Monday, March 31, 2014

‹‹በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን››ክፍል ፪




‹‹ስለ መተላለፋችን ቆሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀ›› ኢሳ 53፡6
ባለፈው ጊዜ የነቢዩ የኢሳይያስን መጽሐፍ መሠረት አድርገን የጌታችንን የመድኀኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ሕማም መከራ መስቀል ለማየት ጀምረን ነበር፡፡ እሱ ጥልቅ በሆነ ፍቅሩ ስለወደደን መተያ በሌላት ነፍሱ ተወራርዶ አዳነን፣ ነቢያት በትንቢት መጽሐፋቸው፣ ሐዋርያት በስብከታቸው ስለ ፍቅር አስተምረዋል እሱ ግን ፍቅርን በተግባር ገለጠው፣ እጆቹንና እግሮቹን በመስቀል አስቸነከረ ይህን ያህልም እወዳችኋለሁ ብሎ ነፍሱን ሰጠ፣ ፍቅርንም በተግባር ሰበከ እኛም አርአያውንና ፈለጉን እንከተል ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነውና፡፡ በፍቅር እንሁን…..ብለን ነበር ክፍል አንድን የፈጸምን ቀጣዩን ክፍል ደግሞ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን ጀመርን፡፡


Friday, March 28, 2014

አንተ ካልፈረድህባት እኔ ማነኝ?




 


ጌታ ሆይ አንተ ብቻ እውነተኛ ዳኛ ነህ፡፡ ሰው ውጪን ይመለከታል አንተ ግን ውስጥን ትመረምራለህ፡፡ ልብ የመከረውን ህሊና የወጠነውን ታውቃለህ ሰው ላይ ላዩን አይቶ ይፈርዳል፡፡ አንተ ግን የልቦናን ጥልቀት አይተህ ትፈርዳለህ እንደ ሰው ቢሆን አይሁድ ወደ አንተ እያዳፉ ያመጧት ሴት ተወግራ ትሞት ነበር፡፡ ኸረ እንደ ሰውማ ቢሆን ማን ይቆም ነበር? ሕግን የምትሰጥም የምትፈርድም አንድ አንተ ነህ ልታጠፋም ልታድንም የምትችል አንድ አንተ ነህ ታዲያ እንዲህ ከሆነ እንደ እኔ ላለው ሰው በሌላው ይፈርድ ዘንድ ማን ሰጠው?

‹‹በእርሱቁስልእኛተፈወስን››




ክፍል 
‹‹ነስአ ደዌነ ወረ ሕማምነ›› (ኢሳ 53፡4)
‹‹ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንን ተሸከመ››
          ልዑለ ቃል ኢሳይያስ በትንቢት መጽሐፉ ደረቅ ሐዲስ እየተባለ በሚጠራው ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ ምስጢሩን ስለገለጸለት የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ መስቀል በትህትና መንፈስ በመሆን መዝግቦልናል፡፡
ሙሴ በምድረበዳ እባብን እንደሰቀለ እንዲሁ በእሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ሊሰቀል ይገባዋል፡፡ (ሐዋ 3፡14) ተብሎ እንደተፃፈ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ በዘመኑ ፍጻሜ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ከሰማየ ሰማያት ወርዶ መለኮታዊ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ሥጋ በመልበስ ፍጹም ሰው በመሆን በተዋሕዶ ከበረ፡፡
ከዚህም የተነሳ የማይራበው ተራበ፣ የማይጠማው ተጠማ ኅይለኛው ደከመ፣ የወደቁትን የሚያነሳ እሱ ወደቀ፣ እውነተኛ ዳኛ ፈታሒ በርትዕ ሆኖ ሳለ በአይሁድ ተከሶ እንደ ወንጀለኛ በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡




Tuesday, March 25, 2014

ዘወትር ይህንን አስታውስ




·         ደካማነትህን አስታውስ ጠንቃቃ እንድትሆንና አንተን ከሚያጠፋህ ከትዕቢትና ከሐሰት ክብር እንድትጠበቅ ያደርግሃል፡፡
·         እግዚአብሔር ለአንተ ያለውን ፍቅር አስታውስ የምስጋና ሕይወት እንድትኖርና እምነት በልብህ እንዲያድግ በእግዚአብሔር ሥራና ፍቅርም እንድትመካ ያደርግሃልና፡፡

ያዘዘን የትኛውን ነው? ከባድ ነው?



