ከአንድ መቶ ስድሳ እስከ ሦስት መቶ
አስራ ሁለት (160-312 ዓ.ም) ያለው ዘመን ዘመነ ሰማዕታት
ወይም የቤተክርስቲያን የስደት ዘመን ይባላል ቤተክርስቲያን ብዙውን ቅርሷን ያጣችው በዚህ ዘመን ነው በዚህ ዘመነ ሰማዕታት በቤተክርስቲያን
ላይ የደረሰውን ግፍ ዘርዝሮ አንድ በአንድ ለማስረዳት በጣም ብዙ ቢሆንም፣ ጎላ ብለው የሚታዩትን ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡
የሮም ግዛት በሰሜን ምስራቅ በኩል
ሰሜን አፍሪቃን ግብፅንና መካከለኛውን ምስራቅ ታናሽ እስያንና ግሪክን፣ በምዕራብ በኩል ፈረንሳይ እና እስከ ታላቋ ብሪታንያም ድረስ
የተንሰራፋ ነበር የክርስትና ሃይማኖት ሮም ቅኝ ግዛት ክፍል ከምትሆን ከፍልስጥኤም ምድር ስለመጣና መምህሮቿም የአይሁድ ሃይማኖት
መጣፍ ‹‹ብሉይ ኪዳንን›› ለማስረጃ ስለሚጠቀሙበት ከላይ በተጠቀሱት የሮም ቅኝ ግዛቶች የነበሩ ሹማምንት ሁሉ ክርስትና ሃይማኖት
አይሁድ የሮምን ግዛት ለማፍረስ የፈጠሩት ሃይማኖት ለበስ ፖለቲካ መስሏቸው ነበር፡፡ የክርስትና ሃይማኖት ግን በርግጥ እነሱ እንዳሰቡት
ሃይማኖት ለበስ ፖለቲካ አልነበረም፣ ይሁን እንጂ የሮማን መንግስት የተስፋፊነት መንፈስ የሚቃወም፤ መንገድ ሁሉ ወደ ሮም ያስገባል
የሚለውን ውርስ የሚቃወም ነበር፡፡
የሮም ነገስታት በግብዝነት የሚፈጽሙትን
የመመለክ ጠባይ ክርስትና ትምህርት በይፋ ተቃወመ፣ ቤተ ክርስቲያን በመመሪያዋ መሠረት ‹‹አምላክ አንድ ነው እርሱም ለመግደል ለማዳን
የሚችል ነው ለሱ ልትሰግዱ እርሱን ልታመልኩ ይገባል ይህ እናንተ የምታደርጉት ለእንጨት ለድንጋይ ለእንሰሳ መስገድ ለነገስታቱም
አምላካዊ ክብርና ስግደት መስጠት አምለኮ ባዕድ ነው›› በማለት አስተማረች፡፡
በዚህ ጊዜ በቤተክርስቲያንና በነገስታት
መካከል እልክ የሚያጋባ ጠብ ተፈጠረ የሮም ነገስታት ሲመለኩና ሲሰገድላቸው ኑረው ከሞቱ በኋላ ደግሞ ምስላቸው፣ ሐውልታቸው ይመለክ
ነበርና ለጠቡ ምክንያት የሆነው ይህ ነው ቤተ ክርስቲያን ‹‹እግዚአብሔር ክርስቶስ ነው›› ወይም ጌታ አምላክ ክርስቶስ ነው ስትል
የሮማ ቄሳሮች ደግሞ እንደለመዱት እናደርጋለን ሲሉ አንዱ ቄሳር አልፎ ሌላው ሲተካ የመከራውም ዓይነትና ብዛት እየጨመረ ሄደ እንዲያውም
የክርስቲያኖች እልቂትና ስቃይ የሮማ ቄሳሮች በመዝናኛና በዕረፍት ሰዓታቸው የሚመለከቱት ነበር ቀኑ አልመሽ ሲላቸውና የሚሰሩት ሲያጡ
ምስኪናን ክርስቲያኖችን ከአናብስት ጋር ያታግሏቸው ነበር ነገር ግን ክርስቲያንና ምስማር ሲመቱት ይተብቃልና ፈተናውንና የመከራው
ብዛት ለክርስትና ኀይማኖት ብርታትና ጥናትን ሰጠው፡፡
ከኔሮን ቄሣር በኋላ በክርስቲያኖች
ላይ ብዙ ስቃይ በማድረስ የታወቀው ወንድሙ ድምጥያኖስ ሲሆን ገና በሕይወት ሳለ ምስሉን አሰርቶ እንዲሰገድለት ሲል የታነሽ እስያ
ክፍል ወደ ምትሆን ወደ ኤፌሶን ላከው ያን ጊዜ ዮሐንስ ወንጌላዊ በኤፌሶን በሐዋርያነት ተግባሩ ላይ እንደ ነበር ይህን ምስል አይቶ
በጣም ተቃወመ የኤፌሶን ክርስቲያኖችም ከዮሐንስ ጋር ሆነው የድምጥያስን የግብዝነት ሥራ ተቃወሙ፣ በዚህ ጊዜ ዮሐንስ ተይዞ ወደ
ሮም እንዲወሰድና የተቃወመበትን ፍርድ እንዲቀበል የሮማ ምክር ቤት ወሰነ፡፡ ዮሐንስ ያን ጊዜ በዕድሜ በጣም የሸመገለ ቢሆንም ሐዋርያዊ
