Friday, January 31, 2014

ወደ እኔ የገባው ሰው ይድናል ይገባል ይወጣል መሠማሪያም ያገኛል

‹‹የሉተራውያን ስህተት በሊቃውንት አስተምህሮ ሲገለጥና ሲጋለጥ››ክፍል 1

እንደ አብና መንፈስ ቅዱስ የአምልኮት ስግደት የሚቀርብለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይግባውና ምንም እንኳን መናፍቃኑ ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ኃይሉን ክደው አማላጅ ቢሉትም ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ያሳደገቻቸው ልጆቹ ግን የጌቶች ጌታ የነገስታት ንጉሥ የገዥዎች ገዥ መሆኑን አምልተውና አስፍተው አርቀውና አራቀው ትውልዱን ሲያስተምሩ ቆይተዋል፡፡
በቅዱሳት መጻሕፍት በጎላና በተረዳ ሁኔታ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት መገለጹ ይታወቃል፡፡ ለቤዛነትና ዓለምን ለማዳን መድኀኔዓለም ክርስቶስ ከቤተልሔም እስከ ቀራኒዮ የተጓዘበትን የድኅነት ሥራ ባለመረዳት ተቋዋሚዎችና ተረፈ ሉተራውያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አማላጃችን ሲሉት ይሰማሉ፡፡








Tuesday, January 28, 2014

የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች



 


‹‹ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ››
በአሁኑ ሰዓት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ አገልጋይ በመምሰል ምዕመን በመምሰል በተለያዩ ጉባኤያት አልፎ አልፎ በመምጣት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ውስጥ አባል መስለው በመግባትና የሰንበት ትምህርት ቤት ዮኒፎርሞችን በመልበስ በበዓላት ላይ ተገኝተው በዓል አክባሪ መስለው በመቀላቀል በመመሳሰል መስቀል በአንገታቸው ላይ አድርገው ኦርቶዶክሳዊ መስለው ፎቶ በመነሳት፣




የሚያስደንቅ ሞት




‹‹ሞታ ለማርያም የሃጽብ ለኩሉ››
(ጥር 21 አርኬ ዚቅ)
ቅዱሳን ሐዋርያት በአባታቸው በመምህራቸውና በመጋቢያቸው በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገትና መለየት ያዘኑና የተከዙ ቢሆንም አማናዊቷ ታቦት ሞገሳቸውና ክብራቸው ጽዮን በመካከላቸው ነበረችና ተጽናኑ ጽዮን ማለት አምባ መጠጊያ ማለት ነውና፡፡ ጽዮንን ተጠጉ ነቢዩ ዳዊትም ‹‹ዕግትዋ ለጽዮን›› ጽዮንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ ብሏልና ጽዮንን ከበው በመካከላቸው አድርገው ከጽዮን ተጠግተው አገልግሎታቸውን ወደ ዓለም ሁሉ አደረሱ፡፡




Monday, January 27, 2014

‹‹ፀሐይን የወለደችው ጨረቃ›› (ራዕ 12፡3)

 



‹‹ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች›› (ሚል 4፡2) እንዲል ነቢዩ ፀሐይ የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ይህንን ፀሐይ ወልዳ የሰጠችን የነቢያት ትንቢታቸው የአበው ተስፋቸው የድህነት ምክንያታችን ከዋክብት አክሊል የሆኑላት ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ያሏት ፀሐይን የተጎናፀፈች ጨረቃ የተባለችው ድንግል ማርያም ናት (ራዕ 12፡2)
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደቷና እድገቷ እንዴት እንደነበር በቅዱሳት መፃሕፍትና በአበው ትውፊታዊ ትምህርት በሰፊው ተገልል፡፡

Thursday, January 23, 2014

ባርነትና መንስኤው



‹‹ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነው›› 2ጴጥ 2፡20
በዕድሜ በጸጋና በአገልግሎት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሸመገለው ሐዋርያው ጴጥሮስ በቀዳሜ ሰማዕት በቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ምክንያት በጳንጦስ፣ በገላትያ፣ በቀጵዶቅያና ታናሽቱ እስያ ተበትነው ለነበሩት ክርስቲያኖች ክፉ ባልንጀርነት ደባል ሱስን በተመለከተ ምክሩን ሲለግስ ‹‹ሰው ለተሸነፈበት ነገር ተገዝቶ የሚኖር ከሆነ ለዚያ ባሪያ ይሆናል›› ብሏል በጎም ሆነ ክፉ ሰው ለሚወደውና ለተለመደው ይማረካልና (2ጴጥ 220) ማንም ሰው ከእናቱ ማህፀን ውስጥ ክፉም ሆነ በጎ ልምድን ይዞ አይወለድም፣ ይልቁንስ በጊዜና በዕድገት በትምህርትም ከህብረተሰቡ ይወርሳል እንጂ የተወለድንበት ያደግንበትና የተማርንበት ህብረተሰብ በሕይወታችን ለምናካብታቸው ልምዶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አስተዋጽኦ አለው፡፡


