ም ንጉስ እስክንድር በነገሰበት ጊዜ
ነው፡፡ አባቱ ፍሬ ቡሩክ እናቱ ዮስቴና ይባላሉ፡፡ ፍሬ ቡሩክና ዮስቴና በህገ እግዚአብሔር በሃይማኖት በትሩፋት በምግባር ፀንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡
የፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም እናት ቅድስት ዮስቴና ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያምን ከመውለዷ በፊት ሰው ሁሉ ዓለሙን ቢገዛ ነፍሱን ካጣ ምን ይጠቅመዋል የሚለውን የወንጌል ቃል ተረድታ መንና ወደ በረሃ ሄደች፡፡ በበረሃ ውስጥም ከሰው ተለይቶ የሚኖር ባህታዊ በዋሻ ውስጥ አገኘች፣ የመጣሁት ለምነና ነው ጌታ በወንጌሉ እርፍን ይዞ ወደ ኋላ የሚያርስ የለም እንዳለ ወደ ዓለም አልመለሰም አለችው፡፡ ሉቃ 9፣62
ይህም ባህታዊ ምናኔ ምንኩስና ለአንቺ አልተፈቀደልሽም ከህጋዊው ባልሽ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ እርሱም ለዓለም ሁሉ ይተርፋል በፀሎቱም ብዙዎቹን ይጠቅማል እንደ መልአክትም ክንፈ ጸጋ ተሰጥቶታል በማለት ነገራት፡፡
ቅድስት ዮስቴናም ከአረጋዊ ባህታዊ ይህን ነገር ሰምታ አደነቀች የፈጣሪዬ ፈቃድ ከሆነ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ ጥቂት ጊዜያት ከቆየች በኋላ ግንቦት 26 ቀን ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ተወለደ፡፡ በአባቱና በእናቱ ቤት ታላቅ ደስታ ሆነ 40 ቀን በሞላው ጊዜ በኦሪትና በሉቃስ ወንጌል እንደተፃፈ በእግዚአብሔር ፊት ያቆሙት ዘንድ ወደ ቤተክርስቲያን ወሰዱት በተጠመቀ ዕለትም ሀብተማርያም ተብሎ ተሰየመ፡፡
ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም በፈሪሃ እግዚአብሔር በትምህርት አደገ፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን ካህናቱ በቤተክርስቲያን ምህላ ሲያደርሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" እያሉ ሲፀልዩ ሰምቶ በልቡናው ይህች ፀሎት በጣም ጥሩና መልካም ፀሎት ናት አለ በዚህ ፀሎት ከዓለም አሳችነት ከገሃነም እሳት እንድንባት ዘንድ አውቃለሁ የንስሐ መንገድ ናት ብሎ ተናገረ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አባታችን አቡነ ሀብተማርያም በዚህች ፀሎት ተጠምዶ በጾምና በፀሎት በስደት የሚኖር ሆነ፡፡
አባቱ ፍሬ ብሩክ አቡነ ሀብተማርያምን የበግ ጠባቂ አደረገው እግዚአብሔር ግን በኋላ ለብዙዎች ስውራን ቅዱሳንና በዓለም ለሚኖሩ ምዕመናን በጎች ጠባቂ ያደርገው ዘንድ ወዶ መርጦታልና ያ ቀን እስኪደርስ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይጠብቀው ነበር፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያም ከአባቱ አጠገብ ተኝቶ ሳለ ‹‹ሀብተማርያም ሀብተማርያም›› የሚል ድምጽ በሌሊት ከሰማይ መጣ፡፡ አባቱ በአጠገቡ ተኝቶ ስለነበረ የጠራው መስሎት አባቴ ሆይ አለሁ ሲል መለሰ ከዚህ በፊት ቃል ከሰማይ ጠርቶት አያውቅም ነበርና እንደ ሳሙኤል ጌታዬ ባሪያህ ይሰማሃል ተናገር አለ፡፡ ሳሙ3፤3 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አናገረው፡፡
ከዚህም በኋላ አባቱ ከሀገሪቱ ታላላቅ ሰዎች አንዷን እጮኛ አጨለትና ታገባለህ አለው አባታችን አቡነ ሀብተማርያም አባቴ ሆይ እኔ ራሴን ለክርስቶስ በድንግልና ለመኖር አጭቻለሁ ተራክቦዬም ቃለ ወንጌልን መስማት እንጂ ሌላ አይደለምና ለምን እንዲህ ትለኛለህ አለ፡፡ አባቱም ያለ አቡነ ሀብተማርያም ፈቃድ ሙሽራይቱን ለማምጣት ሄደ፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያምም ሀገር ጥሎ ለመሰደድ ከቤት ተደብቆ ወጣ፡፡ መንፈስ ቅዱስም በመብረቅ አምሳል አባቱን ገሰፀው በዚህ ድንጋጤ ምክንያት የስጋ አባቱ ከዚህ ኃላፊ ዓለም አረፈ፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያምም የአባቱን እረፍት ሳያይ አፋር ወደምትባል ሀገር ወደ አሰቦት አቡነ ሳሙኤል ገዳም ሄደ አባ ሳሙኤል ከሚባሉ ደግ መነኩሴ ቦታ ገብቶ ኖረ፡፡ በዚያም ገዳም ውሃ በመቅዳት እንጨት በመስበር፣ ልብስ በማጠብ እህል በመፍጨት አበው መነኮሳትን ሲያገለግል ኖረ፡፡ በአባታችን ላይ መነኮሳት ተቆጥተው ሲነሱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በገሃድ ተገልፃ ትገስፃቸውም ነበር፡፡
በዚህ አገልግሎት ላይ ሳለ ገዳሙ ካለበት ተራራ ላይ ወደ በረሃ ወርዶ ውሃ ቀድቶ ተሸክሞ ሲመለስ ውሃውን በእንስራ እንደተሸከመ እግሩን አደናቀፈው፡፡ የቀዳው ውሃ ሊደፋበትና እንስራውም ሊሰበርበት ሲል ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አድነኝ ትወድቅ ዘንድ አትተዋት ብሎ ፀለየ፡፡ ይህን ብሎ በተናገረ ጊዜ የውሃዋ እንስራ ሳትወድቅ ቆመች እጅም ሳይነካት ተመልሳ በትከሻው ላይ ተቀመጠች አባ ሳሙኤልም ይከተሉት ነበርና ይህን ጽኑ ተዓምር አይተው አደነቁ፡፡ ማር 9፡23
እንዲሁ ከዕለታት በአንድ ቀን በሌሊት መብራት ለአባ ሳሙኤል እያበራ ሳለ መብራቱ ከእጁ ወድቆ ጠፋ፡፡ ስለ መምህሩ ስለ አባ ሳሙኤል ቁጣ፣ ፍራቻ፣ ታላቅ ድንጋጤ ደንግጦ ፈጥኖ ባነሳው ጊዜ በእግዚአብሔር ተዓምር ራሱ በራ፡፡ አባ ሳሙኤልም ይህን ተዓምራት አይተው የዚህ ቅዱስ ልጅ የዓለም ሁሉ የጥበብ መብራት ይሆናል ሲሉ ትንቢት ተናገሩ፡፡ በዚህችም ገዳም 12 ዓመት ከትህትና ጋር እየታዘዘ ቤተክርስቲያንን እያገለገለ ኖረ፡፡
ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ከአባ ሳሙኤል ገዳም ወጥቶ እለ አድባር ወደ ተባለ ገዳም ሄደ፡፡ ከአባ መልኬጼዴቅ እጅ የምንኩስናን ስርዓት ተቀበለ፡፡ ከዚያም በመቀጠል በጥልቅ ባህር ገብቶ 150 መዝሙረ ዳዊትና አራቱን ወንጌልና ሌሎች የፀሎት መጽሐፍትን እየፀለየ አምስት መቶ ጊዜ ይሰግድ ነበር፡፡ እህል መብላትን ትቶ እንደ በረሃ ዋልያ ቅጠል መብላት ጀመረ፡፡ አርባ ቀን የሚጾምበት ጊዜና ሰማንያ ቀንም የሚጾምበት ቀን ነበር፡፡ ቅጠልም ቢሆን እህል ቀዝቃዛ ወይም ምንም አይቀምስም ነበር፡፡ ፊቱም እንደ ንጋት ኮከብ ያበራ ነበር፡፡
አራቱን ወንጌላት እየፀለየ ሳለ ቅዱስ ገብርኤልንና ቅዱስ ሚካኤልን በቀኝና በግራ አስከትሎ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት፡፡ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን አለው ያን ጊዜ አቡነ ሀብተማርያም ከፈጣሪው ግርማ የተነሳ ደንግጦ ከመሬት ወድቆ እንደ በድን ሆነ፡፡ ጌታችንም አንስቶ ክቡራን በሆኑ እጆቹ አፀናው ታላቅ የሆነ ቃል ኪዳንም ገባለት በፀሎትህ አምኖ በጎ ስራ ለሚሰራ ሁሉ በህይወት ሳለህ ልብስ በመስጠት ወይም ምግብ በማቅረብ፣ እግር በማጠብ፣ እንጨት ሳር በማቅረብ፣ ውሃ በመቅዳትና በመርዳት ለደከመ ሁሉ እምርልሃለሁ ዳግመኛ ከሞተ በኋላ መንግስተ ሰማያትን አወርሰዋለሁ አንተ ከሞትክም በኋላ ስምህን የጠራውን ዝክርህን ያዘከረውን ሁሉ የሀብተማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በህሊና ያሰበውን በልቦናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ አለው፡፡ ማቴ 10፡41-42
ጠላቶችህ አጋንንትን ያጠፋልህ እና ይጠብቅህ ዘንድ ቅዱስ ሚካኤል ካንተ አይለይም የሰጠሁህን ቃል ኪዳን እንዳልነሳ በራሴ ማልኩልህ ከእናትህ ማህፀን ጀምሮ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ አድርጌ መረጥኩህ እንጂ በብዙ ገድልህና በድካምህ ብቻ የወደድኩህ አይደለም፡፡ ይህን ቃል ኪዳን ከሰጠው በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር፣ በብርሃን፣ በቅዳሴ፣ በስልጣን ወደ ሰማይ አረገ፡፡
ቅድስት ዮስቴናም ባሏ ከሞተ በኋላ ለራሷ ምንም ሳታስቀር ገንዘቧን እናት አባት ለሞቱባቸው፣ ለባልቴቶች፣ ለጦም አዳሪዎች፣ ለድሆች ጨርሳ ሰጠች፡፡ በጾም በፀሎትና በስግደት ሰውነቷን አደከመች፡፡ እንዲህ ባለ ገድል ሳለች ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል ወደ እሷ መጣ እኔን ለማገልገል ሴቶች ወንዶች ባሮችሽን፣ ወንድሞችሽን እህቶችሽን ቤትሽን ስለ ተውሽ ሰማንያ ርስት ከተሞችን ሰባት አክሊሎችን እነሆ አዘጋጀሁልሽ አላት ደጋግ ስራን ሰርታ ከፈፀመች በኋላ አረፈች፡፡ መዝ 115/116 ፡ 6 እግዚአብሔር አምላክ አስቀድሞ ተስፋውን እንደነገራት ሰባቱን አክሊላት ሸለማት ሰማንያውን አህጉራት ገነት አወረሳት፡፡
ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ወደ ቤተክርስቲያን በሄደ ጊዜ ወንጌል ሲነበብ የክርስቶስ ጌትነቱን የሚናገር ወንጌል ሲነበብ "ወዮሴፍ ብእሊሃ ለማርያም ፃዲቅ ውእቱ" የሚል ከቄሱ አፍ ይህን ንባብ ሲሰማ ደንግጦ ወንጌል ወደ ሚነበብበት ስፍራ ሄደ የሚያነበውን ቄስ ገሰጸው "ወዮሴፍሰ ፈሃሪሃ ለማርያም ጽድቅ ውእቱ" በል እንጂ ብእሲሃ አትበል ብሎ መከረው ቄሱም አቡነ ሀብተማርያም እንዳዘዘው ከስህተቱ ወደ ቀና ንባቡ ተመለሰ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ተገልጾ ወዳጄ አመሰገንኩህ እናቴን ድንግል ማርያም ስለ አከበርክ እኔም በመንግስተ ሰማያት ፈጽሜ አከብርሃለሁ አለው፡፡
ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ከጌታ ጋር በተነጋገረ ጊዜ እንደ ነብዩ ሙሴ በፊቱ ብርሃን ተሳለ፡፡ ሰዎችም የፊቱን ብርሃን አይተው መቅረቡን ፈርተው አደነቁ፡፡ አቡነ ሀብተማርያምም ጌታ ሆይ ከንቱ ውዳሴ እንዳይሆንብኝ በፊቴ ላይ የተሳለውን ብርሃን ሰውርልኝ ብሎ ፀለየ፡፡ ጌታም ፊቱን እንደቀድሞው አደረገው፡፡ በጾም በፀሎት ላይ ሳለም በሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ወደ ሰማይ ተነጥቆ ቅዱሳን የሚኖሩባቸውን ዓለማት መንግስተ ሰማያትንና ሲኦልን ተመለከተ፡፡
ሰይጣንም መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ በሀብተማርያም ላይ መከራ አፀናበት ዘንድ ፍቀድልኝ ብሎ ጮኾ፤ ተናገረ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም በሰይጣን ላይ ተቆጥቶ በነፍሱም በስጋውም መከራ ታፀናበት ዘንድ አልፈቅድም ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ መርጨዋለሁና በንፅህናና በቅድስና ኃጢአት እንዳይሰራ ዘወትር እጠብቀዋለሁ በእርሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በሀብተማርያም ፀሎት በተማፀነኝ ሁሉ ላይ እንኳን አላሰለጥንህም ብሎ አሰናበተው ሰይጣንም ይህን ቃል ሰምቶ አፍሮ እያዘነ ሄደ፡፡ ያዕ 1፡12
አባታችን አቡነ ሀብተማርያም እንዲህ ባለ ስራ ላይ ሳለ ሰውነታቸው እንደ መርግድ የሚያሸበርቅ ዘጠኙ ክቡራን ሰዎች ወደ እርሱ መጡ፡፡ አብሯቸው ያለውን መልአክ ይህን ያህል ብርሃን የከበበው ይህ ሰው ማን ነው ብሎ ጠየቀው መልአኩም አባትህ ተክለሃይማኖት ነው አለው፡፡ ክቡር የሆነ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ጠርቶ ልጄ ሀብተማርያም ሆይ ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ስለወደደህ ብዙ ምርኮ እንዳገኘህ በአንተ ፈጽሞ ደስ ይለኛል፡፡ ነገር ግን የምለምንህ ነገር አለና እሺ በለኝ አለ፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያምም ጌታዬ ነገሩ ምንድን ነው አለ? ክቡር አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖትም ከተቀበርኩበት ቦታ እንድትቀበር ቃል ኪዳን ግባልኝ አለው፡፡
አቡነ ሀብተማርያምም ይህንን አደርግ ዘንድ ስለምን ትወዳለህ አለው አቡነ ተክለሃይማኖትም በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስት መቅሰፍቶች አሉና ነው፡፡