ግዴታ ስለሆነ ፍርዱን ለመቀበል ወደ ሮም ሄደ እዚያም በደረሰ ጊዜ የሮማ ዳኖች በደሴተ ፍጥም እንዲጋዝ ወሰኑበት ዮሐንስም በሮማ
ቄሣሮች ያመፁ ሁሉ ወደሚታሰሩበት ወደ ደሴተ ፍጥም ተወሰደ፡፡
ለ98-117 ዓ.ም የነበረው ኃይለኛ
ቄሣር ትራጃን የተባለው ነው ትራጃን በኃይል ብቻ ሳይሆን በዘዴና በማስፈራራትም ጭምር ክርስቲያኖችን ወደ ቤተ ጣዖት ለመመለስ የሞከረ ነው በቤተክርስቲያን ታሪክ
ስሙ በጣም የታወቀው ከሐዋርያውያን አበው አንዱ አግናጥዮስ የሰማዕትነት ተጋደሎውን የፈጸመው በዚሁ በትራጃን ዘመነ መንግስት ነው፡፡
አግናጥዮስ በአንጾኪያ የክርስቶስን መንግስት ሲያስተምርና
ሲሰብክ በትራጃን ወታደሮች ተጠልፎ ወደ ሮም ተወሰደ የአንጾኪያ ምዕመናን እንዲያመልጥ ልብን በሚሰብር ቃላት መላልሰው ለምነውት
ነበር እርሱ ግን በክርስቶስ ስም መሞትን ስለመረጠ ለምዕመኖቹ እንዲህ አላቸው ‹‹ልጆቼ ተውኝ ልቤን አትስበሩኝ እኔ እንደ ንጹሕ
መገበሪያ ለፈጣሪዬ መስዋዕት ለመሆን ነው የምሔደው›› አላቸው እዚያ ሲደርስ የሮማ ነገሥታት በክርስቲያኖች ላይ እንደሚያደርጉት ሁሉ በቲያትር ማሳያው ቦታ
ለነበሩ አናብስት ተጣለ ለሞተለት ለክርስቶስ የመጨረሻ ታማኝነቱን በሥራ ገለጠ፣ ለአንበሶች ስለተጣለ ‹‹ምጥው ለአንበሳ›› የሚል
ቅጥል አለው ለአንበሶች የተሰጠ ለአንበሶች የተጣለ ማለት ነው፡፡
ትራጃን በዘመነ መንግስቱ አልፎ አልፎም
ቢሆን በህጋዊ መንገድ ለመጓዝ የሚፈልግም ይመስላል የቢታኒያና የአወራጃዎቹ ገዥ አድርጎ የሾመው ፓሊኒ የተባለ ገዥ ተሹሞ ወደ ቢታንያ
እንደሄዱ በግዛቱ ውስጥ ብዙ ክርስቲያኖችን አገኘ ያን ጊዜ ክርስቲያኖች ቢሰቃዩም ቢገደሉም ተቆርቋሪ የሌላቸው መሆናቸውን ቢያውቅም
ቸኩሎ አልገደላቸውም ነገር ግን በግዛቱ ውስጥ ብዙ ክርስቲያኖች ማግኘቱንና ምን ማድረግም እንደሚገባው ከበላዩ መመሪያ ስለሚያስፈልገው
ጉዳዩን አብራርቶ ለጌታው ቄሳር ትራጃን ይጽፍለታል ትራጃንም በፓሊኒ የአመራር አስተዋይነት ተደስቶ የበላይነቱንም ስላከበረለት በማድነቅ
የሚከተለውን መልስ ጻፈለት ‹‹ወዳጄ ፓሊኒ በግዛትህ ውስጥ ስላገኘሃቸው ክርስቲያኖች ጉዳይ ትክክለኛነትና አስተዋይነት የተሞላበትን
ተመልክተነዋል ክርስቲያኖች እንደ አውሬ መታደን የለባቸውም ጥፋት ቢገኝባቸውም እንደማንኛውም ዜጋ ወደ ፍርድ ሸንጎ ቀርበው በሕግ
ይቀጣሉ፣ ይልቁንም ክርስቲያን የሚለውን ስም እንዲተው ማሳመን፣ ክርስቲያን የሚለውን ስም ከተውና ለአማልክቶቻችን ከሰገዱ ምንም
ዓይነት ወንጀል ሰርተው ቢገኙም ለሚመጣው መጠበቅ እንጂ ባለፈው የማይቀጡበት መሆናቸውን ቀስ በቀስ ማስረዳት በጣም የተሻለ ነው››
ብሎ ጻፈለት፡፡
ይህ አጻጻፍ ባንድ በኩል የትራጃንን
ተንኮለኝነት ቢያሳይም በሌላ በኩል ደግሞ ያለ ሕግ ሥልጣኑን መከታ በማድረግ ሰውን ከመግደል የተቆጠበ የአመራር ሥልት ያለው መሪ
ይመስላል ትራጃን ክርስቲያኖችን ከመጥላቱ የተነሣ ለአሕዛብ ሃይማኖትና ለሮማ ነገሥታት ጸሮች ናቸው ይላቸው ነበር፣ ብዙ ቄሣሮች
ቤተ ክርስቲያንን በተመሳሳይ የጥላቻ ዓይን ይመለከቷት ነበር፡፡
ከ161-180 ዓ.ም የነገሠው ፈላስፋው
ንጉሥ ማርቆስ አብርሊዮስ ክርስቲያኖች ሞገደኞች ወፈፌዎች ናቸው›› ይል ነበር፡፡ ከ180-192 ዓ.ም የነገሠው ቄሳር ከምዶስ ቀስ
በቀስ በዘዴ እያደረገ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ዕቅድ ነበረው ሌሎችም እንደነ እስክንድሮ- ሳዊሮስ እንደነ ፊሊጶስ ዓረባዊ ያሉ
