Monday, March 24, 2014

ኢትኀልዩ (አትጨነቁ) ማቴ 6፡25



 
ይህንን የማጽናኛ የዋስትና ቃል የተናገረ በጊዜና በዘመን የሚሸነፈው ራሱም በውጥረት በሃሣብ የሚኖረው ደካማው ፍጥረት አልያም ወንበራቸው የሚገለበጠው ሥልጣናቸው የሚሻረው ምድራዊ ነገስታት ሳይሆኑ የሲኦልን ድል መንሳት አስወግዶ ጨለማውን በብርሃን የገለጠ የሞትን መውጊያ የሰበረ የመኖራችን ምስጢር የነገስታት ንጉስ የገዥዎች ገዥ ሲሰጥ የማይሳሳ ሰጥቶ የማይነሣ ብርቱ መደገፊያና የማይሰበር ምርኩዝ መድኅን ዓለም ክርስቶስ ነው፡፡










ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ስብከቱ የጭንቀትን ትርጉም መንስኤውንና መፍትሔውን አስቀምጦልናል (ማቴ 6፡25-34)፡፡ ጭንቀት ማለት ከመጠን በላይ ማሰብ ማለት ነው ከምንም በላይ ጭንቀት አለማመን ማለት ነው ሕይወትን እንደዛሬ ገጠመኙ የሚፈርድና ራሱን በጣም በማየት አቅም የለኝም የሚል ሰው ለጭንቀት ይዳረጋል ያለማመን መፍትሔው ደግሞ ማመን መታመን ብቻ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ጌታ በሚያስተምርበት ዘመን በዮርዳኖስ ማዶ በይሁዳ የነበረ አንድ ሰው ‹‹አምናለሁ አለማመኔን አርዳው›› (ማር 9፡24) እንዳለ አለማመንን አስወግዶ ኃይማኖትን ማጽናት በሃይማኖት መቆም መጎልመስ ያለማመን መፍትሔ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጭንቀት መንስኤዎችን እንዲህ በዝርዝር አስተምሯል፡፡
1.  ያለንን አለማወቅ
‹‹ስለዚህ እላችኋለሁ ስለነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት ወይም ስለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?›› (ማቴ 6፡25) የእግዚአብሔርን ተአምራት፣ ቸርነትና ከለላ ለማወቅ መጻሕፍት ማንበብ ሳያስፈልግ በራሳችን ላይ የተከናወነውን ተፈጥሮ ማየት ብቻ ይበቃል፡፡ ሰው መሆን ትልቅ ዋጋ አለው ሰው ሆነን መፈጠራችን በልመና ወይም በምርጫችን ያገኘነው ሳይሆን የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡
ማንኛውም ዕቃ የራሱን ዋጋ አያውቅም ዋጋው ያለው በሠሪው ልብ ውስጥ ነው የሰውንም ትክክለኛ ዋጋ ራሱ ሰውየው እንኳ አያውቀውም የሰራው እግዚአብሔር ግን ያውቀዋል፡፡ አንድን ዕቃ ውድ የሚያደርገው የተለጠፈበት ዋጋ ነው ሰውም የእግዚአብሔር ምሳሌ ታትሞበታል ቀራንዮን ስንመለከት ደግሞ የሰው ዋጋው ጎልቶ ይታየናል እሱም አምላካዊ ደም ነው ተፈጥሮአችንን ማለትም ነፍስና ሥጋችንን ስንመለከት ውድ ዋጋ ፈሶብናል ዛሬ ቢደረግልን እንኳ ከተደረገልን አይበልጥም ለዚህም ነው ሐዋርያው ‹‹በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ ያለን›› (1ቆሮ 6፡20) የሚበልጠውን የተቀበልን በሚያንሰው መጠራጠር አይገባንም ማንኛችንም ብንሆን የማንፈልገውን ነገር