ይህንን የምስራች ቃል ያበሰሩ ከምስራቃዊ
ኢየሩሳሌም አቅጣጫ ከዳዊት ከተማ በቤተልሔም መንደር የነበሩ እረኞች ናቸው፡፡ (ማቴ 2÷2፣ ሉቃ 2÷5) እነዚህ የቤተልሔም
በግ ጠባቂዎች ቀድሞ ያላዩትን በማየታቸው ሰምተው የማያውቁትን ጥዑመ ዜማ በመስማታቸው የደስታ ጸዳል በፊታቸው በራ
፡፡ ልባቸው የመላዕክትን ቋንቋ ለመስማት በሐሴት ተሞልታለችና ዝማሬያቸው አጥናፍ አቋርጦ ተሰማ፣ ከወዲያኛው ሀገር
ወዲህ አስተጋባ የእረኞቹ ቅላጼ እስከ ሄሮድስ ቅጽረ መንግስት ድረስ ዘልቆ በመግባቱ የልደቱ ዜና የጠላትን ወረዳ አስጨነቀ
ሽብርና ትርምስ ግርግርንም ፈጠረ የመምጣቱን ነገር በጽናትና በጉጉት ሲጠብቁ ለነበሩት ግን የደስታ ቀን የሐሴት ዘመን
የተወደደች ዓመት ሆነ፡፡ በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፣ በቤተልሔም የብርሃን አምድ ተተከለ መላዕክት የእረኞችን ፍርሃት አርቀው
ለዝማሬ በአንድ ላይ ቆሙ… ስብሐት ለእግዚአብሔር በአርያም ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብዕ" የተራራቁት ተቀራረቡ የተጣሉት ታረቁ ለዘመናት ተጋርዶ
የነበረው የጸብ ግርግዳም ፈረሰ "እርሱ ሰላማችን ነውና ሁለቱን አዋሐደ" (ኤፌ 2÷14) (ኢሳ 9÷2)፡፡
Tuesday, December 23, 2014
በእሳትና በውሃ መካከል አሳለፍከን(መዝ65/66:12)
ይህንን ቃል የተናገረ ልበአምላክ ቅዱስ
ዳዊት ሲሆን ለጊዜው የሕዝበ እስራኤልን ከግብፅ ምድር መውጣት አስመልክቶ ተናግሮታል፡፡ እስራኤል ከ430 ዓመት የግብፅ ስደትና
የባርነት ኑሮ ቢከብዳቸው መከራው ቢበዛባቸው ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡ በተለይ የልጆቻቸው ሐዘን ልባቸውን
የሰበረው ራሔልና መሰሎቿ የእስራኤል እናቶች እንባቸውን አፍስሰው ወደ መንበረ ፀባኦት ወደ እውነተኛው ዳኛ ወደ እግዚአብሔር
ጮኹ "የአምብርሃምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ ሆይ ወዴት
አለህ? አብርሃምን ዘሩን ያበዛህ በዘርህ ምድር ይባረካል ብለህ ተስፋ የሰጠህ ይስሐቅንም የታደግህ ያዕቆብንም እንደ መንጋ
የምትጠብቅ እረኛችን እግዚአብሔር ሆይ እስከመቼ ፈጽመህ ትረሳናለህ? እያሉ አብዝተው ተማጸኑ፡፡
Monday, December 15, 2014
የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ስለ ክርስቶስ ስለ አንዲት ሃይማኖት ያደረጉት መንፈሳዊ ተጋድሎ
ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ!!! ሮሜ 13፡7
አባታችን በሃይቅ ከእየሱስ ኖሃ ጋር እግዚዓብሄርን በማገልገል ለ12 አመት ከቆዩ ቡኋላ በጸሎት ላይ ሳሉ ምንግዜም ከአባታችን ተክለ ሃይማኖት የማይለይ የእግዚዓብሄር መላዕክ ቅዱስ ሚካኤል ከድንገት ከምድር ነጥቆ ወደ ሰማይ አወጣቸው ነብያት እግዚዓብሄርን በከፍተኛ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ አየሁት ብለው እንደተናገሩ አባታችን በእግዚአብሄር ዙፋን ፊት ቀረቡ አእላፍ መላዕክት ሲያመሰግኑት አዩ ከዚህ ቡኋላ ክፍልህ ከሃያራቱ ካህናት ጋር ይሁን የሚል ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ አባታችንም የወርቅ ጽና ይዘው ከሃያራቱ ካህናት ጋር ሃያ አምስተኛ ሆነው በሰማይ ያጥኑ ጀመር አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ በማይታጠፍ ህያው በሆነ ቃሉ ቃል ኪዳን ገባላቸው፡፡ እርሱ ከመረጥኩት ጋር ቃል ኪዳኔን ፈጸምኩ እንዳለ አምላካችን እንዲሁ እንደወደከኝ እወድሃለሁ ስምህን ክቡር አደርገዋለሁ በጸሎትህ የሚተመነውን ሰው ሁሉ ስለ አንተ ይድናል መታሰቢያህን የሚያደርግ ሁሉ እኔ በሰማይ አከብረዋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ገባላቸው፡፡ አባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ ምድር ተመለሱ በዚህ ግዜ ወደ ፊት ስላላቸው ተስፋ ስለ እግዚአብሄር ፍቅር እንደ እሳት ልባቸው ነደደ የእግዚአብሄር መንፈስ ያሉባቸውን መጽሐፍት ያነባሉ ሌትና ቀን እየተጉ ይጸልያሉ እንቅልፍ በአይናቸው አይመጣም ከሰማይ ከተመለሱ በኋላ በሃይቅ ለአስር አመት ኖሩ፡፡
የአባታችን የጻድቁ ተክለ ሃይማኖታ የህይወት ታሪክ ስለ ክርስቶስ ያደረጉት መንፈሳዊ ተጋድሎ
እግዚአብሔር ያከበረውን ክቡር ብትለው ከንቱ ነገር ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው ያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል በምድር ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፡፡ ኢሳ 58÷13-14
ጻድቅ አባ ተክለ-ሃይማኖት
አባታችን ተክለ-ሃይማኖት ስለ አንዲት ሃይማኖት ስለ አንድ አምላካችን በስሙ ስላደረጉት ተዓምር መንፈሳዊ ተጋድሎ አጭር የህይወት ታሪክ ፡-
የኢትዮጵያ ብርሃን የእግዚ/ር አብ ምሩጥ አባታችን ተክለ-ሃይማኖት የኢትዮ ቤተ- መንግስት ከአክሱም ወደ ላስታ የተዛወረበት ዘመን ላይ በዮዲት ወረራ ወቅት ተደናግጦ የነበርው ህዝበ ክርስቲያኑ ተረጋግተው በሃይማኖታቸው እየበረቱና እየጸለዩ አምላካቸውንና አምላካችንን እያመሰገኑ የነበሩበት ዘመን ነበረ በወቅቱ የነበሩት ነገስታት እየመነኮሱና ምንኩስና እየተስፋፋ የነበረበት ወቅት ነው፡፡
Tuesday, December 9, 2014
መንገደኛዋ ታዛቢ
መንገደኛዋ ታዛቢ
ወቅቱ ክረምት ነው የአየሩ ሁኔታ የቅዝቃዜው ነገር አያድርስ ነው በረዶው መኪናም
አያስነዳም በእግርም አያስጉዝም ባጠቃላይ ምን አለፋችሁ የዚህ ዓለም ጣጣ ባይኖር ኖሮ ከቤት መውጣት አያስመኝም ነበር በማግስቱ
ታህሳስ 19 ቀን የመላዕኩ የቅዱስ ገብርኤል ክብርና ልዕልና የሚነገርበት የእነዚያ ሶስት የእምነት ጀግኖች የሲድራቅ የሚሳቅና
የአሚዲናጎም የእምነት ምስክርነት የሚወሳበት ታላቅ ክብረበዓል ነበር፡፡ እኔም የዚህን ብስራታዊ መልዓክ ተአምር ለመስመትና
የእነዚህን ሶስት ቅዱሳን ወጣቶችንም የእምነት ምስክርነት ከምንም በላይ ደግሞ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተአምር ለማየት ፈለግሁና
በመላዕኩ በቅዱስ ገብርኤል ስም የታነፀውና በአካባቢው ምዕመናን አማካኝነት ወደ ተሠራው በዋሽንግተን ሲያትል ወደ ሚገኘው
ቤተክርስቲያን ተጉዤ ነበር በአካባቢው በርካታ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰቦች የሚገኙ ሲሆን ከምንም በላይ ግን ፈሪሃ እግዚአብሔር