ንቀውና ተጸይፈው ክርስቲያኖችን ከምንም አይቆጥሯቸውም ነበር፡፡ በቤተክርስቲያን የመጨረሻውን ድል ለማግኘት ብዙ ቄሳሮች ባላቸው
ኃይልና ዘዴ በሙላ ተጠቅመዋል የመጨረሻውና የማያዳግመው ዘዴ ግን በዳክዮስ ዘመነ መንግስት የወጣው አዋጅ ነው፡፡
ዳክዮስ ወዲያው እንደነገሠ የክርስቲያኖችን
መመሪያ አጥንቶ ክርስቲያኖችን በጣም የሚጎዳቸውን ነገሮች ከጠበብቱ ጋር ተመካክሮ የሚከተለውን አዋጅ አወጀ፡፡ አዋጁም ‹‹በሮም
ግዛት በሮማዊ ዜግነት የሚኖሩ ክርስቲያኖች ሁሉ በሮማ ባሕል መሠረት የሮማ መንግስት ህጋዊ ነው ብሎ የተቀበለውንና ነገስታቱም ሲያመልኳቸው
የኖሩትን ጣዖታት በግዴታ እንዲያመልኩና መባዕ እንዲያቀርቡ›› የሚል ነበር ይህን ሳይፈጽም የተገኘ ማንኛውም ዜጋ በሞት መቀጣት
ነበረበት ይህም መንግስታዊ አዋጅ ሮም ለብዙ ዘመን ትከተለው የነበረውን የሃይማኖት ነጻነት ሕግ የሚያፈርስ ስለሆነ በቤተክርስቲያን
ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሮም ግዛቶች በሚኖሩ አይሁዳውያንና አረማውያንም ሁሉ ሁከት ፈጠረ በዚህ ጊዜ ክርስቲያኖች ሌላ አማራጭ መንገድ
ስለሌላቸው አዋጁን አላከበሩም ለዳክስዮስ ጣዖታትም አልሰገዱም መባዕም አላቀረቡም፡፡
ስለዚህም ወንድ ሴት ሕጻን ሽማግሌ
ሳይለይ በሮም ግዛት በሚኖሩ ክርስቲያኖች ላይ አሰቃቂ የሆነ የሞት ቅጣት ታዘዘ ሕፃናት በእናታቸው እቅፍ ታረዱ እናቶችም የልጆቻቸውን
መታረድ ካዩ በኋላ አንድ እግራቸው በግንድ ላይ ታስሮ ሌላው አካላቸው ወደ ታች ቁልቁል እተንጠለጠለ በአሰቃቂ አሟሟት የሰማዕትነት
ጽዋቸውን ጨለጡ፡፡
ምንም በጉልበትና በኃይሉ ቢመካ ሰው
ሁኖ መሞት አይቀርምና ዳክዮስ ሞተ ቤተክርስቲያን ግን አልሞተችም ዳክዮስ ከሞተ በኋላ ወራሾች በዚህ አዋጅ መሰረት ብዙ ክርስቲያኖችን
ፈጅተዋል፤ ብዙ አቢያተ ክርስቲያናትን አቃጥለዋል ከዳክዮስ በማከታተዘል ቤተክርስቲያን ላይ ብዙ ስቃይ ያደረሱት ቄሳሮች ጋሊዮስ
ቄሳር፣ ቨሌርያን አሌራያን ናቸው ከነዚህ በኋላ በዓይነትም ሆነ በብዛት ተመሳሳይና ተወዳዳሪ የሌለው የክርስቲያኖች እልቂት የተፈጸመው
በዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግስት ነው፡፡
ዲዮቅልጥያኖስ ከተራ ቤተሰብ የተወለደ
የድልማጥያ ሰው ነው በልጅነቱ በሮም የወታደር ጦር ትምህርት ቤት ገብቶ በዘመኑ የነበረውን መታደራዊ ጦር ስልት ተምሯል፡፡
The European Court of Human Rights (ECHR) has ordered all crucifixes removed from state schools in Italy. This decision will now be used as a precedent to clear away all Christian symbols in schools and other public offices across Europe.
The ECHR in Strasbourg ruled last week that the presence of crucifixes “violates a child’s right to freedom of religion.”