ያዘዘን የትኛውን ነው? ከባድ ነው?
እውን እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ለአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የሰጣቸው ትዕዛዛት ከባዶች ናቸው? በመጀመሪያ አንድ ነገር ማየት ጌታ ሲመጣ የማይጠይቀን ምድን ነው? ጌታ ሲመጣ በምድር ላይ ምን ያህል ቤት እንደሰራን አይጠይቀንም ግን በትንሽም ጎጇችን ብትሆን እንግዳ እንደተቀበልን ይጠይቀናል፡፡

Monday, March 24, 2014

ኢትኀልዩ (አትጨነቁ) ማቴ 6፡25



 
ይህንን የማጽናኛ የዋስትና ቃል የተናገረ በጊዜና በዘመን የሚሸነፈው ራሱም በውጥረት በሃሣብ የሚኖረው ደካማው ፍጥረት አልያም ወንበራቸው የሚገለበጠው ሥልጣናቸው የሚሻረው ምድራዊ ነገስታት ሳይሆኑ የሲኦልን ድል መንሳት አስወግዶ ጨለማውን በብርሃን የገለጠ የሞትን መውጊያ የሰበረ የመኖራችን ምስጢር የነገስታት ንጉስ የገዥዎች ገዥ ሲሰጥ የማይሳሳ ሰጥቶ የማይነሣ ብርቱ መደገፊያና የማይሰበር ምርኩዝ መድኅን ዓለም ክርስቶስ ነው፡፡









‹‹የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱ ምንድን ነው?›› (ማቴ 24፡3)




ይህንን ጥያቄ የጠየቁት ለጊዜው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዋለበት የዋሉት ካደረበት ያደሩት የእጁን ታምራት ያዩት የቃሉን ትምህርት የሰሙት ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ ከደብረዘይት አቀበት ቁልቁል በማለዳ ፀሐይ የሚያብረቀርቀውን የኢየሩሳሌምን ከተማና በውበቱ እጅግ ያማረውን የዘሩባቤልን ሕንፃ ቤተመቅደሱን በመልካም ድንጋይና በተሰጠው ሽልማት እንዳጌጠ ሲነጋገሩ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህ የምታዩት ሁሉ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ የማይቀርበት ዘመን ይመጣል ባላቸው ጊዜ ነበር ‹‹መምህር ሆይ ይህ ሁሉ መቼ ይሆናል?›› ይህስ ይሆን ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድን ነው? ያሉት፡፡ (ማር 13፡3)



Tuesday, March 18, 2014

የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላ ሀሳቦችን ማን ያስተውላል?




ዲያብሎስ የብርሃን መልአክ መስሎ በመቅረብ ሰውን ማሰናከልና ሰውን መጣል ትልቁ ሰውን የሚዋጋበት መንገድ ነው፡፡ ወንጌልም ይህን ያረጋግጥልናል 2 ቆሮ 1114 ይሁን እንጂ ብርሃንን የተጎናጸፈ ጨለማ መንፈሳዊነትን የተላበሰ ስጋዊ ሀሳብና ምክርን ጠላት በሕይወታችን ምን ያህል ጊዜ አቅርቦልናል? እንደነዚህ ያሉ ሀሳቦች የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላ ሀሳቦች ሊባሉ ይችላሉ፡፡

Saturday, March 15, 2014

‹‹ለክፉው ዘመን የማምለጫ መርከብ››




ንዋየ ኅሩይ ቅዱስ ጳውሎስ ዘመኑን ዋጁ ይላል በተለይም ክርስቲያኖች የዓለም ብርሃን የዓለም ጨው ተብለናልና በውጭ ባሉት ዘንድ በጥበብ እየተመላለስን ዘመኑን ልንዋጅ ይገባል፡፡ ያለንበት ዘመን ደግሞ እውነት በሐሰት የተዋጠበት ግፈኞች ደም አፍሳሾች የበዙበት ፍርድ የተጓደለበት ግብረ ሰዶማዊነት በዓለም ላይ ያለ ዕፍረት የሚሠራበት፣ ትዕግስት ትህትና፣ ይቅርታ፣ ከሰዎች ጠፍቶ ትዕቢት፣ ጭካኔ ፣ ቂም በቀል የነገሠበት ክፉ ዘመን ነው ‹‹ለዚህም ነው ነቢየ እግዚአብሔር ሚክያስ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ ከዚያም አንገታችሁን አታነሱም ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም›› (ሚክ 2፡3) በማለት ስለዚህ ጉቦኛ፣ ግፈኛ፣ አመንዝራ አላስተዋይ ትውልድ ይናገራል፣


Friday, March 14, 2014

ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥(ኤፌ5:32)




 

 