ያላቸው እግዚአብሔር ለራሱ የመረጣቸው የቤተክርስቲያን ማህበረሰቦችም አሉ፡፡
Tuesday, November 18, 2014
Tuesday, October 14, 2014
ማዕተብ የክርስቲያን ዓርማ
"ማህተብህን
በአንገትህ እሰረው ስትሔድ ይመራሃል
ስትተኛ ይጠብቅሃል"
ምሳ 6÷21
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች በአንገታቸው ላይ ክር
ያስራሉ ለሕፃናቶቻቸውም ክርስትና ሲነሱ ክር ያስሩላቸዋል በሕፃናቱም ሆነ በአዋቂዎቹ ክርስቲያኖች የሚታሰረው ክር በግዕዝ
ማዕተብ በአማርኛ ማተብ ይባላል፡፡ ቃሉ የወጣው ዐተበ ካለው ግዕዛዊ ግሥ ሲሆን ዐተበ ፍቺው አመለከተ ባረከ ማለት ነው፣
ማዕተብ ከዚህ ይወጣል ምልክት ማለት ነው፡፡ ለተጠመቁ ክርስቲያኖች የክር ማዕተብ ለሃይማኖት ምልክትነት ወይም መታወቂያ ከመሆኑ
በፊት በብሉይ ኪዳን ዘመን የሃይማኖት አባቶች ከጣዖት አምላኪዎች ተለይተው የሚታወቁበት ምልክት ነበራቸው፡፡
Thursday, October 9, 2014
ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ከክርስትና በፊት ሥዕል በቤተ አሕዛብም ሆነ በቤተ አይሁድ የታወቀና ከአምልኮት ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ በቤተ አሕዛብ ዕንጨት ጠርቦ ደንጊያ አለዝቦ ማምለክ የተለመደ ነበር፡፡ እንዲያውም የሮማ ነገሥታት አማልክት ተብለው ከመመለካቸው በላይ ከሞቱ በኋላ ሥዕላቸው በደንጊያና በዕንጨት እየተቀረጸ ሲመለኩ መኖራቸው በታሪክ ይታወቃል፡፡ ክርስትና በመጣ ጊዜም ከክርስትና ጋር ያጣላቸው ይኸው ልማዳቸው ነው፡፡ በክርስትና ትምህርት ይህ አምልኮ ጣዖት ነውና፤ በቤተ አይሁድም እንደ አሕዛብ ሳይሆን በታቦተ ሕጉ በጽላተ ኪዳኑ ላይ ሥዕለ ኪሩብን እንዲስል ራሱ እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት ነበር፡፡
ከክርስትና በፊት ሥዕል በቤተ አሕዛብም ሆነ በቤተ አይሁድ የታወቀና ከአምልኮት ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ በቤተ አሕዛብ ዕንጨት ጠርቦ ደንጊያ አለዝቦ ማምለክ የተለመደ ነበር፡፡ እንዲያውም የሮማ ነገሥታት አማልክት ተብለው ከመመለካቸው በላይ ከሞቱ በኋላ ሥዕላቸው በደንጊያና በዕንጨት እየተቀረጸ ሲመለኩ መኖራቸው በታሪክ ይታወቃል፡፡ ክርስትና በመጣ ጊዜም ከክርስትና ጋር ያጣላቸው ይኸው ልማዳቸው ነው፡፡ በክርስትና ትምህርት ይህ አምልኮ ጣዖት ነውና፤ በቤተ አይሁድም እንደ አሕዛብ ሳይሆን በታቦተ ሕጉ በጽላተ ኪዳኑ ላይ ሥዕለ ኪሩብን እንዲስል ራሱ እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት ነበር፡፡
Sunday, September 28, 2014
“ዕፀ መስቀሉ ከየት መጣ”
“ዕፀ
መስቀሉ ከየት መጣ”
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ
ለምንድን ግን የእግዚአብሔ ኃይል ነውና እንደተባለው በቆሮ 1÷18/ ክርስቲያኖች ኃይላችን፣ መመኪያችን፣ ነፍሳችን መዳኛና የምንጸናበት