እነሱም፡-
1. መብረቅ፣
2. ቸነፈር፣
3. ረሃብ፣
4. ወረርሽኝ፣
5. የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡
የአንተም አጽም በውስጡ የተቀበረ እንደሆነ አጥንቴ የተቀበረባት ሀገሬ ከነዚህ መቅሰፍታት ትድናለችና ልጄ ሀብተማርያም ሆይ አንተ የማታውቀው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር የተሰጠህ እኔ የማውቀው ክብር አለህና ስለዚህ ነው ቃል ኪዳን ግባልኝ ብሎ ማለደው፡፡ ይህን ሲባባሉ እንዲህ የሚል ቃል መጣ፡፡ ከወዳጄ ከሀብተማርያም አንደበት ይህ ቃል ኪዳን አይወጣም እርሱ በወደደው የሚቀበር አይደለም፡፡ እንዲህም ብለህ የምታስገድደው ለምንድን ነው እኔ በወደድሁት ቦታ ይቀበራል እንጂ የሚል ቃል ተነገረ፡፡ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖትም እየለመነና እየሰገደ ሶስት ጊዜ ከስላሴ ዙፋን ተንበረከከ፡፡ይሁን ይደረግ የሚል ቃል ከሰማይ ሰማ በወዳጄ በሀብተማርያም አጥንት ቦታህ የምትድን ስለሆነች ፈቃዴ ነው ብሎ ጌታ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡
ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም በፀሎት ላይ ሳለ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ የቆምክባትን ቦታ ምስራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን ባርክ አለው፡፡ ሲባርክም ሶስት አጋንንት በፀሎቱ ስልጣን ታስረው በፊቱ ታዩት፡፡ እነዚህም አጋንንት ከኖህ ጀምሮ ሰውን በማሳት ከኖርን በኋላ ከአንተ ጋር ምን ፀብ አለን አሉ አባታችንም አቡነ ሀብተማርያም በትዕምርተ መስቀል ሲያማትብ ሁለቱን አጋንንት ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው አንዱ ጊዜዬ ስላልደረሰ አታጥፋኝ አለው፡፡ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይህንን ተወው ጊዜው አልደረሰም አለው፡፡ የጌታ ቃል እንዲህ ብሎ በተናገረ ጊዜ ሰይጣን ከአባታችን ተለይቶ ጠፋ፡፡ ማር 9፡23
ከዚህም በኋላ ዕለተ ሞቱ በደረሰ ጊዜ ለሞቱ ምክንያት የሚሆን ቸነፈር ያዘው፡፡ ጌታችንም በምስጋና ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ዛሬ ወደአንተ የመጣሁት ከድካም ወደ እረፍት እወስድህ ዘንድ ነው ሰባት የጽድቅ አክሊሎችን አዘጋጅልሃለሁ፡፡