ምስጢረ ተክሊል


ተክሊል የሚለው ቃል ከለ ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም አከበረ ለየ ቀደሰ ለትልቅ ዓላማ ክብር አበቃ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ተክሊል ማለት ክብር ማለት ነው፡፡ በእግዚአብሔር የሚያምኑ ወንድና ሴት በካህናት ሥርዓተ ጸሎት ሁለቱ አንድ የሚሆኑበት ምስጢር፣ በሚታይ አገልግሎት የማይታይ ጸጋ የሚቀበሉበት ምስጢር ነው፡፡




Thursday, March 13, 2014

የኋላውን እየተውን ወደፊት መጓዝ



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
 


ልጄ ሆይ እነሆ በመንፈሳዊ ሕይወትህ ወደ ፊት እንዳትጓዝ ተብትቦ የያዘህ ብዙ ያለፈ የትዝታ ገመዶች ይኖራሉ፡፡ እነዚህም በጎም ሆነ ክፉ ትዝታዎች ሊሆኑ ይችላሉ አስተውል ተደርገው ወይም ሆነው ያለፉ ናቸው፡፡ ነገር ግን በልብህ ውስጥ ስላሉ ስትተኛ ስትነሳም ስትቀመጥም ስትሄድም ከአንተ ጋር ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዘወትርም ይታሰቡሃል ታዲያ ያለፈውን በጎም ይሁን ክፉ ስራህን እያሰብክ ባለፈው ታሪክህ ተዘፍቀህ የምትኖር ከሆነ ወደ ፊት እንዴት መጓዝ ይሆንልሃል?


Monday, March 10, 2014

‹‹ዓይኖችህ ከሚያዩት የተነሣ ዕብድ ትሆናለህ›› (ዘዳ 28፡34)






‹‹ዓይኖችህ ከሚያዩት የተነሣ ዕብድ ትሆናለህ›› (ዘዳ 28፡34)
እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት በሙሴ በኩል ለርስቱ ለተጠሩ ለበኩር ልጆቹ ለእስራኤል ትዕዛዙን ይጠብቁ ዘንድ ሥርዓቱን ያደርጉ ዘንድ ሰው ሆነው ለተፈጠሩበት ዓላማ ይኖሩ ዘንድ በግልጽ ተነግሯል፡፡
‹‹እስራኤል ሆይ ዝም ብለህ አድምጥ ዛሬ የአምላክህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆነሃል ለአምላክህም ለእግዚአብሔር ቃል ታዘዝ ዛሬም የማዝዝህን ትዕዛዙን ሥርዓቱን አድርግ›› (ዘዳ 27፡10-26)




Monday, March 3, 2014

በሰውም በእግዚአብሔርም ፊት መልካሙን አስብ



በሰውም በእግዚአብሔርም ፊት መልካሙን አስብ
ለልቤ ከልቤ

ልቤ ሆይ ሃላፊ አለም ሩጫው እሰኪ ይብቃህና ጥቂት አረፍ ብለን የውስጣችንን እንነጋገር፡፡ ልቤ ሆይ አንደው ጾምን የምትጾምበትን እውነተኛ ምክንያት ንገረኝ? በአካባቢህ ያሉት ሰዎች ስለሚጾሙ? ስርዓተ ቤተክርስቲያን ስለሆነ ብቻ ነው? ጽዋሚ ለመባል? ቁመናህንስ ለመጠበቅ ይሆን? እሺ ደግሞስ መጣብኝ ወይስ መጣልኝ ነው የምትለው? በቅበላ ጊዜስ በጾም ውስጥ ሥጋ እንዳያምርህ ጥሩ አድርገህ ነው አምሮትህን የምታወጣው? ገና ሳይገባ የሚፈታበትን ቀን ቆጥረኸው ይሆን? እንጃ! ብቻ መልሱን አንተው ታውቀዋለህ፡፡ የምወድህ ልቤ ሆይ እንዲያው እውነተኛውን ጾም ከማየታችን በፊት ዳግም እስኪ ጥቂት ልጠይቅህ? ሰው የደሃውን ጩኸት እንዳይሰማ ጆሮውን ደፍኖ ቁርሱን መብላት ቢተው ምን ይረባዋል? ከልቡ መዝገብ ክፉን ሳያወጣ ወደ ውስጡ ምግብን ማስገባት ቢያቆም ለሰው ምን ይበጀዋል? በአይኑ ከንቱን እያሳደደና እያየ ጾምሁ ቢል እንዲህ ያለውን ሰው ከሰማያውያን ማን ያምነዋል? ይህ ሁሉ ለታይታ የሚሆን የውጭ ብቻ አይደለምን?