አንደክምበትም የምንደክመው ለምንፈልገው ነገር ነው እግዚአብሔር ከአፈርና ከሕያዊት ነፍስ ሲፈጥረን ደክሞብናል ይህ ድካሙን አስቦ ነው እንደ ገና በቀራኒዮ የደከመው ነቢዩ ለጌታው አዝኖ ‹‹እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ ስሙ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን? አምላኬን ደግሞ የምታደክሙ›› (ኢሳ 7፡13) ማለቱ ለዚህ ነው፡፡
ከማህፀን ጀምሮ እስከዚህ ዕድሜያችን በችግር በድካማችን በታሪካችን ሁሉ አብሮን ተራራ ወጥቷል፣ ሸሎቆ ወርዷል ታዲያ ይህን ሁሉ ዋጋ የከፈለብን ሊተወን ነውን? በፍጹም አይደለም፡፡ ነቢዩ ኤርሚያስ የእግዚአብሔርን ብርቱ ክንድና ጥበቃውን ባልተረዳበት ዘመን እኔ ብላቴና ነኝ ሲል ‹‹ከሆድ ሳልሰራህ አውቄሀለሁ በማህፀንም ቀድሼሃለሁ›› በማለት ከጥንት ከመሠረቱ እንደሚያውቀው ገልጾለታል፡፡ ክቡር ዳዊትም በመዝመሩ ሠሪያችን እግዚአብሔር ግሩምና ድንቅ አድርጎ ተጠብቦ እንደሠራን ሲገልጽ ‹‹ግሩምና ድንቅ ሆኞ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ ሥራህ ድንቅ ነው ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፈ›› ኤር 1፡5፣ መዝ 138፡14 በማለት በዝማሬ አመስግኗል፡፡
ጭንቀት ሲገጥመን አሳብም ሲወጥረን የምንለው ችግር በትክክል የሆነ ነው? ወይስ ይሆናል የምንለው ፍርሃት ነው? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን አብዛኛው ጭንቀታችን ባልተጨበጠ ነገሮች ላይ ነው ጭንቀት ያለንን ነገር እንዳናይ ይጋርደናል ስለዚህ ያለንን ማየት ያስፈልጋል ሥራ ስናጣ ቢያንስ ሥራ ያማረን ጤና ስላለን መሆኑን ማሰብ ይገባናል ለመጨነቅም አንዱ ነገር ሊኖረን ያስፈልጋል ምንም የሌለው አይጨነቅምና መጨነቃችን በራሱ ባዶ እንዳልሆንን ይመሰክርብናል፡፡
ሕጻን ልጅ ጤንነቱ ካልታወከ በቀር ምን እበላለሁ? ምን እጠጣለሁ? ምን እለብሳለሁ? ብሎ አይጨነቅም ምክንያቱም ስለ እርሱ የሚያስቡ ወላጆች አሉትና እኛም ለእግዚአብሔር እስከ ሽበት ሕጻናቶች ነን የፍቅር ጥገኞች ነን ወላጆች በልጆቻቸው መምህራን በደቀመዛሙርቶቻቸው ንጉሥ በሠራዊቱ ደስ እንደሚላቸው እግዚአብሔር በእኛ ደስ ይለዋል ስለምንበላውና ስለምንጠጣው ደግሞም ስለምንለብሰው እርሱ ያስባልና እርሱ የፈጠረውን የማይጥል ያስቀመጠውን የማይረሣ ነው፡፡ መብል መጠጣችንን ደግሞም ልብሳችንን የሚያዘጋጅልን ክርስቲያን ስለሆንን አይደለም ስለፈጠረን ነው ‹‹ፍጠረኝ ሳይሉኝ ፈጥሬአቸዋለሁ›› ብሎ ያስብልናል፡፡
እግዚአብሔር ስለፈጠራቸው ብቻ የማያኖራቸው ብዙ ሕዝቦች አሉ ‹‹እርሱ በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና በጻድቃንና በኃጢዓተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና›› (ማቴ 5፡45) ‹‹እርሱ ለማያመሰግኑ ለክፉዎችም ቸር ነውና ይመግባቸዋል ይሰጣቸዋል›› (ሉቃ 6፡36) ተብሎ በወንጌል ተመዝግቧል፡፡