1. ስለ ንፁህ ድንግልናህ፣
2. አለምንና በውስጡ ያለውን ንቀህ በመኖርህ፣
3. ስለ ፍፁም ምንኩስናህ፣
4. ዘወትር አራቱን ወንጌላትን በማንበብህና በመፀለይህ፣
5. ስለ እኔ ብለህ ስለተራብከው፣
6. በጾም ስለተጋደልክ፣
7. ቂምና ጥላቻን፣ ትዕቢትን፣ ትምክህትን፣ በልብህ ውስጥ ባለማስቀመጥህ ስለ ንፁህ ተልዕኮ ክህነትህ፣ ስለ ንፁህ መስዋዕትህ ነው ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡
በተጨማሪም እኔ የሰጠሁህን ቃል ኪዳን ተስፋ አድርጎ መጽሐፈ ገድልህን ለሚጽፈው ስሙን በመንግስተ ሰማያት በእውነት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፣ ለቤተክርስቲያንህ ዘይትን፣ ወይንን፣ ዕጣንን፣ ህብስትን እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ በአንተ ስም መብዓ የሰጠውን የወደደውን ሁሉ አደርግለታለሁ፡፡ በመንግስተ ሰማያትም ከወዳጆቼ ከቅዱሳን ጋር በደስታ አኖረዋለሁ፡፡ የአቡነ ሀብተማርያም ፈጣሪ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ብሎ ያንተን ስም ጠርቶ ቢለምነኝ ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገባለት ይህንንም ካለው በኋላ ጌታችን አፉን ሶስት ጊዜ ሳመው፡፡ ያን ጊዜም ከመድኃኒዓለም ጣዕም ፍቅር የተነሳ ነፍሱ ከስጋው ተለየች መዝ 115/116 ፡ 6 በሰማያዊ መልአክት በምድራውያን ስውራን ቅዱሳን ዘንድ ታላቅ ደስታ ሆነ ህዳር 26 ቀን አረፈ፡፡ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማህሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በፃዲቁ መቃብር ቀበሩት፡፡
የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከታቸው ይደርብን አሜን፡፡