መስቀል እናምናለን፡፡ ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “እግሮቼ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን” እንዳለም /መዝ 131÷7/ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ውሎ እኛ ለሠራነው ኃጢአት ካሣ እንደሆነ እያሰብን እንሰግድለታለን፡፡ በልባችን፣ በሰውነታችንና
በቤታችን እንስለዋለን፡፡ በአባቶቻችን እንባረክበታለን፡፡ እንደትምህርታችን የድኅነታችን ብርሃን የበራበት ይህ መስቀል የእንጨት
ነው፡፡ እንጨት ከመሆኑ ጋርም አንድም ለመስቀሉ ካላቸው ፍቅር ወይም ታሪክን በተረት ቀርፀው ከማስቀረት ልማዳቸው የተነሣ ይህ መስቀል
ከየት መጣ? ለሚለው አባቶች የሚተርኩት አንድ ታሪክ አለ፡፡ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
Thursday, September 25, 2014
ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠኃቸው
ከላይ በርእስነት ያነሣነውን ኃይለቃል
በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ነቢዩ ዳዊት ተናግሮታል፡፡ አባቶች ነገሮች ከመፈጸማቸው በፊት አስቀድሞ ትንቢት አላቸው ሲሉ ትንቢት
ይቀድሞ ለነገር" እንዲሉ፡፡ (መዝ. ፶፱÷፬)
የእግዚአብሔር ወዳጅ፣ መዝሙረኛው ዳዊት
በትንቢት መነጽርነት የተረዳው ምስጢር ቢኖር መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተሰቀለበት ክቡር መስቀል የሚያድን፣ ከሰይጣን የሚታደግ፣
ከክርስቲያኖች ጋሻ ሆኖ የተሰጠበ በረከት መሆኑን ነው፡፡ ነቢዩ የመስቀሉን አዳንነት የተገነዘበው በተሰጠው የትንቢት ጸጋ
ነው፡፡ በቀራንዮ መሥዋዕት የሆነው ቸሩ አምላክ ክቡር መስቀሉን ሊቀድሰው ስለፈለገ ቅዱስ ሥጋውን ቆረሰበት ክቡር ደሙን
አፈሰሰበት፡፡
Wednesday, September 10, 2014
‹‹አዲስ ልብንና አዲስ መንፈስን ለእናንተ አድርጉ›› (ሕዝ 18፡31)
መልካም አዲስ ዓመት
ኃይለ ቃሉን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሚመክርበት ዘመን ከአበይት ነቢያት አንዱ በሆነው
በነቢዩ በሕዝቅኤል በኩል ስለብዙ ነገር ተናግሮታል፡፡ ለጊዜው ለእስራኤል ዘሥጋ ይነገር እንጂ ፍጻሜው ግን እኛም እንማርበት ዘንድ
ተመዝግቦልናል፡፡ በመሆኑም የዚህ ጽሑፍ ዋና መልዕክትና መሠረታዊ ዓላማ በምድራዊው የኮንትራት ኑሯችን በዘመን ተሰፍሮና ተወስኖ
በተሰጠን ዕድሜ በተለይም በቀሪ ጊዜያችን አሮጌውንና የዛገውን ልብ አውጥተን አዲስ ልብን ገንዘብ እንድናደርግና በአዲስ ሕይወት
እንድንመላለስ ማሳሳብ ነው፡፡
Saturday, June 28, 2014
‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም›› (ማቴ16፡18)
ይህንን ኀይለ ቃል ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊሊጶስ ቂሳሪያ ለሊቀ ሐዋርያት ለቅዱስ
ጴጥሮስ ተናግሮታል፡፡ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወለድ በተለየ አካሉ ጸጋና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ፡፡ (ዮሐ
1፡14)
ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም ነፍስና ሥጋን ነስቶ በፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆነ ‹‹ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ ከዘመን አስቀድሞ የነበረ
እርሱ ትንሽ ህፃን ሆኗልና፣ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘላለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ
ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ ኀጢዓትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት ይህን
ወድዷልና፡፡ ክብሩ ተለይቶት የነበረ ሥጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው የጸጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ሥጋንም የባሕርይ ገዥ ሊያደርገው
ወደደ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ››
(ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 220)
Monday, June 16, 2014
ክርስቲያናዊ ቤተሰብእ
ቤተሰብእ ማለት በቅዱስ ጋብቻ አማካይነት በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች (ወንድና ሴት) ግንኙነት የሚጀመረውና
ቁጥራቸው ይነስም ይብዛም የሚወለዱትን ልጆች ጨምሮ በጋራ የሚመሰረተው ማኅበር ነው፡፡
እንዲህ ዓይነት ቤተሰብእ የሚመሰረተው በቅዱስ ጋብቻ በሥጋውና ደሙ አማካኝነት ነው ይህም የጋብቻ ቡራኬና ጸሎት የሚፈጸመው አምላካችን እግዚአብሔር በሥነ-ፍጥረት
ጊዜ ሰው እንዲበዛ ቅዱስ ፈቃዱ ስለሆነ ለመባዛቱም ምክንያት የሚሆነው የወንድና የሴት ግንኙነት ሲኖር መሆኑን በማረጋገጥ አዳምና
ሔዋንን ፈጥሮ እንዲህ ሲል የፈጸመውን የመጀመሪያ የተክሊል ጸሎትና ቡራኬ መነሻ በማድረግ ነው ‹‹እግዚአብሔርም ሰውን ፈጠረ በመልኩ
በእግዚአብሔር መልክ ፈጠራቸው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው እግዚአብሔርም አላቸው ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት የባሕሩንም አሣ የሰማዩንም
ወፍ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሰውን እንሰሳ ሁሉ ግዙ›› ዘፍ 1፡27
Tuesday, June 3, 2014
Monday, April 28, 2014
Friday, April 25, 2014
ክርስቲያን በመሆንህ ታፍራለህ?
ክርስቲያን በመሆንህ በሌሎች ፊት ያፈርህበት ጊዜ
ነበር? ምንአልባት ከማያምኑ ጋር ምግብ ልትበላ ቀርበህ
ሳለ በእነርሱ ፊት መጸለይ አሳፍሮህ ያውቃል? ወይም ማማተብ እየፈለግህ ሌሎች ስለሚያዩህ እምነት
በልብ ነው ብለህ በህሊናዬ አማትቤያለሁ ያልክበት ጊዜ ይኖር ይሆን? ብቻ በአንድም መንገድ ይሁን በሌላ ከማያምኑ ጋር ስትሆን ወይም ለብቻህ ሳለህ የምታደርገውን መንፈሳዊ ነገር ሌሎች ሰዎች
የሚሉህን በመፍራትና በማፈር ሳታደርገው ቀርተህ አታውቅ ይሆን? ብዙዎቻችን አምነንበታል ስለምንለው ነገር እኛ ሄደን እነሱ ዘንድ ልንመሰክር ቀርቶ ገና ለገና ያዩናል በማለት ሁል ጊዜ
የምናደርገውን መንፈሳዊ ነገር ስንቀንስ ይታያል ይህ ግን ግብዝነት አይደለም ትላለህ?