አንድ ሕጻን አድጎ ለአካለመጠን ሲደርስ ከወላጆቹ ጥገኝነት ይወጣል፡፡ ያለ ወላጆቹ መኖር የማይችለው ሕጻን ብቻውን መኖር ይችላል አሁንም ግን ያለ እግዚአብሔር ጥገኝነት መኖር አይችልም የእግዚአብሔር መጠጊያ የማያሳቅቅ ራስን ለመቻል የማያሳስብ ነው፡፡
በሕይወትበተሞላውዓለማችንሦስትዓይነትሕይወቶችአሉ፡፡የእፅዋትሕይወት፣የእንስሳትሕይወትናየሰውሕይወትናቸው፡፡የእጽዋትሕይወትልምላሜያቸውሲሆንበመጠውለግይሞታል፡፡የእንስሳትሕይወትደግሞነፍስሲሆንእስካሉድረስብቻይኖኑናሲሞቱያበቃል፡፡የሰውሕይወትግንለባዊነት/አሳቢነት/፣ነባቢነት/አስበንመግለጥ/፣ሕያውነት/ዘላለማዊነት/ያለውነው፡፡ስለዚህየሰውሕይወትበመጠውለግናበመሞትብቻአያበቃምዘላለማዊነው፡፡ሰውንክቡርከሚያሰኙትነገሮችአንዱበውስጡየተቀመጠውይህዘላለማዊነትነው፡፡
ጌታችንወቅታዊስለሆነውስለእጽዋትሕይወትበመናገርየእኛሕይወትየላቀመሆኑንይገልጣል፡፡‹‹ስለልብስስለምንትጨነቃላችሁ? የሜዳአበቦችእንዴትእንዲያድጉልብአድርጋችሁተመልከቱአይደክሙም፣አይፈትሉምነገርግንእላችኋለሁሰሎሞንስእንኳበክብሩሁሉከእነዚህእንደአንዱአልለበሰም፡፡እግዚአብሔርግንዛሬያለውንነገምወደእቶንየሚጣለውንየሜዳሣርእንዲህየሚያለብስከሆነእናንተእምነትየጎደላችሁእናንተማይልቁንእንዴት?›› /ማቴ. 628-30/
እኛለአበቦችአልተፈጠርንምአበቦችግንለእኛተፈጥረዋልእኛለእጽዋትአልተፈጠርንምእጽዋትግንለእኛተፈጥረዋል፡፡እግዚአብሔርለራሳቸውማሰብለማይችሉትአእዋፋትያስባልየተራቆቱመስኮችንምበአበባያለብሳልከእኛአልፎለእኛስለተፈጠትየሚያስብከሆነእኛማየታየንናዘወትርየምንታይፍጥረትነን፡፡ሰሎሞንበባለጠግነቱናበክብሩብዛትሁሉንአድርጓል፡፡ቤቱንበወርቅአስለብጧል፣በሐርምአስኪጊጧል፣የተዋቡልብሶችንለብሷልእርሱበንጉሳዊበጥበባዊናበባለጠግነትክብሩየለበሰውልብስእግዚአብሔርአንዲትአበባንካለበሳትልብስጋርአይወዳደርም፡፡ሰሎሞንበንጉስነቱለራሱተጨንቆያደረገውእግዚአብሔርለአበባውካደረገውጋርቢመዛዘንአይጠጋጋም፡፡
የሰሎሞንልብስከተፈጥሮውጋርተከናወነአይደለምከሰውነቱበላይየሚውልነው፡፡የአበቦችልብስግንከተፈጥሯቸውጋርየተሰራነው፡፡ልብሳቸውምየሚያድግየሚፈካ፣ራስንየሚያድስየክረምትየበጋየሆነሁሉምልብስግንውብናየታወቀዲዛይነሮችእንኳንየማይሰሩት/የማይጠልፉት/ነው፡፡ሸማኔዎችአበቦችንአይተውይሰራሉአበቦችግንየራሳቸውልብስአሏቸው፡፡እኛበንጉሳዊክብርእንኳንለራሳችንብንጨነቅእግዚአብሔርለአበባየተጨነቀውንያህልአይሆንም፡፡እኛለራሳችንከምናስብእግዚአብሔርለአበባያሰበውእንዲህከሆነለእኛያሰበውማእንዴትይልቅ!
ሁላችንምብንሆንበአእዋፋትላይጥናትልናደርግናልንደነቅባቸውእንችላለን፡፡ነገርግንአንድኪሎስንዴእንኳሰፍረንላቸውአናውቅምእግዚአብሔርግንያኖራቸዋል፡፡እነዚህፍጥረታትአይዘሩም፣አያጭዱም፣የማብሰያማድቤት፣የማከማቻጎተራየላቸውም፡፡የሰማይአምላክግንያኖራቸዋል፡፡በእርግጥየሰማይወፎችአይዘሩምእንጂአይሰሩምአልተባለምባይዘሩምምግባቸውንለመልቀምይሯሯጣሉ፡፡እግዚአብሔርየእስራኤልንሕዝብእንደሰማይአእዋፋትአርባዓመትበበረሃመግቧቸዋል፡፡እግዚአብሔርለመስክአበቦችናለሰማይአእዋፋትእንዲህካሰበለእኛማእንዴትያስብልንይሆን?