Friday, January 17, 2014

ክፍል ሁለት ዘመነ ዲዮቅሊጢያኖስ ዳግም በሮም ምድር



ዲዮቅልጥያስ ከደሀ ቤተሰብ የተወለደ በመሆኑ መንግስታዊ ዘር ባይቆጠርለትም አረግ ባይመዘዝለትም ተራ መታደር ሳለ ሀገሩ ከፋርስ መንግስት ጋር በተዋጋች ጊዜ ያሳየው ጀብዱና የጀግንነት ሙያው በመላው የንጉሠ ነገሥት መንግስት ውስጥ ለመታወቅ አብቅቆታል መልካም ዝናንም አትርፎለታል፡፡ እንዳጋጣሚም ሆኖ በዘመኑ የሮም መንግስት አስተዳደር ከስፋት የተነሣ ተዘበራርቆ ስለነበርና ወደ መውደቅም አዘንብሎ ስለነበር ዲዮቅልጥያኖስ የመንግስቱን ሥልጣን ይዞ (285 ዓ.ም) አውግስጦስ የሮም ንጉሥ ነገሥት ተባለ፡፡



Thursday, January 16, 2014

ዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ዳግም በሮም ምድር





ከአንድ መቶ ስድሳ እስከ ሦስት መቶ አስራ ሁለት (160-312 ዓ.ም) ያለው ዘመን ዘመነ ሰማዕታት ወይም የቤተክርስቲያን የስደት ዘመን ይባላል ቤተክርስቲያን ብዙውን ቅርሷን ያጣችው በዚህ ዘመን ነው በዚህ ዘመነ ሰማዕታት በቤተክርስቲያን ላይ የደረሰውን ግፍ ዘርዝሮ አንድ በአንድ ለማስረዳት በጣም ብዙ ቢሆንም፣ ጎላ ብለው የሚታዩትን ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡
የሮም ግዛት በሰሜን ምስራቅ በኩል ሰሜን አፍሪቃን ግብፅንና መካከለኛውን ምስራቅ ታናሽ እስያንና ግሪክን፣ በምዕራብ በኩል ፈረንሳይ እና እስከ ታላቋ ብሪታንያም ድረስ የተንሰራፋ ነበር የክርስትና ሃይማኖት ሮም ቅኝ ግዛት ክፍል ከምትሆን ከፍልስጥኤም ምድር ስለመጣና መምህሮቿም የአይሁድ ሃይማኖት መጣፍ ‹‹ብሉይ ኪዳንን›› ለማስረጃ ስለሚጠቀሙበት ከላይ በተጠቀሱት የሮም ቅኝ ግዛቶች የነበሩ ሹማምንት ሁሉ ክርስትና ሃይማኖት አይሁድ የሮምን ግዛት ለማፍረስ የፈጠሩት ሃይማኖት ለበስ ፖለቲካ መስሏቸው ነበር፡፡ የክርስትና ሃይማኖት ግን በርግጥ እነሱ እንዳሰቡት ሃይማኖት ለበስ ፖለቲካ አልነበረም፣ ይሁን እንጂ የሮማን መንግስት የተስፋፊነት መንፈስ የሚቃወም፤ መንገድ ሁሉ ወደ ሮም ያስገባል የሚለውን ውርስ የሚቃወም ነበር፡፡






Wednesday, January 15, 2014

‹‹የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው››(ሉቃ 23:34)






ይህንን ቃል የተናገረው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የእግዚአብሔር ልጅ በተለየ አካሉ ከድንግል ማርያም ተወልዶ እንባቸውን ሊያብስ ነገራቸውን ሊገለብጥ ታሪካቸውን ሊቀይር ከምንም በላይ ሰዎች በኃጢዓት ሞት ተፈርዶባቸው መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ተጭኗቸው ጸጋቸው ተገፎ ከክብራቸው ተዋርደው ነበርና፣ ክብራቸው ይመለስ ዘንድ ጸጋ ያለብሳቸው ዘንድ ሊቁ አትናቴዎስ በትምህርቱ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጆችን የእግዚአብሔር ያደርግ ዘንድ የሰው ልጅ ሆነ›› እንዳለ ሰው ሆኖ ቢወለድ ሰዎች ግን ግብራቸው ክፉ ነበርና በመገለጡ ደስ አላላቸውም ይልቁንም ‹‹የዮሴፍ ልጅ ፣ የጸራቢ ልጅ›› ብለው አምተው አሳሙት ክፉ ስድብንም ሰደቡት ይባስ ብለው ይገድሉት ዘንድ ፈለጉ ጥዋትና ማታም መግቢያ መውጫ አሳጡት ዕለተ አርብ ቀን እስኪደርስም ፈታ አጥተው አሳደዱት፣ በመገለጡ ሐሴት አድርገው በድኅነቱ ታምነው፣ በተስፋው ተስፋ አድርገው ከዋለበት እየዋሉ ካደረባት እያደሩ የቃሉን ትምህርት የሚሰሙትን የእጁን ተአምራት የሚያዩትንም አብረው አሳደዷቸው በስሙም እንዳይማሩና እንዳያስተምሩ ማዕቀብ ጣሉባቸው ነገር ግን እውነት ለጊዜው ትዳፈን ይሆናል እንጂ አትጠፋም፡፡