Sunday, November 4, 2012

ተመየጢ ተመየጢ ሱላማጢስ




ይህንን ቃል የተናገረዉ ንጉስ ሰሎሞን ነዉ፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ከመዝሙር ሁሉ ሚበልጥ መዝሙር ተብሎ በሚጠራዉ መጽሃፉ በመሐልይ መሓልይ ላይ ደጋግሞ ተመለሺ ተመለሺ እያለ ሲዘምር እናያለን፡፡ሰሎሞን ማለት የቃሉ ትርጉም መስተሳልም የሰላም ሰዉ ሰላማዊ ማለት ነዉ፡፡(፪ኛ ሳሙ12፤24) ይህም የሆነበት ዘመኑ እርቀ ሰላም የተደረገበት ስለሆነ ነዉ፤ አባቱ ዳዊት ግዚአብሔር ጋር: እግዚአብሔርም ከዳዊት ጋር በታረቁበት ዘመን ስለተወለደ መስተሳልም ሰላማዊ  እንዲሁም ይዲዲያ ወይም በእግዚአብሔር የተወደደ ተብሏል፡

የሎዶባር ምርኮ








የእስራኤል ልጆች ከጠላት ጋር በጦር ቀጠና ዉስጥ ሲፋለሙ የ አምስት አምቱ የዮናታን ልጅ ሜንፊቦስ በተፋፋምዉ የጦር ክልል ዉስጥ ነበረ፡፡
ሜንፊቦስ ማለት የቃሉ ትርጉም ወድቆ የተሰበረ ማለት ነዉ፡፡የህጻኑን ነፍስ ለማትረፍ ሞገዚት በትከሻዋ አዝላዉ ካደጋዉ ቀጠና ለማምለጥ በፍጠነት ስትሮጥ ሜንፊቦስቴ ክፉኛ ወደቀ ሽባም ሆነ፡፡