በማቴ. 625-28 ‹‹ተመልከቱ›› የሚልቃልሁለትጊዜተጠቅሷልማየትብቻአይበቃምመመልከትማስተዋልይገባል፡፡ተመልከቱየተባለውፍጥረታትንነውአእዋፋትየሚያዜሙትከሰውጎጆአጠገብነው፡፡አእዋፋትበእኛደስብሏቸውየሚዘምሩትንያህልእኛደስተኞችአይደለንምዛፎችቀጥብለውቆመዋል፡፡እኛግንኑሮንሰዎችጠላትንእየፈራንአንገታችንንደፍተናል፡፡እነርሱለእኛበመፈጠራቸውኮርተውከቆሙእኛማእንዴትልንጸናይገባል! ሰማይንተመልከቱ፣ጥቁርወይምነጭአይደለምሰማያዊነውጥቁርቢሆንየሚየስፈራነጭቢሆንአዙሮየሚጥልበሆነነበር፡፡እግዚአብሔርግንውብጣራአድርጎልናልሰማይቅርፁእንጂድባብ /ጥላ/ ነው፡፡
በእያንዳንዱፍጥረትውስጥየተጻፈውንምስክርነትብናጠናማንበብለሚችልፍጥረታትንሁሉፊደልናቸው፡፡ነፋሳትንከመዛግብትየሚያወጣደማናትንበሰማያትየዘረጋዝናብንበወቅቱናበጊዜያትየሚሰጥእግዚአብሔርነው፡፡ይህዝናብበሰዎችአስተዳደርሥርቢሆንየቢሮሰራተኞችእስኪፈራረሙክረምቱየሚገባውጊዜውንናወቅቱንአሳልፎጥቅምትላይበሆነነበር፡፡እግዚአብሔርግንከሕይወትጋርየተያያዙነገሮችንበእጅአድርጎታልለሕይወትየሚጠነቀቅእርሱብቻነውና፡፡
ይህሁሉእንክብካቤይህሁሉፍቅርለእኛነው፡፡እንደዚህተወደድንለምንእንጨነቃለን?እንዲህተደርጎልንለምንእንደነግጣለን? አዎየጭንቀታችንመንስኤያለንንአለማወቅነው፡፡
2.     አቅማችንንአለማወቅ
የጭንቀታችንሁለተኛመንስኤአቅማችንንአለዋወቅነውተፈጥሮአችንንብናየውበዓይንእንኳሊታዩየማይችሉባክቴሪያዎችሊያጠቁትየሚችልእጅግደካማተፈጥሮነው፡፡የዓለምንሕዝብበአንደኛደረጃእየፈጀያለውየወባትንኝበዓይንእንኳንሞልታየምትታይአይደለችም፡፡በጣምአቅመደካሞችነን፡፡አቅምየሌለውሰውይገዛል፡፡እኛምአቅመቢሶችስለሆንንኃይለኛውንጌታመጠጋትናለእርሱመገዛትያስፈልገናል፡፡
ጌታችንናመድኃኒታችንኢየሱስክርስቶስ‹‹ከእናንተተጨንቆበቁመቱላይአንድክንድመጨመርየሚችልማነው?››/ማቴ.622/ ብሏልበገዛቁመታችንላይእንኳንማዘዝአንችልም፡፡ረዘምኩብለንማጠር፣አጠርኩብለንመርዘምአይቻለንምበራሳችንላይአቅምከሌለንበሁኔታዎችላይእንዲትአቅምይኖረናል?የገዛጭንቀታችንየያዝነውንነገርካላስተካከለየሌለንንነገርማምጣትእንዴትይቻላል? ብዙስንትነገሮችቢኖሩምመጨነቃችንምትልቁከንቱነገርነው፡፡
ለብዙዘመናትለራሳችንተጨንቀናል፡፡ከእግዚአብሔርበላይግንለራሳችንደግአልሆንምለብዙዘመናትበፍርሃትአምጠናልየሚጎድለውምከመጉደልየሚሆነውምከመሆንአልቀረም፡፡ራሳችንንመርሳትናእግዚአብሔርንማሰብያስፈልገናል፡፡አሊያራሳችንንከመጠንበላይካየነውእንጨነቃለንአንችልምና፡፡እግዚአብሔርንስናይግንእንበረታለን፡፡ጭንቀትለመጣውችግርወለድመክፈልእንጂመፍትሔአይደለምእንደውምስንጨነቅችግሮችመወሳሰብይጀምራሉየውሉጫፍእየጠፋቀጣይቀንምአልታይእያለንይመጣል፡፡ስንጨነቅየመለኮትብርታትይርቀናል እግዚአብሄር ቢያስብልን ይሻላል፡፡
በሕይወታችን ውስጥ ያገኘናቸው ትልልቅ ትርፎች ተጨንቀን ያገኘናቸው አይደሉም መልካችን፣ ቤተሰባችን፣ አገራችን፣ ትዳራችን ሁሉም ሲሆኑ እግዚአብሔር ያሰበልን ናቸው፡፡ በሕይወት ላይ የእኛ ድርሻ ትንሽ ሲሆን እርሱም መቀበል ነው በሕይወት ላይ አብዛኛው ድርሻ የእግዚአብሔር ነው ለምሳሌም አገራችንን እንወዳለን፣ ባንዲራዋንም ስናይ እንባችን ይመጣል ቤተክርስቲያንና ቤተመንግስት በዚህ ባንዲራ ያጌጣሉ በየቲሸርታችን ላይ ሳይቀር ባንዲራውን አስቀርጸናል አገራችንን ግን የሰጠን ማን ነው? ስንል እግዚአብሔር ነው ቤተሰባችንን በጣም እንወዳለን ያውም ሳይታወቅብን፣ የሌለንው ሰው ችግር ስንሰማ ግን ተራራ ቢያህልም ቀላል ነው እንላለን የቤተሰባችን ችግር