የሴኬምን እንቅፋት ማስወገድ
ሴኬም በውስጧ ርኩሰትና አማልክት የሞላባት የአሕዛብ
ከተማ ነች፡፡ ከእቅፋቶቿ ብዛት የተነሳ ለመንፈሳዊ ሕይወት ምቹነት የላትም ለዚህም ነበር እግዚአብሔር ያዕቆብን ‹‹ከሴኬም ተነስተህ
ወደ ቤቴል ውጣ›› ያለው ዘፍ 35፡1፡፡ ቤቴል ማለት የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው ያዕቆብ ከልጆቹ ላይ ጌጣጌጥን አማልክትን ሳይቀር
ተቀብሎ በጉድጓድ ውስጥ ቀበራቸው፡፡ የሴኬም እንቅፋት ናቸውና ለቤቴል ኑሮ አይገቡም፡፡ ይህን ይዞ ቤቴል ቢገዛ ኖሮ የቦታ ለውጥ
እንጂ ትክክለኛ የሕይወት ለውጥ አይሆንለትም ነበር እንቅፋቶቹ ዛሬም አሉና፡፡
Thursday, April 24, 2014
Wednesday, April 23, 2014
‹‹ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብሩ መጣች›› (ዮሐ ፳፩፣፩)
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን=>በዓቢይ ሃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን => አግአዞ ለአዳም
ሰላም => እምእዘየሰ
ኮነ => ፍሰሃ ወሰላም።
+ ትረጉም +
--------------------
ክርስቶስ በታላቅ ሃይሉና ሥልጣኑ ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነሳ፤
ሰይጠንን አሰረው፤ አዳምን ነፃ አወጣው፤
ከእንግዲህ ወዲህ ፍሰሃ፣ ሰላም፣ ደስታ ሆነ:: አሜን!
አሰሮ ለሰይጣን => አግአዞ ለአዳም
ሰላም => እምእዘየሰ
ኮነ => ፍሰሃ ወሰላም።
+ ትረጉም +
--------------------
ክርስቶስ በታላቅ ሃይሉና ሥልጣኑ ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነሳ፤
ሰይጠንን አሰረው፤ አዳምን ነፃ አወጣው፤
ከእንግዲህ ወዲህ ፍሰሃ፣ ሰላም፣ ደስታ ሆነ:: አሜን!
መግደላዊት ማርያም መጌዶል በሚባለው የትውልድ አገሯ መግደላዊት ማርያም ትባላለች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
ብዙ ማርያሞች ስላሉ መግደላዊት ማርያም በመባል ተለይታ ተጠቅሳለች በውስጧ ታላቅ የፍቅር ትንታግ የሚቀጣጠልባት መግደላዊት ማርያም
እስከዚህ ቀን ድረስ እንዴት ታግሳ ተቀመጠች? ስንል ጌታችን የተቀበረው ዓርብ ማታ ነው ቅዳሜ እንዳትመጣ የአይሁድ ሰንበት ነው በሰንበት ከተወሰነ
ኪሎ ሜትር በላይ መጓዝ ስለማይቻል በሕግ ገደብ ተይዛ ቅዳሜን ከሌሎች ቅዱሳን አንዕስት ጋር በጭንቀት አሳለፈች፡፡
Saturday, April 19, 2014
‹‹ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን መካከል ተነስቷል››
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ~~~~~~በዓቢይ ሃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን ~~~~~~~ አግአዞ ለአዳም
ሰላም ~~~~~~~~ እምእዘየሰ
ኮነ ~~~~~~~ ፍሰሃ ወሰላም። አሜን!!!