‹‹ከገሊላ ወደ ማዕዶተ ዮርዳኖስ››





የአበው ቃል ኪዳን ተስፋ የነቢያት ትንቢት ና ሱባኤ ተፈጸመ እግዚአብሔር መተኪያ የሌለውን አንድ ልጁን ላከ እርሱም ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ እርሱ ዳግም በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሻር ይኸውም ዲያብሎስ ነው፣ በሕይወታቸው ሁሉ ስለ ሞት በፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ፣ ከሕግ በታች ሆኖ በሞገስና በጸጋ ቀስ በቀስ አደገ በግዕዘ ሕጻናት በትን ከተማ በናዝሬት ገሊላ ተመላለሰ በተወደደችው ዓመት፣ የተወደደችውን የእግዚአብሔር ዓመት አምላካችንም የሚበቀልባትን ቀን የምስራች ሰበከ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በእሱ ላይ ነውና ለድሆች የምስራችን ይሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀባው ልባቸው የተሰበረውን ጠገነ ለተማረኩት ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን የምስራች ተናገረ፡፡

Monday, January 6, 2014

‹‹በተወደደችው ዓመት››






በተወደደችው ዓመት እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከ የተነገሩ ትንቢቶች ተፈጸሙ የተቆጠሩ ሱባኤዎች ተጠናቀቁ በቤተልሄም ይሁዳ በእኩለ ሌሊት ፀሐይ ፍንትው ብላ ወጣች የተናቁት ሰዎች ከቁጥር የማይገቡት እረኞች የፀሐይን ብርሃን ፈጥነው አዩ ‹‹የሚያከብረውና የከበረው አከበራቸው ብርሃንን ቀድሞ አሳያቸው ስብሐት ለእግዚአብሔር በአርያም ወሠላም በምድር ስምረቱ ለሰብዕ›› በማለት ሰዎችና መላዕክት በአንድ ላይ ዘመሩ፣ የብርሃን አምድ ከሰማይ እስከምድር ተተክሎ ታየ፣ ለወትሮው በሥነፍጥረት ፀሐይ የታዘዘችው በቀን እንድትሰለጥን ነበር ነገር ግን በተወደደችው ሰዓት ጨረቃና ከዋክብትን ተባበረች በእኩለ ሌሊት ለምስጋና መጣች ለመኖሯ ዋስትና ፈጣሪዋ የማይጠልቀው ፀሐይ ባልተለመደ ሁናቴ ተወስኖ አይታለችና፣ ደግሞስ ዳዊት ‹‹ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ›› ብሎ የለ ሰማያት ያለው ሰማያዊ ፍጥረታትን ሰማያትን ጨምሮ እንዲህ ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብትን ነውና የከበረውን ለማክበር መጣች አዎ! የተወደደች ዓመት ስቃይ ያበቃባት መርገም የተደመሰሰባት ፍዳ የተፋቀባት የአመጽ መዝገብ የተገለጠባት መቃብር የተዘጋባት፣ ሞት የተሻረባት ሲዖል ተዘግቶ ገነት የተከፈተባት ምርኮ የተመለሰባት እውነትም የተወደደች ሰዓት የአልቃሾች እንባ የታበሰባት የደስታ ዘመን፣







Thursday, January 2, 2014

‹‹የዓለም ብርሃን ተወለደልን››




‹‹የዓለም ብርሃን ተወለደልን››
‹‹ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃነ››
ልዑለ ቃል ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔር የራቀውን ስላቀረበለት የረቀቀውን ስላጎላለት የመሲሁን መምጣት የክርስቶስን መወለድ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት መወሰን በትንቢት መነጽር ተመልክቶ ሲናገር ‹‹ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃን ዐቢየ ወለእለሂ ይነብሩ ውስተ ጽልመት ወጽላሎት ሞት ብርሃን ሠረቀ ሎሙ›› (ኢሳ 9፡2) በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃንን አየ በሞት ጥላ በጨለማ ሀገር ለኖሩ ሰዎችም ብርሃን ወጣላቸው አለ፡፡