ግን የስናፍጭ ቅንጣት ብታህልም ዕረፍት ትነሣናለች ይህንን ቤተሰብ የመረጠልን ማነው? እግዚአብሔር ነው ራሳችንን በጣም እንወዳለን ሰፊ ቤት ቢኖረን የቁም መስታወት ተክለን ራሳችንን ለማየት እንመኛለን ራሳችንን የሰጠን ሰው ያደረገን በእጆቹ ያበጃጀን በመዳፉ የቀረፀን ግሩምና ድንቅ አድርጉ የፈጠረን (መዝ 118፡78) እግዚብሔር ነው የእግዚአብሔር አሳብ ይበልጣል እርሱ ያሰበውም ይስማማናል አገራችን ቤተሰባችንና ራሳችን ተስማምቶን ወደነዋልና፡፡ እግዚአብሔር የመረጠው የምንወደው ነው አሁንም እየሆነ ያለው የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ ደስ ሊለን ይገባል፡፡
እያንዳንዱ ጉዟችን የእሾህ ጉዝጓዝ ያለበት የማይረገጥ ጎዳና ሆኖብን ይሆናል፡፡ ክርስቶስን ከሆንን በኋላ የምንኖርበት ሥፍራ በፈተና የታጠረ ሆኖብን ይሆናል ባለጋሮቻችን ስለበላን፣ ስለጠጣን፣ ስለለበስን ሳይሆን ምድር ለተሸከመችን ይከብዳቸው ይሆናል፡፡ ግን በሕይወት አለን አውጥቶ የሚያገባን ደግሞም የሚያኖረን እግዚአብሔር ነውና ተጠልተንም፣ ተሰደንም ሰዎች ሳይቀበሉንም ያኖረናል ሕይወትን የኃያላን ጉልበት የነገስታት ሥልጣን አያቆማትም የሕይወት ባለቤት እግዚአብሔር ነውና፡፡ ከራስ ፀጉር ቢበዛ ጠላቶቻችንን ለማስተናገድ አቅም የለንም ነገር ግን አቅም ካላቸው በላይ እየኖርን ነው የማይታየው እግዚአብሔር የሚታየውንና የማይታየውን ጠላታችንን ይመልስልናልና ለዚህ ሳይሆን ይቀራል ሐዋርያው ‹‹በአሸነፈው በእግዚአብሔር ከአሸናፊዎች ሁሉ እንበልጣለን›› ያለው፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል 10፡29-31 ‹‹ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አቅወድቅም የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቁጥሮአል እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ›› ይላል አስደናቂ ዋስትና፣ የማይደፈር ከለላ ነው፡፡ ድንቢጦች ትንንሽ ቢሆኑም በገበያ ሥፍራ ሁለቱ በአምስት ሳንቲም ይሸጣሉ ዋጋው ምንም ትንሽ ቢሆን ዋጋ አላቸው እኛ ከድንቢጦች ይልቅ ዋጋ አለን፡፡ራሳችንን ብናውቀውም የራስ ጠጉራችን ቁጥሩ ምን ያህል መሆኑን ግን አናውቅም የሰማይ አባት ግን የራሳችንን ጠጉር ቆጥሮታል እኛ አንዲቱ ጠጉር ሳይሆን አስሩ ቢነቀል አይጨንቀንም ያለ ሰማዩ አባታችን ፈቃድ ግን አንዲቱ ጠጉራችን አትነቀልም፡፡
የሰውነት ክፍሎቻችንን ካየናቸው ያላየናቸው ይበዛሉ፡፡ እነርሱን የሚያይና ትክክለኛ ሥራቸውን እንዲሰሩ የሚያደርጋቸው እግዚአብሔር ነው በእውነት የጭንቀታችን መንስኤ አቅማችንን አለማወቅ ነው ልብና ኩላሊታችንን ያላየን እነርሱን የማዘዝ አቅም የሌለን ሰዎች ነን ሁሉ ከሚገዛለት ጌታ ጭንቀታችን እንዲገዛ እኛ አስቀድመን ለእግዚአብሔር እንገዛ፡፡
3. የሚበልጠውን ክብር አለማሰብ
ጌታችን ሲናገር ‹‹ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት ጽድቅንም ፈልጉ ሌላው ሁሉ ይጨመርላችኋል›› (ማቴ 6፡33) ብሏል፡፡ መንግስቱን ሁሉ መንግስተ ሰማያትን ጽድቅን ብሉ የዘላለም ሕይወትን እሹ ሌላው ሁሉ ምድራዊ ኃላፊ ጠፊ ነውና በሌላው መንግስቱን ብሎ ኃይማኖትን ጽድቅን ብሉ ምግባርን ማለቱ ነው፣ አስቀድማችሁ ኃይማኖታችሁን አጽኑ ምግባራችሁን አቅኑ ወይም ኃይማኖትን ከምግባር አስተባብራችሁ ያዙ ሌላው ሁሉ እንደ ዳረጎት ይጨመርላችኋል ሲል ነው፡፡