+++ ትረጉም +++
ክርስቶስ በታላቅ ሃይሉና ሥልጣኑ ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነሳ፤
ሰይጠንን አሰረው፤ አዳምን ነፃ አወጣው፤
ከእንግዲህ ወዲህ ፍሰሃ፣ ሰላም፣ ደስታ ሆነ!!! አሜን! —
ጌታችን አምላካችን
መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ነውና መቃብር ይዞ አላስቀረውም፣ ትንሣኤ ነውና ሞት በእርሱ ላይ ስልጣን አልነበረውም በመሆኑም
ከሦስት መዓልትና ሌሊት በኋላ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ሞትን ድል አድርጎ መውጊያውንም ሰብሮ በኃይሉ ተነስቷል፡፡
‹‹ኦ መዊት አይቴ ሃሎ ቀኖትከ›› ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህ የታለ›› ተብሎ በትንቢት በተነገረው መሠረት
ገዥውንና ኃያሉን አሸንፎ መውጊያውን ሰብሮ ጌታችን ተነስቷል፡፡
Thursday, April 17, 2014
‹‹ከክርስቶስ ጋር አብረን ከሞትን አብረን እንነሳለን››
‹‹ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሳኤውንም በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን›› ሮሜ 6፡5
‹‹ከክርስቶስ ጋር አብረን ከሞትን አብረን እንነሳለን››
ኢየሱስ ክርስቶስ
የሞተውን አዳም ለማዳን ሥጋን ተዋሕዶ እንደሚሞት የሚያውቀው ከዘመናት በፊት ነው፡፡ ቤተልሔም ከመወለዱም በፊት የሚሞትበት ጊዜ
እየቀረበ እንደሆነ፣ የሰውን ልጅ ሥጋ የለበሰውም ሞቶ ሞትን ለመግደል እንደሆነ ያውቃል የመጣበት ዓላማም ለሞመት ነው ለደቀመዛሙርቱም
በተለያየ ጊዜ በምሳሌ ነገረ ሞቱንና ጊዜያቱን ነግሮአቸዋል፡፡ ‹‹በደብረታቦር ብርሃነ መለኮቱን ከገለጸበት ቀን ጀምሮ አለቆች ከጻፎችም
ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀመዛሙርቱ ይገልጥላቸው ነበር›› (ማቴ 16፡21)
ለሚጠሉት ላሰቃዩት ለአይሁድ እንኳ ሳይቀር በምሳሌ ይነግራቸው ነበር ‹‹ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ››
አላቸው፡፡ (ዮሐ 3፡19)
Thursday, April 10, 2014
‹‹የአሸናፊነት የድል ጩኸቶች››
ጌታችን መድኀኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለ በኋላ በመስቀል ላይ ሆኖ የተናገራቸው 7ቱ አጻርሐ መስቀል በመባል የሚታወቁት የአሸናፊነት የድል ጩኸቶች
ናቸው፡፡
1. ‹‹ኤሎኼ ኤሎኼ ኤልማስ ላማ ሰብቅታኒ››
አምላኬ አምላኬ
ለምን ተውኸኝ ማለት ነው (ማቴ 27፡46) ይህን አሰምቶ የተናገረው በ9 ሰዓት ነው እርሱ አምላክ ሆኖ ሳለ አምላኬ አምላኬ ለምን
ተውከኝ ብሎ የተናገረው ለምንድን ነው፣ ቢሉ ከሕገ-እግዚአብሔር ርቆ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የተተወ አዳምን ሥጋ ተዋሕዶ
ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጥ ነው፡፡
ይህንን ቃል
አምላካችን ስለ ብዙ ነገር ተናግሮታል
Monday, April 7, 2014
የቀድሞው ስምዖን ዛሬ በእኔ ውስጥ እንዴት ይቀየር?