According to the judgement, the court found that the “compulsory display of crucifixes violated parents’ rights to educate their children as they saw fit and restricted the right of children to believe or not to believe.”
The move was obviously brought as a result of the increasing number of Islamic children in European schools as that group steadily outbreeds indigenous Europeans and colonises the Continent.
Although the ruling was made with specific reference to schools in Italy, the precedent which it has now set can easily be applied throughout the EU.
A “human rights group” called Helsinki Monitor has already formally started proceedings against the Greek government, using the Italian case as a precedent.
It has demanded that Greek courts remove icons of Jesus Christ from above the judge’s bench and that the gospel no longer be used for swearing oaths in the witness box.
According to reports, Helsinki Monitor is urging trade unions to challenge the presence of religious symbols in Greek schools.
The ECHR ruling has been met with harsh criticism across Italy, and responses have included suggestions of holding a referendum on the subject.
Italian Prime Minister Silvio Berlusconi derided the ruling, stating that Italy is not bound to adhere to it.
Mr Berlusconi went so far as to say that even if Italy loses its appeal, he considers it to be disrespectful and that Italy would not be coerced into upholding it.
It remains to be seen how he expects to counter an EHRC ruling when Italy is firmly tied into the new EU constitution which has transferred such powers to the bureaucrats in Brussels.
It can also therefore not be too long before the “Church of England” name of many schools in Britain is also challenged.
This is nothing less than the steady, purposeful and malicious de-Christianisation of Europe in preparation for its complete Islamification.

ይቀጥላል
No comments:
Post a Comment