ዋነኛውና ቀዳሚው ነገር መንግስቱና ጽድቁ ወይም የዘላለም ሕይወት ነው የዚህ ዓለም ነገር ግን ተጨማሪ ነው፡፡ የሰው የጸጋ ደመወዝ የዘላለም ሕይወት ነው፣ የዚህ ዓለም ትርፍ ግን ተጨማሪ ወይም ዳረጎት ነው ዋስትና የሚፃፈው ደግሞ በደመወዝ እንጂ በተጨማሪ (ዳረጎት) አይደለም፡፡ የወዲያኛው ዓለም እንጂ ይህ ዓለም ዋስትና የለውም ለዚህም ነው ቅዱስ ዳዊት ‹‹በልቡ የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው›› (መዝ 84(85)፡5) በመሆኑም የሚቀድመው ካልቀደመ የሚከተለው ሥፍራውን አይዝም አሰንደኛን ሁለተኛ ላይ ወስደን ከኖርን፣ ሁለተኛውን አንደኛ ላይ አምጥተን ከኖርን ከትርፍ ኪሳራው ያመዝናል፡፡ ምክንያም ‹‹ለሥጋ ማሰብ ሞት ነው›› ተብሎ ተጽፏልና፡፡
በዚህ ምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች ነን፣ ኑሯችንም የኮንትራት ሠራተኞችን ይመስላል፡፡ ጊዜያችን ሲያበቃ ዘመናችን ሲፈጸም መንገደኞች ነን በመሆኑም የምደሩ ባይሳካልን ለሰማያዊ ለዘላለማዊ የሚሆን ስንቅ ካዘጋጀን ባለተስፋ ነን ክርስቲያን የምድሩ ጎጆ የኮንትራት ቤት ቢፈርስበት በሰማይ የማይፈርስ አገር አለው ነገር ግን ሐዋርያው ‹‹እኛ ሀገራችን በሰማይ ነው ከሰማይ የሚመጣውንም እንጠብቃለን›› (ፊልጵ 3፡19) የሚኖረው እስከጊዜው ነው፣ የቀጠረው ወዳጅ አለ፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለማይፈርሰው ማደሪያ ከተረከ በኋላ የክርስቶስ መልዕክተኞች እንደሆንን ይናገራል (2ቆሮ 5፡20) ክርስቲያን የክርስቶስ አምባሳደር ነው አምባሳደር አገሩን ወክሎ ከአገር ርቆ የሚኖር ነው ዘክርስቲያንም አምባሳደር ከሆነ የሚኖረው ከአገሩ ርቆ ነው ማለት ነው አምባሳደር ወደ አገሩና ወደ መንግስቱ የሚጠራበት ጊዜ አለ እስከዛው ድረስ የአምባሳደርነት ሥራውን እየሠራ ጥሪውን ይጠባበቃል በእውነት የጭንቀታችን አንዱ መንስኤ የሚመጣውንና የሚበልጠውን ክብር አለማሰብ ነው ፍርድ የሚታወቅበት እውነት የበላይ የሆነባት ከገቡ የማይወጡባት ጌታ ለወዳጆቹ ያዘጋጀው አገር አለችን በዚያ መዝራት ማጨድ፣ መውጣት መውረድ ልፋት እንግልት የለም ይህችን አገር የሥጋ መጋረጃ ሲገለጥ እናያታለን፡፡
4. የነገን ማሰብ
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል›› (ማቴ 6፡34) ብሏል፡፡ በሰው ሕይወት ውስጥ ነገ ሰላም ሳይሆን ረባሽ ቃል ነው ብዙዎቻችን ስለ ነገ በማሰብ ደክመናል፡፡ የማናውቃት ነገ እጅግ ታስጨንቀናለች ነግ ክፉ ሊመጣ ይችላል፣ ነገ ደግ ሊመጣ ይችላል ግን እርግጠኛ አይደለንም ስለማናውቀው ነገር መጨነቅ ነገ ይባላል፡፡ የሰው ልጅ በነገ ፍርሃት ተይዟል የሰው ዕድሜ የሚያልቀው ያለፈውን በማመስገን አሊያም በመፀፀት፣ ያለውን በማማረር፣ የወደፊቱን ደግሞ ምን ይመጣብኝ ይሆን? ብሎ በመጨነቅ መሆኑ ያሳዝናል የሰው ልጅ የሚኖረው በዘትላንትናና በነገ መካከል ታፍኖ ነው ሁሉም ሰው በጣም የሚጨነቀው ዛሬ አይደለም ነገ ነው ነገ ግን የእግዚአብሔር ምስጢር ናትና ማንም አያውቃትም ሰነገ ዘላለም ናትና ላይደርስበት ይችላል፡፡