በሰ ው ትከሻ ያለ ስጋ ለባሹን ክንድ ያደረገ ሁሉ ይወድቃል ፤ ይሰበርማል። የማይወድቅ  በእግዚአብሔር የተደገፈ ብቻ ነዉ፡፡መጽሃፍ “ በሰዉ የሚታመን ስጋ ለባሹን ክንዱ የሚያደርግ ልቡን ከእግዚአብሔር የሚመልስ ሰዉ እረጉም ነዉ”(ኤር 17፤5 )ይላል፡፡ በሰዉ ትከሻ መኖር ምን ይሰራል ? በሰዉ መመካትስ ምን ይጠቅማል? የተሸከሙንስ ሰዎች ትከሻቸዉ የ እግዚአብሔርን ያህል ተመችቶልን ይሆን? በጭራሸ እንኳንስ ሊመች የተደገፍናቸዉ ሰዎች ጭራሽ ለስብራትና ለከፋ ሃዘን የዳረጉን ብዙዎች ነን፡፡  ለመሆኑ ሰዉ ምንድን ነዉ ? ነቢዩ ኢሳይያስ  “ለመሆኑ ሰዉ ምንድን ነዉ? እስትንፋሱ በ አፍንጫዉ ያለበትን ሰዉ ተዉት “ (ኢሳ 2፤22) ይላል፡፡

Thursday, November 1, 2012

ማንኛውም ክርስቲያን ሊያውቅ የሚገባ ፍሬ ጥቅሶች።




በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መሠረት 5ቱ ሀብታት፣ 5ቱ ፍኖተ ጽድቅ፣ 5ቱ አቀብተ ሲኦል፣ 5ቱ ፍኖተ ኃጢአት፣ 5ቱ ሐራ ሲኦል ነገስታት፣ 5ቱ ህሩያነ ነገስታት፣ 5ቱ አርዕስተ አበው ሲባሉ እነሱም፤
፩. †♥†5ቱ ሐብታት የተባሉት፤†♥†
፩.፩ ሐብተ ፈውስ፣  ፩.፪  ሐብተ ክህነት፣  ፩.፫ ሐብተ ትንቢት፣ ፩.፬  ሐብተ መዊእ፣      ፩.፭  ሐብተ መንግስት ናቸው።
...
፪. †♥† 5ቱ ፍኖተ ጽድቅ የተባሉት፣ †♥†
፪.፩ ፍቅር ፪.፪ ትህትና ፪.፫ ጾም ፪.፬ ጸሎት ፪.፭ ምጽዋት ናቸው
፫. †♥† 5ቱ አቀብተ ሲኦል የተባሉት፣†♥†
፫.፩ ጣኦትን ማምለክ ፫.፪ አፍቅሮ ንዋይ ፫.፫ ተጣልቶ አለመታረቅ ፫.፬ ሰው መግደል ፫.፭ እናት አባትን አለማክበር ናቸው።
፬. †♥† 5ቱ ፍኖተ ኃጢአት የተባሉት †♥†
፬.፩ ትዕቢት ፬.፪ ስስት ፬.፫ ምቀኝነት ፬.፬ ስርቆት ፬.፭ ዝሙት ናቸው።
፭. †♥† 5ቱ ሐራ ሲኦል ነገስታት †♥†
፭.፩ ፈርኦን በኤርት የሰጠመው ፭.፪ ሰናክሬም ፭.፫ አንጥያኮስ ፭.፬ ሔሮድስ ፭.፭ ዲዮቅልጥያኖስ ናቸው።
፮. †♥† 5ቱ ህሩያነ ነገስታት የተባሉት †♥†
፮.፩ ህዝቅያስ ፮.፪ ኢዮስያስ ፮.፫ ዳዊት ፮.፬ ሰለሞን ፮.፭ ንግስተ ሰባ አዜብ ማክዳ ናቸው።
፯. †♥† 5ቱ አርዕስተ አበው የተባሉት †♥†
፯.፩ አዳም ፯.፪ ሄኖክ ፯.፫ ኖህ ፯.፬ አብርሃም ፯.፭ ሙሴ ናቸው።
ለወደፊትም አደዳድስና አንባብያን ማወቅ ያለባቸውን አስደናቂ የቤተ ክርስቲያን ታሪኮችን ይዤላችሁ ብቅ እላለሁ ለዚህም የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ይርዳን አሜን።
†♥† ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር በአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡ እድሜ ለንሰሐ ዘመን ለፍሰሃ ሰጥቶኝ ይህችን ታህል ስለ አባታችን እንድመሰክር የረደኝ አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን።
†♥† አመስግኛት የማልሰለች፣ ስለሷ ተናግሬ የማይደክመኝ፣ በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡
†♥† ሌሊትና ቀን ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑና ሳይሰለቹ የሚጠብቁን ሊቀነ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሩፋኤል ቅዱስ ዑራኤል ቅዱስ ራጉኤል ቅዱስ ፋኑኤል እልፍ አእላፋት የሆኑ ጠባቂ መላእክት ሳመሰግን በደስታ ነው፡፡


†♥† በጸሎታቸው ያልተለዩኝን ጻድቃን አባቶቼን አቡነ ተክለሃይማኖትን አቡነ ገብረምንፈስ ቅዱስን አቡነ ሀብተማርያምን አቡነ አረጋዊን አቡነ ኪሮስንና ሌሎች ቅዱሳን አባቶቼን እንዲሁም እናቶቼን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራን ቅድስት አርሴማን ብዙ ያልጠቀስኳቸው ቅዱሳንን ለማመስገን ቃላት የለኝም፡፡

†♥† በሰማኝትነታቸው የጥንካሬ ምሳሌ የሆኑልኝ በጸሎታቸው የረዱኝን ቅዱሳን ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ቅዱስ እስጢፋኖን መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስንና ሌሎችን ቅዱሳን ሰማዕታትን ሁሉ በእጅጉ አመሰግናለሁ ለዘላለሙ አሜን፡፡
                           †♥† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያውያ ተወላጆች ቅዱሳን ታሪክ በሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ።



“የክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር”




“የክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር”
(ብፁእ አቡነ ሺኖዳ 3ኛ)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቃየ ፤ ነገር ግን ስለእኛ ተሰቃየ ፡ ስለእኛ ተሰቃየ ፤ እኛን ከስቃይ ከህማም ያድነን ዘንድ እርሱ ተሰቃየ ፡ እኛን ከሞት ያድነን ዘንድ ሞተ ፤ እኛን ከድካም ያሳርፍ ዘንድ እርሱ በእጅጉ ደከመ ፤ ክርስቶስ እኛን ያድነን ዘንድ ተሰቃየ ፡ ስለሌሎች ተሰቃየ ፤ ህማሙ በነፍሱና በስጋው ላይ ወደቀ ፡ ለረጅም ሰአት መስቀሉን ተሽክሞ ነበርና ፡ በሚወድቅ ሰአት ከባዱ መስቀል ተጭኖት ነበርና ፡ የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፍተው እንዲንገላታ አድርገውት ነበርና ፡ ቅዱስ ስጋውን በሚስማር ቸንክረው እንዲሰቃይ አድርገውት ነበርና ፡ በመስቀል ላይ ለረጅም ሰአት ተሰቅሎ ነበርና ፡ ደሙ እንደውሃ ፈሶ ነበርና ፡ ተደብድቦ ተገርፎም ነበርና ፤...
ደበደቡት ፡ ገረፉት ፡ ተፉበት እኒህ ሁሉ የጌታችን የስጋ ህማሙ ናቸው ፤ ነገር ግን የተቀበለው መከራ ይህ ብቻ አይደለም ፤ የስጋ ህማም ያልሆነ የነፍስ ህማምንም ታግሷል እንጂ ፤ እንደ ርጉም እንደበደለኛ መቆጠሩ ይህ አንዱ ህማሙ ነበር ፡ የመሰደቡ ህማም ይህ አንዱ ህማሙ ነበር ፡ በሁሉ ፊት መዋረዱ ይህ አንዱ ህማሙ ነበር ፡ የመካድ ህማም ፡ በሁሉ የመወገዝ ህማም ፡ እኒህም ሌላው ህማሙ ናቸው ፤ ሃዋርያቱ እንኳን ሳይቀሩ ትተውት ሽሹ ፡ ጴጥሮስ እንኳን ሶስት ጊዜ ካደው ፡ በወንድሞች መካከል በድካም መታየት ይህ ራሱ ለነፍስ ትልቅ ህማሟ ነው፡፡
ጌታችን ግን ይህ ሁሉ መከራ ሲደርስበት ራሱን ይከላከል ዘንድ ምንም አላደረገም ፡ ራሱን አልተከላከለም ፤ በገዥወች የፍርድ ዙፋን ፊት በቆመ ጊዜ የውሽት ምስክሮችንና ክሶችን አቀረቡበት ፡ እርሱ ግን ዝም አለ ፡ ምላሽም አላቀረበም ፡ “አንተ ስለራስህ አትናገርምን? እኒህ ሁሉ ባንተ ላይ ሲመሰክሩ እንደምን ዝም ትላለህ?” እስኪሉት ድረስ ዝም አለ ፡ በጲላጦስም ፊት ሁሉ በሃሰት ሲከሱት ምንም አልተናገረም ፡ ዝም አለ እንጂ ፤ ራሱን ይከላከል ዘንድ አንዳች አላደረገም ፤ ራሱንስ ይከላከል ዘንድ ቢወድ ይህ በእርሱ ዘንድ እጅግ ቀላል ነበረ ፡ በክርስቶስ ዘንድ ያለ እውቀት ፡ ማመዛዘን ፡ መረዳትና ማሳመኛ ሊከላከልለት በቂ ነበርና ፤ ነገር ግን ፈቃዱ ራሱን ይከላከል ዘንድ አልነበረም ፡ ፈቃዱ ሌሎች ያድን ዘንድ ነበር እንጂ ፤ ሌሎቹም ይድኑ ዘንድ እርሱ መሰቀል ነበረበት ፤ ታገሉት “ አንተ የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ ራስህን ከመስቀል ላይ አውርድ” እያሉ ታገሉት ፤ እርሱ ከመስቀል ወርዶስ ቢሆን እኛ ሁላችን በጠፋን ነበር ፤ እርሱ ግን እኛ እንድንለት ዘንድ ስለእኛ በእነሱ መሽነፍን ወደደ ፡ ስላቃቸውን ይታገስ ዘንድ መረጠ ፤ እራሱንስ ይከላከል ዘንድ አልወደደም ስለሁሉ ሰው መከላከልን መርጧልና ፡ እኛን ያድን ዘንድ ስለሁሉ እርሱ ዋስ ሆነ ፤