በስመ አብ ወወልድ
ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ይድረስ የእግዚአብሔር
መንግስት ቁልፍ በእጁ ላለ ስለ ሞተልህም ስለ ክርስቶስ ስም በሮም አደባባይ ቁልቁል ለተሰቀልህ ታማኝ ምስክር ለሆንከው ለቅዱስ
ጴጥሮስ፡፡ በጌታ ፊት በምስጋና ለጸናች ነፍስህ ሰላም እላለሁ፡፡ ጴጥሮስ ሆይ ከዚህ ምድር ከተለየህባት ጊዜ ጀምሮ ስለ ነፍሴ እየተጋህ
እንደሆነ እምነቴ ነው፡፡ ጴጥሮስ ሆይ የፈተናው ዓለም ሕይወት እንዴት ይዞሃል? ብትለኝ ልክ አንተ በመንፈስ ቅዱስ ታድሰህ በእምነትና በቅድስና ከመመላለስህ
በፊት ያለውን የቀደመ ሕይወትህን ይመስላል እልሃለሁ፡፡
Monday, March 31, 2014
‹‹በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን››ክፍል ፪
‹‹ስለ መተላለፋችን ቆሰለ
ስለ በደላችንም ደቀቀ›› ኢሳ 53፡6
ባለፈው ጊዜ
የነቢዩ የኢሳይያስን መጽሐፍ መሠረት አድርገን የጌታችንን የመድኀኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ሕማም መከራ መስቀል ለማየት ጀምረን
ነበር፡፡ እሱ ጥልቅ በሆነ ፍቅሩ ስለወደደን መተኪያ በሌላት ነፍሱ ተወራርዶ አዳነን፣ ነቢያት በትንቢት መጽሐፋቸው፣ ሐዋርያት በስብከታቸው
ስለ ፍቅር አስተምረዋል እሱ ግን ፍቅርን በተግባር ገለጠው፣ እጆቹንና እግሮቹን በመስቀል አስቸነከረ ይህን ያህልም እወዳችኋለሁ
ብሎ ነፍሱን ሰጠ፣ ፍቅርንም በተግባር ሰበከ እኛም አርአያውንና ፈለጉን እንከተል ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነውና፡፡ በፍቅር እንሁን…..ብለን
ነበር ክፍል አንድን የፈጸምን ቀጣዩን ክፍል ደግሞ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን ጀመርን፡፡
Friday, March 28, 2014
አንተ ካልፈረድህባት እኔ ማነኝ?
ጌታ ሆይ አንተ
ብቻ እውነተኛ ዳኛ ነህ፡፡ ሰው ውጪን ይመለከታል አንተ ግን ውስጥን ትመረምራለህ፡፡ ልብ የመከረውን ህሊና የወጠነውን ታውቃለህ
ሰው ላይ ላዩን አይቶ ይፈርዳል፡፡ አንተ ግን የልቦናን ጥልቀት አይተህ ትፈርዳለህ እንደ ሰው ቢሆን አይሁድ ወደ አንተ እያዳፉ
ያመጧት ሴት ተወግራ ትሞት ነበር፡፡ ኸረ እንደ ሰውማ ቢሆን ማን ይቆም ነበር? ሕግን የምትሰጥም የምትፈርድም አንድ አንተ ነህ
ልታጠፋም ልታድንም የምትችል አንድ አንተ ነህ ታዲያ እንዲህ ከሆነ እንደ እኔ ላለው ሰው በሌላው ይፈርድ ዘንድ ማን ሰጠው?
‹‹በእርሱቁስልእኛተፈወስን››
ክፍል ፩
‹‹ነስአ ደዌነ ወጾረ ሕማምነ››
(ኢሳ 53፡4)
‹‹ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንን
ተሸከመ››
ልዑለ ቃል ኢሳይያስ በትንቢት መጽሐፉ ደረቅ ሐዲስ እየተባለ በሚጠራው ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ
ምስጢሩን ስለገለጸለት የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ መስቀል በትህትና መንፈስ በመሆን መዝግቦልናል፡፡
ሙሴ በምድረበዳ
እባብን እንደሰቀለ እንዲሁ በእሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ሊሰቀል ይገባዋል፡፡
(ሐዋ 3፡14) ተብሎ እንደተፃፈ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ በዘመኑ ፍጻሜ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ከሰማየ ሰማያት
ወርዶ መለኮታዊ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ሥጋ በመልበስ ፍጹም ሰው በመሆን በተዋሕዶ ከበረ፡፡
ከዚህም የተነሳ
የማይራበው ተራበ፣ የማይጠማው ተጠማ ኅይለኛው ደከመ፣ የወደቁትን የሚያነሳ እሱ ወደቀ፣ እውነተኛ ዳኛ ፈታሒ በርትዕ ሆኖ ሳለ በአይሁድ
ተከሶ እንደ ወንጀለኛ በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡
Tuesday, March 25, 2014
Subscribe to:
Posts (Atom)