የሚገርመው የሰው ልጅ ነገን ለመኖር እርግጠኛ ሆኖ የሚጨነቀው ነው፡፡ የሚገርመው ዘግን ነገ ብዙ ተአምሮች አሉ ነገ ክፉ ይመጣል ብሎ መጨነውም ሆነ ነገ አገኛለሁ በምንለው ነገር መመካት ተገቢ አይደለም፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ ‹‹ቀን የሚያመጣው ምን እንደሆነ አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ›› ምሳ 27፡1 ይላል፡፡
ዛሬን ከተቀደስን ግን ነገ ድንቅ ናት ትላንት ዘር ነው ዛሬ ቅጠል ነገ ፍሬ ነው ክርስቲያን ‹‹ስለነገ ትጨነቃለህ ወይ›› ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ ሊሆን የሚገባው ‹‹ዛሬን በትክክል ከኖርኩ ለነገ ስለሚተርፈኝ ለነገ አልጨነቅም›› የሚለው ነው አዎ ዋናው ነገር ዛሬን በትክክል መኖር ነው ጌታችን ‹‹ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋልና›› ብሏል (ማቴ 6፡34) የቀኑ ክፋት የተባለው የቀኑ ግዳጅ ነው እያንዳንዱ ቀን የራሱ የሆነ የቤት ሥራ አለው የዛሬን የቤት ሥራ ዛሬ ሥሩ ማለቱ ነው ስለ ነገ ብንጨነቅም ጭንቀት እንጂ የነገ ትክክለኛ የቤት ሥራ ምን መሆኑን አናውቅም ስለ ነገ ያለን ግንዛቤ ከግምት አያልፍም የዛሬን ጉዳይ መወጣት መቼ አነሰንና ነው ስለ ነገ የምንጨነቀው? በእውነትም ሁሉም ነገር እንደ ስጋታችን አይደለም፡፡ ትላንትና ላይ ዛሬ ነገ ነበረች ነገር ግን ዛሬ እንደፈራናት ሳይሆን መልካም ቀን ነች፡፡
ከሰዓቱ በፊት ሁሉም ነገር ከባድ ነው፣ ኃይል ግን በጊዜው ይመጣል ስለ ዛሬ ስናስብ የማይጨዘንቀን ስለ ነገ ስናስብ ግን የሚጨንቀን ለምንድን ነው? ብለን ስንጠይቅ መልሱ ዛሬ ላይ ስንደርስ ዛሬን የሚያኖር ኃይል ከሰማይ ተልኮልናል ነገ ላይ ግን አልደረሰንም ስለዚህ ነገን የሚያውል ኃይል አልመጣም፡፡ ስለ ነገ ያለን ሐሳብ በራሳችን ጫንቃ ላይ ብቻ ስለሚያርፍ ያስጨንቀናል ሁሉም ነገር ግን በሰዓቱ ቀላል ነው፡፡
ስ ነገ ማሰብ ካስፈለገን ግን ዛሬ ክፉ ብሠራ ነገ መከራ እቀበላለሁ ዛሬ በወንጌል ካላመንኩ ነገ ገሀነም እወርዳለሁ ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው ሰው ግን ስለ ነገ የሚያሳስበው ያው ሆጉ ነው፡፡ ሆዱ እንዳይጎድል ኅሊናውን ያጎድላል ሌባ ነፍስ ገዳይ የሚሆነው ስለ ነገ በመጨነቅ ነው ትልልቅ ሌቦች አገር ንብረት የሚያሸሹት ነገ ተረጋግተው ለመኖር ነው ጠብ ለማይል ኑሮ ሰርቀን ቀማን ኑሮም መጎደሉን አላቋረጠም፡፡
የጭንቀት መፍትሔዎች
ሀ/ ኀሳብን በእግዚአብሔር ላይ መጣል
ከጭንቀት መፍትሔዎች ዋነኛውና አንዱ እግዚአብሔር እንደሚያስብልን በማመን ሃሣብን ሁሉ በእርሱ ላይ መጣል ነው እግዚአብሔር የፈጠረውን የማይረሣ አምላክ ነውና እርሱ ያስብልናል
‹‹እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን በእርሱ ላይ ጣሉት›› (1ጴጥ 5፡7)
ለ/ እግዚአብሔር እንደሚያስብልን እንደማይተወን በሙሉ ልብ ማመን
እግዚአብሔር ስለ እኛ ያስባል እንኳንስ እኛ በክርስቶስ ክርስቲያን ተሰኝተን ስሙን ለምንጠራው እርሱ ለማያምኑትም የእርሱ ፍጥረት ናቸውና ያስባል እርሱ ስለ እኛ የሚያስብ ከሆነ መጨነቅ አይገባንም አንድ ሰው የሚይዘውን ዕቃ ሁለት ሰው ከያዘው ይበልጥ ይከብዳል፡፡ ስለዚህ ለእግዚአብሔር በጸሎትና በምስጋና መተው ያስፈልጋል