ዳግምም ጌታችን ራሱ ስለራሱ ፈቃድ ተሰቃየ ፤ ራሱ ? እንደምን በራሱ ፈቃድ ተሰቃየ? ምን ማለት ነው? ይህ ማለት ክርስቶስ ራሱ አይሁድ ሊይዙት ወደሚፈልጉበት ቦታ በእግሩ ሄዷልና ነው ፡ የት ቦታ አይሁድ ሊይዙት እንደተማከሩ እርሱ አስቀድሞ ያውቅ ነበርና ፡ ጊዜውንም ያውቅ ነበርና ፡ ስለዚህም እርሱ ራሱ ወደሚይዙበት ቦታ ሄደ ፡ ይሁዳ አሳልፎ ከመስጠቱ በፊት ራሱን አሳልፎ ሰጠ ፡ ዳግምም በራሱ ፈቃድ ራሱን ለሞት አሳልፎ ሰጠ ፡ ስለዚህም እንደዚህ አለ ፦ “ነፍሴን ላጠፋትም ላነሳትም ስልጣን አለኝ” በዚህም ከሚደርስበት ስቃይ ሁሉ ራሱን ይጠብቅ ዘንድ ይችል ነበር ፡ ነገር ግን በጄ አላለም ፤ እርሱ በራሱ ፈቃድ ለእኛ ራሱን መስዋእት አደረገ፡፡
በጌታችን በክርስቶስ ያየነው ስቃይ ሁሉ ጌታችን ለእኛ ያለው የፍቅር ምልክቶች ናቸው ፤ ጌታችን “ስለወዳጆቹ ነፍሱን ከሚሰጥ የሚበልጥ ፍቅር የለም” አለን ፡ ስለዚህም እነዚያ ስቃዮቹ ሁሉ ስቃዮች ብቻ አልነበሩም ፍቅሩም ነበሩ እንጂ ፤ እንግዲህ እግዚአብሄር በእኛ ላይ ያለውን ፍቅር ያሳይ ዘንድ ሃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለእኛ ሞተ ፤ የክርስቶስ ስቃይና ፍቅሩ የሚለያዩ አይደሉም ፤ የክርስቶስ መስዋእት የፍቅር መስዋእት ነው ፡ እግዚአብሄር በክርስቶስ ያመነ ሁሉ እንዲድን እንጂ እንዳይጠፋ አንድያ ልጁን አሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ አለሙን ወዷልና ፤ ስለዚህ ክርስቶስ ስለእኛ ባለው ፍቅር ስቃይን ተቀበለ ፤ በእኛ ላይ ባለው ፍቅር ምክንያት ባይሆን ኖሮማ ስለእኛ ባልሞተ ነበር ፤ እንግዲህ እኛም ክርስቶስን መልሰን እንውደደው ፡ ስለወደደን እንውደደው ፤ የክርስቶስ መከራ ራሱን ባዶ በማድረግ የተገለፀ ነበር ፤ እንዴት? ምናልባት አንዳንዶቻችሁ ክርስቶስ የሰውን ስጋ በለበሰ ጊዜ ራሱን ባዶ አድረገ ብላችሁ ታስቡ ይሆናል ፡ ልክ ናችሁ ፤ እርሱ የባርያን መልክ መያዙ ፡ በሰው አምሳል መገለጡ ፡ በከብቶች በረት መወለዱ ፡ ይህ ሁሉ ራሱን ባዶ ማድረጉ ነው፡፡
ነገር ግን የሚበልጠው ራስን ባዶ ማድረግ በስቅለቱ የፈፀመው ነው ፤ ምክንያቱም ጌታችን ሃይሉን ይጠቀም ዘንድ ይችል ነበርና ፡ ነገር ግን ሃይሉን ይጠቀም ዘንድ አልወደደም ፡ ሊያስሩት በመጡ ጊዜ ሃይሉን አልተጠቀመም ፡ በፍርድ ወቅትም ሃይሉን አላሳየም ፡ በስቅለቱ ጊዜም ሃይሉን አላሳየም ፡ በጥፊ በመቱት ጊዜ ፡ በውርደት ፊቱ ላይም በተፉበት ጊዜ ሃይሉን አልተጠቀመም ፤ ሃይሉን አልተጠቀመም ፡ እርሱ ራሱን ባዶ አድርጓልና ፤ ራስን ባዶ ማድረግ!! ሃይሉን አልተጠቀመም ፡ ነገር ግን ይቅርታውን ተጠቀመ ፡ ስለዚህም በቅዳሴአችን “አንተ የክፉወችን ማስጨነቅ ታግሰሃል” እንላለን ፡ “መታገስ - ምን? የክፉወችን ማስጨነቅ ፡ ጌታ ሆይ “ ከሃፍረትና ከምራቅ መተፋት አንተ ፊትህን አላዞርክም ፡ ከአይሁድ ጥፊም ጉንጮችህን አላራቅክም” ፤ ይችል ነበር ነገር ግን ለእኛ ሲል ከእንግልት ራሱን አላረቀም ፡ በእኛ ላይ ስላለው ፍቅር የተነሳ ከመከራ አልሽሽም፡፡ የማዳን ስራውን ይጨርስ ዘንድ እስከመጨረሻው ታገሰ ፡ ይህ ነው እንግዲህ የሚበልጠው ራስን ባዶ ማድረግ ፤ ራስን ባዶ ማድረግ፡፡
የክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር እጅግ በሃይል የተሞላ ነበር ፡ ይህ ሃያል ፍቅሩ በፅናቱ ብቻ የሚገለፅ አይደለም ፡ በማዳን ስራውም ጭምር እንጂ ፤ ክርስቶስ በጥልቅ ፍቅሩ ፡ በመታሰሩ ፡ በሞቱ የዲያቢሎስን ራስ ቀጠቀጠው ፡ የዲያቢሎስን ራስ ቀጠቀጠው !! የደረሱበትን ስቃዮችና ውርደቶች ሁሉ በትእግስት በመቋቋሙ ሃይለኛ ነበር ፤ በዝምታው ውስጥ ስለራሱም ባለመከራከር ውስጥ ሃይለኛ ነበር ፡ እርሱ ሃይለኛ ነበር ፡ በሞቱ ሞትን አሽንፎታልና ፤ እርሱ ሃይለኛ ነበር ዲያቢሎስን ድል ነስቶታልና ፤ እመኑኝ ስለክርስቶስ ከሚነገሩት የተመረጡ ንግግሮች ሁሉ በጣም ግሩሙ “ራሱን ባዶ አደረገ” የሚለው ነው ፤ ስለመዳናችን እንዲህ ተነገረ “በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤” ከዚህ የሚበልጥ ራስን ባዶ ማድረግ አለን? እርሱ ስለእኛ መተላለፍ እንደተቀሰፈ ተቆጥሯልና ፤ ግር የሚለው ነገር ህግ ተላላፊወች ሁሉ በግራ የተሰቀለው ወንበዴ እንኳን ሳይቀር በአንደበታቸው በውርደት ቃል እየሰደቡት የነበረ መሆኑ ነው ፡ በቀኝ የነበረው ወንበዴ ግን አልተባበረም ፤ እርሱ ስለእኛ ርጉም ሆነ ፡ ለእኛም ሲል ሐጢአተኛ ተባለ ፡ ብቻውን ቅዱስ የሆነ እርሱ አንዳች እንኳን ሃጢአት ሳይኖርበት ስለእኛ በደለኛ ሆነ ፤ ከሁሉ ይልቅ ብሩክ እርሱ” በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሁሉ ርጉም ነው” ተብሎ ስለተፃፈ ርጉም ተባለ ፤ እንግዲህ ከዚህ በላይ ራስን ባዶ ማድረግ አለን? በፍፁም የለም!! ይህ ነው የክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር! ይህ ነው የክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር!