‹‹እርሱ በክፍዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፣ በጻድቃንና በኀጢዓተኞችም ላይ ዝናምን ያዘንባልና›› (ማቴ 5፡45) (ሉቃ 6፡35)
‹‹በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁአዕምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል›› (ፊልጵ 4፡6-7)
ሐ/ ለእግዚአብሔር የሰጠነውን ዳግም አለማንሣት
ሐሳባችን በእግዚአብሔር ላይ ከጣልን፣ እርሱ ያደርገዋል ብለን ከተማመን በኋላ መጠራጠርና በሁለት አሳብ ማነከስ አያስፈልግም ‹‹ትካዜህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል እርሱም ይደግፍሃል›› (መዝ 54፡22) ለእግዚአብሔር ከሰጠን በኋላ በእምነት ማረፍ ይገባል፡፡ ‹‹ዕረፉ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ዕወቁ›› (መዝ 46፡10)
መ/ ቢሆንም ባይሆንም የጌታ ፈቃድ ይሁን ብሎ በእምነት ዝም ማለት ያስፈልጋል
‹‹ሙሴ ሕዝብ እስራኤልን በዘጠኝ ጽኑ ተአምራት በአስረኛ ሞተ በኩር በአስራ አንደኛ ስጥመተ ኤርትራ ባሕር ከግብፅ የባርነት ቀንበር ካወጣቸው በኋላ ጉዞ ጀመሩ ነገዘር ግን ትንሽ እንደተጓዙ ያልጠበቁት ነገር ገጠማቸው ከፊታቸው በዋና የማይሞከረው የቀይ ባሕር ከኋላ ፈርኦን ሠራዊቱን አስከትሎ መልሶ ባሪያ ልያደርጋቸው ዘንድ ይከተላል፣ ግራና ቀኝ ሊወጡት ሊቧጥጡት ማይችሉት የፈርሆት ተራራ፣ ግራ ገባቸው ጨነቃቸው በሙሴም ላይ አጉረመረሙበት በዚህ ጊዜ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ሕዝቡን ‹‹›አትፍሩ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ›› (ዘጸ 14፡13)  ነበር ያላቸው ክርስቲያን መቆም ያስፈልገዋል (በእምነት መጽናት) ፈጥሮ አይጥለኝም ስለ እኔ ነፍሱን ሰጥቶ ሌላውን አይነሣኝም ቢከለክለኝ እንኳ ነፍጎኝ ሳይሆን፣ ጠልቶኝ ሳይሆን ለዓላማ ነው ብለን ማመን ይገባናል፡፡ ‹‹ሶስቱ ወጣቶች አናንያ አዛርያና ሚሳኤል ለሰማዕትነት ሲዘጋጁ አልተጨነቁም ይልቀሱንስ በእምነት በመጽናት ንጉሡን እንዲህ ነበር ያሉት›› ‹‹ቢያድነንም ባያድነንም እግዚአብሔር አምላካችን ነው›› (ዳን 3፡18) ባያድነንም ማለታቸው በሰማዕትነት ማለፋችን ለእግዚአብሔር ክብር ለሆነ የጌታ ፈቃድ ይሁን ማለታቸው ነበረ፡፡
እንግዲህ ብዙ ዘመን የተሸነፍንበት የተጨነቅንበት ይበቃል መጨነቅ የእግዚአብሔርን ፍቅሩን፣ ተስፋውን፣ ሀይሉን መጠራጠር መሆኑን፣ ከምንም በላይ መጨነቅ ኀጢዓት መሆኑን አውቀን ንስሐ መግባት ያስፈልገናል ወገኖቼ ኑሮን የጀመርነው እኛ አይደለንም ብዙ ትውልድ አልፏል፡፡ የተሄደበት መንገድ ደግሞ አያስጨንቅም በችግር የሞተ ሰው ቢኖርም ጭንቀት ግን ከችግሩ በፊት ይገድላል በፍርሃት ዘጠኝ ጊዜ ከመሞት አንዱን ሞት አንድ ጊዜ መቀበል የእምነት ጀግንነት ነው አትጨነቁ ያለ አምላክ በዙፋኑ አለ እርሱ የታመነ ነውና በተስፋ እናምልከው
ወስብሃት ለእግዚአብሔር

ዋቢ:-

(አትጨነቁ)
መጽሐፍ ቅዱስ(81)
በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ

No comments:

Post a Comment