Sunday, October 28, 2012

ተዋሕዶ መጠርጠር የሌለባት ሃይማኖት








ካለፈዉ የቀጠለ….

እናም ትንቢቶቹ በመሀመድ ወይም በሉተር አልያም ከእነርሱ ወዲህ ለተመሰረተ ሃይማኖት የተነገሩ ናቸዉ ተብሎ እንኳን ቢታሰብ ፍጹም የማይመስል ነገር ነዉ፡፡ምክንያቱም መስራቾቹ እነርሱ እስከሆኑ ድረስ ከመሀመድ ወይም ከሉተር በፊት ሃይማኖት አልነበረም እንዴ ? ተብሎ ቢጠየቅ መልስ አይኖርም፤ምናልባት ላለማመን ተብሎ ሌላ ነገር ካልተነገረ በቀር ማለት ነዉ ወይም በሌላ በኩል ከእነ መሀመድ እና ሉተር በፊት የነበሩ ሐዋያት ቅዱሳን ጻድቃን ሰማእታት በሙሉ እነ ሉተር ዘመን ላይ ስላልደረሱ እነዚህ ሁሉ ሃይማኖት አልነበራቸዉም ማለት ነዉ? ሰዉነታቸዉ እንደ ሽንኩርት በሰይፍ የተቀረደደዉ ፤ በእሳት የተቃጠለዉ ፤ አጥንታቸዉ  እየተፈጨ በንፋስ የተበተነዉ ፤ ቆዳቸዉ ተገፎ አቅማዳ እስኪሆን ድረስ ያደረሳቸዉና ያን ሁሉ ሰማእትነት ይከፍሉ የነበረዉ ገና ወደፊት ፍር ለሚመሰርተዉ ሃይማኖት ነበር ማለት ነዉ?




Sunday, October 21, 2012

ተዋሕዶ መጠርጠር የሌለባት ሃይማኖት



ትንቢቶች ሁሉ መፈጸማቸዉ ግድ ነዉ፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ህግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለእኔ የተጻፈዉ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል (ሉቃ24፤44) እንዳለ ስለርሱ የተነገሩ ትንቢቶችን በሙሉ እርሱ ፈጽሟቸዋል፤ ነቢያትና ሐዋርያት ስለመጪዉ ጊዜ  የተናገሩትም ትንቢት ቅንጣት ታክል እንኳን ሳትፈጸም አትቀርም፡፡ ስለ ሰዎች እምነትና ክህደት የተነገሩ ትንቢቶች ተፈጽመዋል፡፡እየተፈጸሙም ነዉ ገና ወደ ፊትም ይፈጸማሉ፡፡
ሐዋርያት “በግልጽ በለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በዉሸተኞች  ግብዝነት የተሰጠዉን የ አጋንንትን ትምህርት እያደመጡ ሃይማኖትን ይክዳሉ”  (1ጢሞ4፡1) <<በቅዱሳን ነቢያትም ቀድሞ የተባለዉን ቃል በሐዋርያቶቻችሁም ያገኛችሁትን የጌታንና  የመድሃኒታችንን ትዕዛዝ እንድታስቡ በሁለቱ  እያሳሰብኳችሁ ቅን ልቡናችሁን አነቃለሁ፡፡በመጨረሻዉ ዘመን እንደራሳቸዉ ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ>>(2ጴጥ3፤2) የሚሉት ትንቢቶች ሁሉ የግድ መፈጸም አለባቸዉ፡፡<<ክህደት  ትጠፋለች ሃይማኖት ግን ለዘላዓለሙ ትጸናለች>>ሲራ40፤12


“ወኢንህድግለነ ማህበረነ”መሰባሰባችንን አንተዉ (ዕብ 10፡25)




ከፍረት አለም ጀምሮ ቅዱሳን መላእክት ሆኑ የሰዉ ልጆቸ እግዚአብሄርን በህብረት  ሆነዉ እንደየተፈትሮአቸዉ እንደሚያመልኩት መፅሃፍት ያስረዱናል ፡፡በብሉይ  ኪዳን አይሁድ ለእግዚአብሄር በለዩት ስፍራ በማህበር በመሰባሰብ እግዚአብሄርን ያመልኩት ነበር፡ ለስሙም መስዋእትን በፊቱ ያቀርቡ ነበር ፡ ፡በሐዲስ ኪዳንም ሐዋርያት እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ  በመሆን በህብረት ይጸልዩና በሰሙ ይሰበሰቡ እንደነበር ቅዱስ ሉቃስ በሐዋርያት ስራ ላይ ዘግቦት እናነባልን፡፡ ሐዋ4፡32   ይህን ማህበርም  ለእዉነተኖች ክርስቲያኖች አስረክበዉ አልፈዋል፡ ፡